የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ነሃሴ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በብአዴን 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርትና ለጉባዔው በሚቀርቡ ሌሎች ወቅታዊና መደበኛ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት በሀገር ደረጃና ብአዴን በሚመራው የአማራ ክልል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝና ታሪካዊ ጊዜ ላይ የሚካሄድ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ድርጅቱ የመሪነት ሚናውን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ለጉባኤው እንዲቀርቡ ጥልቀት ያለው ውይይት ካካሄደ በኋላ በጉባዔ አጀንዳዎችና በሌሎች ጉዳዮች ስምምነት ላይ በመድረስ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡ በመቀጣጠል … [Read more...] about “ብአዴን ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል” የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ኢትዮጵያ ድምፅ ሬድዮ 25ኛ አመት
ከስዊድን ሃገር የሚሰራጨዉ የኢትዮጵያ ድምፅ ሬድዮ የተመሰረትበትን 25ኛ አመት ካድማጭ ወዳጆቹ ጋር ለማክበር ዝግጂቱን በሰፊዉ እያከናወነ ይገኛል። ሁላችሁም ታድማችኋል። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድምፅ ሬድዮ 25ኛ አመት
ተአምረ ኦሮሞ ወአማራ
ፍቅሬ ቶሎሳ ራሱን ከማናቸውም የጎሣ ቆዳ ገሽልጦ ወጥቶ፤ መጨረሻውን በቅጡ ሳያውቅ ከሀረር ተነሥቶ በአሜሪካ ዞሮ ኢትዮጵያ ገባ፤ በሁለት እጆቹ ኦሮሞንና አማራን በጋማቸው ይዞ አዛመዳቸው፤ የፍቅሬ ቶሎሳ ሀሳብ፣ እምነት፣ ሕልም (አንዳንዶች ቅዠት ይሉታል፤) ገና ባልታወቀ መለኮታዊ መንገድ ዞሮ ዞሮ ለማና ዓቢይ የሚባሉ ሰዎችን ያፈራ የኢትዮጵያ መሬት ላይ አረፈ፤ የኢትዮጵያን መሬት ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ነዘረው፤ ለማና ዓቢይ የሚባሉትን ሁለት ኢትዮጵያውያን ከአንድ መቶ ሚልዮን ሕዝብ መሀል ነቅሶ አውጥቶ አንቀረቀባቸው፤ ለማንና ዓቢይን አንቀርቅቦ አወጣና አንድ አደረጋቸው! ዘር፣ ፖሊቲካ፣ ጥቅም፣ ሥልጣን፣ ጉልበት ወይም ሀብት አይደለም፤ እግዚአብሔር በረቂቅ ጥበቡ ፍቅሬን ከአሜሪካ ለማንና ዓቢይን እነሱ በማያውቁት መንገድ አገናኝቶ፣ እነሱ ባልገባቸው መንገድ አስማምቶ … [Read more...] about ተአምረ ኦሮሞ ወአማራ
አብርሃ ደስታ ስለ ህወሓቶች፤ “አሳልፈን አንሰጣቸውም”
"አብርሃ ደስታ ሆይ!" ጃዋር በኦነግ የፊደል መማርያ ማደጉን እና አንተም በወያኔ የጥላቻ መማርያ ደብተር ማደግህን ለዛሬ የተበረዘ አስተሳሰባችሁ አስተዋጽኦ ቦኖረውም (ለዛወም ይሆናል “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ” ብሎ ጃዋር ሲል ፖለቲካው ይመቸኛል ያልከው) ትንሽ ስታድግ አክራሪ ብሔረተኛነትክን ትንሽም ቢሆን ማሻሻል ነበረብህ። ሆኖም ፈቀቅ አላልክም። አፈር በል! በፖለቲካው እየሸበትክ ስትመጣ “ሰከን ስትል” የኋለ ኋላ የምትናገራቸው ነገሮች መልሰው ይከነክኑሃል። አብርሃ ደስታ ዞሮ ዞሮ የወያኔ ጀሌ ነው እያልን ስንናገር፤ ብዙ ሰዎች አላመኑም ነበር። ጀሌ ማለት የግድ አባል መሆን ማለት አይደለም። ድሮ የተከናነበበትን ማጃጃያ ነጠላውን ጥሎ ዛሬ በግልጽ ስለወያኔዎች ወንጀለኞች ጥብቅና ቆሞ እየተከራከረ ነው። ድሮም ዛሬም ከወያኔ የተደመረ እንጂ ከወያኔ የተለየ ሰው አልነበረም … [Read more...] about አብርሃ ደስታ ስለ ህወሓቶች፤ “አሳልፈን አንሰጣቸውም”
አሸንዳ/ሻደይ ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኤርትራ የሚከበር “የጋራ ጸጋና ህዝባዊ በረከት እንጂ የምንጣላበት፣ እንደ አላቂ ሃብት በድርሻ-ድርሻ የምንካፈለው አይደለም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድየ የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነትና የወንድማማችነት ህያው ማስረጃ! በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን የሃገራችንን ህዝቦች እንዳይበታተኑ ያስተሳሰሩ፤ እንዳይለያዩ ያጣመሩ፣ እንዳይፈርሱ ያማገሩ በርካታና ጠንካራ ማጎች በሀገራችን ሁሉም ጫፎች በክብር እና በፍቅር እዚም እዚያም አሉ። ህዝቦቻችን በጋብቻ ተዛምደው፣ በማንነት ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው። ልክ እንደ ምስራቁ፣ ደቡቡና ምእራቡ ህዝባችን ሁሉ የሰሜን የሃገራቸን ህዝቦችም በባህል፣ በቋንቋ፣ በዘር፤ በሃይማኖት ወዘተ ተሰናስልው፤ ተዋደውና ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ስለመሆናቸው በርካታ የታሪክ፣ የባህል፤ የእምነት እና የቋንቋ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚያስፈልገው ሁነት ሳይሆን በህይወታቸው ውስጥ ከተረበረቡ እልፍ መገለጫዎቻቸው የሚስተዋል ግሩም እውነት ነው። የዚህ አንድነትና የጋራ ማንነት- … [Read more...] about አሸንዳ/ሻደይ ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኤርትራ የሚከበር “የጋራ ጸጋና ህዝባዊ በረከት እንጂ የምንጣላበት፣ እንደ አላቂ ሃብት በድርሻ-ድርሻ የምንካፈለው አይደለም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ
የመንጋ ፖለቲካ እና የመንጋ ፍትሕ የትም ሃገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። ተከስቶም ያውቃል። የዘርፉ ባለሙያዎች ዋነኛ ምክንያቱ "በተቋማት እና በመንግሥት የተቆጣ ሕዝብ፣ ከምሬት እና ከቁጭት የተነሳ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ በሥሜት የሚወስደው በቀል አዘል "የፍትሕ ጥያቄ" ነው" ይሉታል። በዚያ መልኩ ስንረዳው መፍትሔው ቀላል ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንጋ ፖለቲካውን እና የመንጋ ፍትሕን በዋነኛነት በሕዝብን ይሁኝታ (ለመልካም እሴት በመገዛት) እና የጸጥታ ኃይሉ በሚወስደው እርምጃ ብቻ ለመቆጣጠር ማሰባቸው ግን ሙሉ አይመስለኝም። ነፃነትል መሸከም አለመቻል አድርጎ መሳላቸውም አልተመቸኝም። ብዙ ትክክለኛ ጥያቄዎች "በመንጋው" ተነስተዋልና። ይልቁንስ ሕዝቡ በለውጡ ላይ ከፍተኛ ተስፋን በመጣሉ ዝቅተኛው ካድሬ እና የአስተዳደር አካል ሕዝቡ የሚፈልገውን ለማድረግ አለመቻሉ ነው። … [Read more...] about የመንጋ ፍትሕ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ
“እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
ትውስታችሁን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ካሁን በፊት እኔ የጻፍኳቸው፤ ጃዋር የተናገራቸውን ነጥቦች ላስታውሳችሁ። “ኦሮሞዎች ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ አገባድደውታል” ጌታቸው ረዳ (3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ- 2015) “በማሃይም አዝማሪዎች እና በደደብ ምሁራን ጭንቅላት እየተመራችሁ የምታሽቃብጡ ኢትዮጵያውያን ሁላ የኦነግ እና የሻዕቢያ ባንዴራ ይዛችሁ መዝለል እና ማሽቃበጣችሁን ተው” (ጌታቸው ረዳ “የግንቦት 7 ጀሌዎች የኦነግና የሻዕያ ባንዴራ ማውለብልብ ብርቅ ሆኖባቸዋል- 2015) አሁን ደግሞ ጃዋርን ላስታውሳችሁ፡ “ኦሮሚያ በአፍሪካ ውስጥ እንደ ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ብሔሮች የሚኖሩባት አካባቢ የለም። ምናልባት ጆሃንስ በርግ በስተቀር። ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ‘ብሔር’ ‘ብሄረሰብ’ የለም።ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about “እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት
የምናውቀውን አብይ እንፈልጋለን!
“ህልም በሥራ ብዛት ይታያል። እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል” “ብዙ ህልም ባለበት ዘንድ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ።” መፅሀፈ መክብብ ምዕ 5 ቁጥር 3 እና 7 አስቀድሞ ቃል ተነገረ፤ ቃሉም የአብይ ነበረ፤ ቃሉም ኢትዮጵያዊነትን ከወደቀበት ማንሳት ነበረ፤ ቃሉም በእኛ ዘንድ ህያው ሆነ፤ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን ከመሪዋ ጎን ቆመን ከፍ አደረግን፤ ከአፅናፍ አፅናፍ ሆ! ብለን ተነሳን፤ በያደባባዩ ተመምን፤ መሪያችንን አብይን እንደ ጨው በተበተንባት ምድር ሁሉ ስሙን ጠራን፤ እነሆ ኢትዮጵያ መሪዋን ሙሴን አገኘች ስንል ብሥራት ተናገርን፤ እርሱም አላሳፈረንም፤ ሙሴነቱን እጃችንን ይዞን አቅፎንና ስሞን እንባችንንም አብሶና ደሙንም ለግሶን አልቅሶና አንሰቅስቆን ከሰቆቃና ከግርፋት ከእስርና ከስደት ነፃ አውጥቶን ወደ ነገይቷ ኢትዮጵያ … [Read more...] about የምናውቀውን አብይ እንፈልጋለን!
An afternoon with a quiet revolutionary
I spent a Saturday afternoon in Los Angeles attending a “Thank You” tour by my hero Andargachew Tsige upon his release from TPLF Woyane Gulag. To remind you how he became a prisoner - he was abducted in broad daylight from an International airport by Woyane security in collaboration with Yemen. It is a brazen act that broke many laws and conventions and it can only be carried by a regime that believes it was answerable to no one. It took its lawlessness into the international arena. It is not … [Read more...] about An afternoon with a quiet revolutionary
ለምንገነባው የፍቅር ድልድይ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ
ሰው ማሰቡን የሚያቆመው ሲሞት ብቻ ነውና ሃሰቡን ለመሰሎቹ በማካፈሉ የሚወገዝበት ዘመን ማክተሙን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሥትራችን፣ ዶ/ር አብይ አህመድ ከቃል በላይ በተግባር ዕውን እነዲሆን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደሚሰሩ በማረጋገጣቸው በእጅጉ ተደስቻለሁ። "ለምን ታስባለህ? ሃሰብህንስ ለምን ታካፍላለህ ?" በማለት የሚገድበው ሳይኖር" ህዝብን ታነቃለህ፣ የግለሰብን ህሊና በማንቃትና የግንዛቤ እጥረቱንም በመቅረፍ፣ በድምርም ህዝብ እንከኔን እንዲያይ በማደረግ ህግ እና ህገመንግስት እኔ ራሴ ሆኜ ሳለ፣ ህገመንግስቱን ጥሰሃል፣ በሥልጣንም ያለአግባብ ባልገሃል፣ በማሰኘት እንደጠላ ታደርጋለህ። ... አንተ እኔ ህዝብን እንዳሻው እየመራው የምሰራው ሥራ የማይታይህ ፀረ-ልማትና ፀረ-ህዝብ ነህ፣ ፀረ ህገመንግስት ነህ፣ ወዘተ። በማለት ሰዎች በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው እነዳይጠቀሙ … [Read more...] about ለምንገነባው የፍቅር ድልድይ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ










