በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ ይከለላሉ ይባል ነበር፤ አሁንም ያው ይመስላል! ያነበብሁትን በትክክል ካስታወስሁት በጥንታውያን ግሪኮች ሰርቀው መያዝ እንጂ መስረቅ ወንጀል አልነበረም (የምታስታውሱ አርሙት)፤ የምንመሳሰለው በጥንታዊነት ብቻ መስሎኝ ነበር! ከዚህ ቀደም ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ይመስለኛል) ተረግመናል ብሎ፤ ነበር፤ እኔንም መሰለኝ! ኢትዮጵያውያን መልካቸውን፣ ነብሮች ቆዳቸውን እንዴት ይለውጣሉ ያለው መልካችንን ነበር፣ ወይስ ጠባያችንን ማለቱ ነበር! ነገሬ ሁሉ የጥንቶቹን አባትና እናት … [Read more...] about መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
prof mesfin
የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!
ከ27 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ የተገኙት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ ዶ/ር ዐቢይ የዕለቱን የመወያያ አጀንዳ ከገለጹ በኋላ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች አሳባቸው እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው፤ የኔታ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የገቡት። ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ በአዳራሽ ውስጥ የነበሩ ተሰብሳቢዎች የኔታ የመቀመጫ ወንበራቸውን እስኪይዙ ድረስ የተሰብሳቢው ዓይን በፍቅርና በአክብሮት እሳቸው ላይ ነበር ያረፈው። የተጀመረው ውይይት በተሰብሳቢዎች በሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት ቀጥሎ ለሻይ ዕረፍት ስብሰባው ተቋረጠ። ሁላችንም ሻይ እና ቡና ወደተዘጋጀበት ቦታ አመራን፤ ዶ/ር ዐቢይ ለሻይ በወጣንበት ወቅት የቱ ጋር እንዳሉ እኔ ልብ አላልኩም፤ ይልቁንም ለየኔታ ትኩስ ነገር ምን ላምጣሎት ብዬ ስጠይቃቸው፤ “አንድ ሲኒ ቡና ትንሽ ስኳር ጨምረ አመጣልኝ፣ ከዚያ … [Read more...] about የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!


