እንደ መግቢያ ሰሞኑንን ከኮቪድ - 19 ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሓኖም አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ከሚያራምደው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር ካደረገ፣ በጅምላ ሴቶች እንዲደፈሩና ከነነፍሳቸው ለአውሬ እንዲጣሉ ካደረገ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ትህነግ ቴድሮስ የተቀዳ አመራር እንደነበር አይዘነጋም። የተመረጠው በኃያላኑ ዓላማና መልካም ፈቃድ ነበር፤ ኃያላኑ አሁን ፍጥጫ በሚመስል ውዝግብ ውስጥ ይገኛሉ፤ የተመረጠበትን ዓላማ የፈጸመ ከሆነ መወገዱ የማይቀር ይሆናል፤ ካላለቀ ደግሞ ዕድሜ ማራዘሚያ ይሰጠዋል። የቴድሮስ የWHO ምርጫ ወቅቱ የዛሬ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር … [Read more...] about የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
Politics
አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል!
ስለ ዓድዋ ጦርነት አንዳንድ እውነታዎች❗️ ቀን: የካቲት 23, 1888 ቦታ: አድዋ፤ ኢትዮጵያ አሸናፊው ሀይል: ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች አጤ ምኒልክ እቴጌ ጣይቱ ተክለ ሀይማኖት ራስ መኮንን ራስ ሚካኤል ራስ መንገሻ ፊታውራሪ ገበየሁ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ፊታውራሪ ዳምጠው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ኒኮላ ሊዮንቴቭ በጣልያን በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች ኦሬስቴ ባራቴሪ ቪቶሪዮ ዳቦርሚዳ ጁሴፔ አሪሞንዲ ማቲዎ አልቤርቶኒ ጁሴፔ ኤሊና በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት 80,0000 መሳርያ የታጠቅ 20,000 ጦርና ጎራዴ የታጠቀ 8,600 ፈረሰኛ በጣልያን በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት 24,804 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቅ ወታደር 56 ረጅም ርቀት ተወርዋሪ መሳርያዎች በኢትዮጵያ በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር … [Read more...] about አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል!
የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል
ኦነግ አወዛጋቢ ማንነቱና ያልረጋ የፖለቲካ ሩጫው ዛሬም መነጋገሪያ ሆኗል። ቀደም ሲል ለኦሮሞ ትግል እንደ አንድ ብቸኛና ልዩ ምልክት ተደርጎ የተወሰደው ኦነግ በአራት ጎራ ተከፍሎ ቢቆይም አገር ቤት ከገባ በኋላ አንድ መሆን አልቻለም። በኤርትራ በረሃ እያለ እርስበርስ ጎራ ለይቶ በጥይት የተጫረሰው ኦነግ፣ በአውሮፓና በአሜሪካ ባሉ የተለያዩ አመራሮቹ የስልጣን ሽኩቻ አንድ መሆን አቅቶት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት አስቆጥሮ አሁን አገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ ሁሉም አካላት ወደ አገር ቤት ቢገቡም ልዩነታቸውን ማስወገድ አልቻሉም። ዳውድ ኢብሣ (ፍሬው ማሾ)፣ አባ ነጋ፣ ገላሳ ዲልቦና ጄኔራል ከማል ገልቹ የተቀራመቱት ኦነግ አራት መልክ ይዞ ወደ አገር ቤት ሲገባ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳው “ለምን አንድ አትሆኑም? አንድ ሁኑና ኑ” የሚል ነበር። እነዚህ አራት ክንፎች እንኳን … [Read more...] about የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል
በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች
በቡራዩ የተከሰተውን ረብሻ አስመልክቶ ቢቢሲና የመንግሥት ሚዲያዎች የተሟላ መረጃ አለማቅረባቸውን የቡራዩ ነዋሪዎች ለጎልጉል ገለጹ። እነሱ እንዳሉት በአንድ መጠነኛ ሆቴል ምረቃ ላይ ለተነሳው ጸብ መነሻው በሽብር ተግባሩ የሚታወቀውና ጃል ማሮ (ኩምሣ ድርባ) የሚባለው የኦነግ ሸኔ ሽፍታ መሪ ፎቶ በጨረታ እንዲሸጥ መቀረቡን ተከትሎ ነው። ነዋሪዎቹ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሲያስረዱ በምረቃው ላይ ጃል ማሮን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች በዝተው ነበር። የውዳሴው ሙዚቃ መብዛቱ ከቡራዩና አካባቢው ወይም በተለምዶ የ“ሸዋ” የሚባሉትን ኦሮሞዎች አላስደሰተም። ሙዚቃው ቅይጥ እንዲሆን ቢጠየቅም ሰሚ አልነበረም። “በዚህ ስሜት ውስጥ እያሉ ነው ጃል መሮ የሚባለው የኦነግ ሸኔ ሽፍታ መሪ ምስል ለጨረታ የቀረበው” ሲሉ በስፍራው የነበሩ ምስክሮች ያረጋግጣሉ። አክለውም “የዚህን ጊዜ ንትርክ ተነሳ። … [Read more...] about በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች
“ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
“በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ” አለበት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተወሰዱ እና ሊወሰዱ ይገባቸዋል ስላላቸው እርምጃዎች የካቲት 5፣ 2012 መግለጫ አውጥቷል። በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ እንዳለበት የገለጸው መግለጫ ለሀገሪቱ ደህንነትና ለህዝቡ ህልውና ሲባል ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን እንደማይታገስ አቋም መያዙን ይፋ አድርጓል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ መግለጫ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱን የማጠናከርና የህግ የበላይነትን የማክበርና የማስከበር ተግባሩን … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
“እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ? የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል። የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል። በመሰዳደብ፣ ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል። ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል። የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦ "ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።" "አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች … [Read more...] about “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ
ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል” ታዬ “ዲቃላ” በጃዋር ስሌት ዋስትና የሌላቸው ኦሮሞዎች “በዐቢይ ላይ ቁርዓን ይዤ ጅማ እዘምታለሁ” ጃዋር ጃዋር በሁለት ጠርዝ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየበረረ መሆኑንን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ናቸው። በገሃድ እንደታየው ቤተመንግሥት ለመግባት የተጫኑለትን ስሞች በሙሉ አራግፎ ፖለቲከኛ ሆኗል። ወደ ሥልጣን በሚያደርገው ጉዞ ዋንኛው ዓላማ የተደረገው አማራን ማበጣበጥ ነው። ለዚህም ምኞቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማና በመላው ኦሮሚያ እንዲጠሉ ቁርዓን ይዞ ዘመቻ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ ደግሞ በጃዋር ጉዳይ መለሳለስ አሳይቷል እየተባለ የሚተቸው መንግሥት የተከማቸውን ፋይል ሊገልጥ ጫፍ መዳረሱን የሚያሳዩ ፍንጮችም ገሃድ እየወጡ ነው። በሌላ በኩል “ዲቃላ” በሚል ጃዋር የሚጠራቸው ኦሮሞዎች ዋስትናቸውን … [Read more...] about ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
https://www.youtube.com/watch?v=NIvQXi8NwPo&feature=youtu.be&fbclid=IwAR13D7r_vtAWnyoTUm8e_yaHBwF_-QBrSVp7wJhB0-ezVQNHVrUZFPXecR8 … [Read more...] about “ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህወሓት መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤ እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው። ደብረፅዮን ወደ ህወሓት የተቀላቀለው በመጨረሻው 1974 ዓም አካባቢ ነው። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታዬ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!! የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋን መምራት ይችላል ወይ? ነው፤የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲልም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታለች፤ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ አባይ … [Read more...] about ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
አምስተኛ ቀኑን ያሳለፈው የሕንጣሎ ወረዳ ተቃውሞ ቀጥሏል
የክልሉ መንግስት ምላሽ ቢጠየቅም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ትላንት አምስተኛ ቀኑ አልፏል በትግራይ ክልል የሕንጣሎ ወረዳ ነዋሪዎች በአዲሱ የአስተዳደር መዋቅር ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን ተቃውመዋል። “በአቅራቢያችን መተዳደር እንፈልጋለን” በማለትም ከመቀሌ ከተማ ወደሳምረ በሚወስደው ደንጎላት በሚባል አካባቢ መንገድ ዘግተው የክልሉ መንግስትን ምላሽ በመጠባበቅ አራተኛ ቀናቸውን ደፍነዋል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ የ“ወረዳችን ይመለስልን” ጥያቄ በማቅረብ ከህብረተሰቡ በተወከሉ ነዋሪዎች አማካኝነት ላለፉት ስድስት ወራት ያክል ወደክልል አስተዳደር ተመላልሰው ቢጠይቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪ አቶ መሀሪ ገብረ፤ “ህብረተሰቡ ሌላ ሃሳብ የለውም፣ ዓላማው ወደክልሉ ቢሮ … [Read more...] about አምስተኛ ቀኑን ያሳለፈው የሕንጣሎ ወረዳ ተቃውሞ ቀጥሏል










