ሳይታሰብ ብልጭ ብላ እንደገና ድርግም ያለችው የለውጥ ጭላንጭል፣ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ተቋጥራ የነበረች የተስፋ ስንቅንም ይዛ ጭልጥ ያለች ይመስላል። አዕምሯችን ይህንን ቅጽበታዊ ለውጥ ለመቀበል ቢቸግረውም፣ በሌላኛው መነጽር ስንመለከተው ግን ይህ ሊሆን ግድ ይላል። በተዓምር የቆመች የዚህች የደም ምድር እጣ ፈንታን መጽሃፉ በአንዲት ምዕራፍ ውስጥ እንደቋጫት እንገነዘባለን። አይናችንን በደንብ ካልገለጥን ግን ነገሩን ላናየው እንችላለን። ስለዚህ መፅሐፉን ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። መረዳትንም ይጠይቃል። በደንብ የተረዳው ሰው፣ በለሆሳስ የተላለፈ መልዕክቱን ያገኘዋል። መልዕክቱም ግልጽ ነው። የነጻነት ተጋድሎ። በዚህ ፍልሚያ ውስጥ ሶስት ተዋንያን ይኖራሉ። ተሻጋሪ ሕዝብ፣ አሻጋሪ ሰው እና አሳዳጅ ሃይል። ከብዙ ትንቅንቅ እና ተጋድሎ በኋላ የአሳዳጁ ገቢር ከትዕይንቱ ይወጣና ሁለቱ … [Read more...] about “እርካብና መንበር” – ሙሴ እና ዐብይ*
Opinions
የኔ ሃሳብ
የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
ኢህአዴግ መሽቶበታል። አቅሙ ክዶታል። ባልሞት ባይ ተጋዳይነት አለሁ ቢልም ዘላለማዊ ዕንቅልፉ ግን የሚቀርለት አይመስልም። የሜክሲኮውን ፒ አር አይ ፓርቲ አርአያው አድርጎ ሰባ አመታትን እጓዛለሁ ብሎ የተነሳው ድርጅት ግማሽ መንገድ እንኳን ሳይጓዝ ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል። ገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው የርዕዮተዓለም ልዩነት በማይታረቅ መንገድ የአደባባይ ሙግት ጀምሯል። ኦዲፒ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መማል ካቆመ ቆይቷል። ሊቀመንበሩ ዓብይ አህምድም (ዶ/ር) ከትናንት ጋር የተኳረፉት ለዚህ ይመስላል። ብአዴን የምመራበትን ርዕዮተ ዓለም ዳግም አጤነዋለሁ ብሎ ዛሬ መወያየቱን ጀምሯል (ይህ ዘገባ ከተጻፈ በኋላ ብአዴን አዴፓ በሚል ህወሓት የሰጠውን ቀይሮታል)። ከዚህ በአንጻሩ ህወሓት አብዮታዊ ዲሞክራሲን ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ ብሎ ሙጥኝ ማለትን ወዷል። ደኢህዴን ሁለት ጎራ ይዞ የለየለት ፍልሚውን … [Read more...] about የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…
መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ ይከለላሉ ይባል ነበር፤ አሁንም ያው ይመስላል! ያነበብሁትን በትክክል ካስታወስሁት በጥንታውያን ግሪኮች ሰርቀው መያዝ እንጂ መስረቅ ወንጀል አልነበረም (የምታስታውሱ አርሙት)፤ የምንመሳሰለው በጥንታዊነት ብቻ መስሎኝ ነበር! ከዚህ ቀደም ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ይመስለኛል) ተረግመናል ብሎ፤ ነበር፤ እኔንም መሰለኝ! ኢትዮጵያውያን መልካቸውን፣ ነብሮች ቆዳቸውን እንዴት ይለውጣሉ ያለው መልካችንን ነበር፣ ወይስ ጠባያችንን ማለቱ ነበር! ነገሬ ሁሉ የጥንቶቹን አባትና እናት … [Read more...] about መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ተደጋጋፊ ወይስ ተገዳዳሪ?
“ኢትዮጵያ አገራችን የየራሳችን አኩሪ ባህል ያለን፣ የየራሳችን መልክዓ ምድር፣ አሰፋፈር የነበረንና ያለን፣ ብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት አገር በመሆንዋ ያፈራነው የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፣ መጪው የጋራ ዕድላችን መመሥረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል ጥቅማችንን፣ መብታችንንና ነፃነታችንን በጋራና በተደጋጋፊነት ለማሳደግና አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመገንባቱን አስፈላጊነት በማመን እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ይኼንን ሕገ መንግሥት በተወካዮቻቸው አማካይነት አፅድቀነዋል።” ከላይ የተገለጸው በ1987 ዓ.ም. ከፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መግቢያ ላይ የተወሰደና አገሪቱ ካለፉት 23 … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ተደጋጋፊ ወይስ ተገዳዳሪ?
በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች
ባንዲራ የአንድ አገር ሕዝብ ማንነት መገለጫ ነው። የሰው ልጆች በታሪካቸው ውስጥ የየራሳቸውን ቡድን ወይም ወገን ከሌሎች ለመለየት ጨርቅን በተለያዩ ቀለሞች በመቀባት፣ እንጨት ላይ ሰክተው በእጃቸው ይዘው በመዞር፣ አንገታቸው ላይ በማሰር ወይም ጎልቶ እንዲታይ ከማሰብ አንጻር ረዘም ባሉ እንጨቶች ላይ እየሰቀሉ ከማንነት መገለጫም ባሻገር ይዞታን ወይም ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ይጠቀሙበት እንደነበር የሕብረተሰብ ታሪኮች መዝግበዋል። ባገራችን ባንዲራ እንደ ኢትዮጵያ መገለጫ ሆኖ መቼ እንደቀረበ በትክክል ባይታወቅም፣ ባንዲራን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ያስተዋወቁት አጼ ምኒልክ መሆናቸው በሰፊው ይነገራል። ያኔ ትክክለኛ ስሙ “ሰንደቅ ዓላማ” በመባል ቢታወቅም፣ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ ግን “ባንዲራ” በሚለው የጣሊያንኛ ቃል ተተክቶ ዛሬ በስፋት እየተጠቀምንበት ነው። … [Read more...] about በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች
የጎሳ ፖለቲካ ጣጣ፣ ‘ሀዘናችን ቅጥ አጣ’
ከአንድ ሃዘን ወደ ሌላ፤ ላለፉት ጥቂት ወራት ክልላትን እያዳረሰ ያለውና ጎሳ ላይ ያነጣጠረው ግጭት ከቡራዩ ሃዘን ሳናገግም በዚህ ሳምንት ደግሞ ዳግም ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዞረ። በክልሉ ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ፣ አማራ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይ ሌላ አስከፊ ጥቃት መፈጸሙን መርዶ ሰማን። ሰዎች ተገድለዋል፤ በአሥር ሺዎች ተፈናቅለዋል። ለዚህም ጥቃት የተለያዩ ኃይሎች እንደ ምክንያት እየተጠቀሱ ነው። ከእንዲህ ያለው አስነዋሪ እና እጅግ ኋላ ቀር ከሆነ የጎጠኝነት ስሜት እንዴት ይሆን የምንላቀቀው? በጎጥ ጥላቻ ላይ ምህለቁን የጣለው ዘር ተኮር ፖለቲካችንስ መቼ ይሆን የሚጸዳው? ከእንዲህ ያለው ቅርቃር ለመውጣት እንደ ሰው ማሰብ ብቻ ይበቃን ነበር። ከዚያም ሲያልፍ የአንድ አገር ልጆች በመሆናችን ብቻ ልንተዛዘን፣ ልንደጋገፍ እና አብረን ልንኖር በቻልን ነበር። ይህ ሁሉ ቢቀር በየጎሳ … [Read more...] about የጎሳ ፖለቲካ ጣጣ፣ ‘ሀዘናችን ቅጥ አጣ’
የጠብ ሱስ
ከጅብ ከበሮ የተሰራ አታሞ ዘወትር እንብላው፤ እንብላው ይላል የሚል ተረት ሰምቻለሁ ልበል? አዎ፤ ሳልሰማ አልቀርም። ሀሳቡም ግን ጅብ ቆዳ ሆኖ እንኳን (ቆዳ ሆኖ ብቻ አይደለም አታሞ ተለጉሞበትም) ያው የተፈጥሮ እንብላ ባይ ባህሪውን አይተውም ማለት ይመስለኛል። ያው ቢሞትም ቆዳው የጅብ ነዋ። ይህን ምሳሌ ያስታወሰኝ የሰሞኑ የአምስት የዖሮሞ ድርጅቶች ያወጡት ጠብ ያለሽ በዳቦ አይነት መግለጫ ነው። በእርግጥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች አይነተኛ ተግባር ምናልባትም ቋሚ ስራ መግለጫ ማውጣት ስለሆነ ድርጅቶቹ ያው እንደለመደው ሰብሰብ ብለው እስቲ መግለጫ እናውጣ ቢሉ ያባት ይባል ነበር። የነዚህኞቹ ግን የዘር አዋጅ እንጂ መግለጫ የሚባል ስላልሆነ በእውነቱ በጥብቅ የሚያነጋግርም የሚያስተዛዝብም ምናልባትም ደግሞ ህግ ካለም በህግ የሚያስጠይቅ ግዴለም አቅልለን እንመልከተው ካልን ደግሞ … [Read more...] about የጠብ ሱስ
የክልሎች የመሬት ቅርምት እና ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፓሊሲ
1) መነሻ እውነታዎች፤ በዚህ ቋንቋን መሰረት ባደረ የጎሳ ፌዴራል ስርዓት፦ (ሀ) ጊዜ ያነሳቸው ባለጉልበቶች በጎሳና በቋንቋ ተቧድነው የኢትዮጵያን ህዝብ የጋራ መሬትና የተፈጥሮ ሃብትን ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ አግበስብሰው በመያዝ ከዚህ መስመር አትለፍ፣ ይህ የኔ ክልል ነው አንተን አይመለከትህም፣ መጤዎች ከክልላችንን ለቃችሁ ውጡ፣ መሬቱን እንፈልገዋለን ወደ ሃገራችሁ ሂዱ እያሉ የሃገሪቷን ዜጎች ተወልደው ካደጉበት፣ አድገው ከተዳሩበት፣ ወልደው ከከበዱበት ከሃገራቸው ላይ እንደ ዋዛ ቤተስብ በሚያፈርሱበትና በሚያፈናቅሉበት፣ በተለይም አንዱ የሃገር ባለቤትና አፈናቃይ ሌላው በሃገሩ ላይ ባዳና ሁለተኛ ዜጋ በሆነበት ሁኔታ፣ (ለ) ጥቂቶች የሃገርን ሃብትን ዘርፈውና የንፁሃንን ደም አፍሰው፣ በየእስር ቤቱ ዜጎችን ቶርቸር እያደረጉና እያሰቃዩ ከህግ በላይ ሆነው ሰውንም እግዚአብሔርን … [Read more...] about የክልሎች የመሬት ቅርምት እና ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፓሊሲ
“በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ገዱ አንዳርጋቸው በምሁራን መድረክ ያድረጉት የመክፈቻ ንግግር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበራችሁ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች! እንኳን ወደ አማራ ክልል መዲና ውቢቷ ባህርዳር ከተማ በሠላም መጣችሁ! ከነገሬ ሁሉ በማስቀደም የአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ የጐደለውን ትሞሉለት ዘንድ ምክራችሁን እና የሙያ ድጋፋችሁን በመሻት ለልጆቹ ያደረገውን ይህን ታሪካዊ ጥሪ ያለምንም ማቅማማት ተቀብላችሁ እዚህ በመካከላችን በመገኘታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በረጅሙ የሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ ህዝብ በስልጣኔ፣ በተለይም በመንግስት አስተዳደር፣ በታሪክ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በአርበኝነት ተጋድሎ እንዲሁም በኢኮኖሚ ዕድገት ለሃገር ያበረከተው ድርሻ ትልቅና አይረሴ ቢሆንም ያለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት … [Read more...] about “በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
Abiy lamented about the country’s lack of project management competency in his first press release
I've not yet watched the Press Release (PR) Abiy gave this morning. However, I was given a short clip taken from the PR where he was talking about why mega projects are failing in Ethiopia. He is right on the money. He pinpointed the culprit - the country's lack of capacity to implement the principles of Project Management. This is not the first time he was lamenting about it. A couple of months ago, I remember Abiy talking to the business community where he emphasized the need to build the … [Read more...] about Abiy lamented about the country’s lack of project management competency in his first press release










