• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው)

March 2, 2020 11:12 am by Editor 1 Comment

በፈረስ ስማቸው ጎራው በመባል ይታወቃሉ፣ ከአድዋ በፊት ከኢጣሊያ ጋር በተደረጉ የአምባላጌ እና የመቀሌ ጦርነት ላይ በጀግንነት የተዋጉ የጦር መሪም ናቸው ፊታውራሪ ገበየሁ!

በአምባላጌ ጦርነት ወቅት ጎራው ገበየሁ የጠላትን የጦር ሰፈር እንዲቃኙ በተላኩበት ጦርነቱን አስጀምረው በዚያ መሽጎ የነበረውን የኢጣሊያ ጦር ድል አደርገዋል ለዚህም፥

“ያ ጎራው ገበየሁ

አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው፤

ለምሳም ሳይደርሱ ለቁርስ አደረጋቸው።” ተብሎ ተገጥሞላቸዋል።

ምንም እንኳን የአምባላጌው ድሉ የኢትዮጵያ ቢሆንም ፊታውራሪ ገበየሁ ግን ገና ያልታዘዘ ጦርነት ነው ያስጀመሩት ተብለው እንዲታሰሩ ተወሰነባቸው። እርሳቸውም “ጀግና የጦር መሪ የምኒልክ አብሮ አደግ ነኝ እንዴት ይሆናል” ሳይሉ ፍርዱን ተቀብለው በሰንሰለት ታሰሩ። በኋላ ላይም በመቀሌው ጦርነት ወቅት ተፈትተው በጀግንነት ተሳተፉ።

በመጨረሻም በአድዋ ላይ በአምባ ኪዳነምሕረት በኩል የኢጣሊያ ጦር ጥቃት በጨመረ ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማፈገፈግ ሲጀምር ፊታውራሪ ገበየሁ “እንዴት ትሸሻላችሁ እንዴት እንደምሞት ሂዱና ለንጉሥ ተናገሩ” ብለው መድፍና ጥይት በሚዘንብበት መሐል ተወርውረው ገቡ። ሲያፈገፍግ የነበረው ሌላው ሠራዊትም እርሳቸውን እያየ ተከትሏቸው ወደ ጦሩ ገባ፤ ጎራው ገበየሁ ግን በመትረየስ ተመትተው ወደቁ ሕይወታቸውም በዚያ አለፈ። ከሰባት ዓመት በኋላም በቃላቸው መሠረት አጽማቸው በትውልድ መንደራቸው አንጎለላ እንዲያርፍ ተደረገ።

ምንጭ፤ መንዝ ጌራ የመገናኛ ጽ/ቤት

ፊታዉራሪ ገበየሁ ማናቸው ? ያልተነገረው ታሪካቸው ምንድነው ?

ፊታዉራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራዉ) በነሐሴ 12.1836 አ.ም በሸዋ ክፍለ ሃገር በተጉለትና ቡልጋ አዉራጃ አንጎለላ ልዩ ስሙ *አስታ ቆላ ጌጠር* በምትባል ስፍራ ተወለዱ። ክርስትናም የተነሱት በፅርሀ አርያም አንጎለላ ኪዳነ ምህረት ነዉ። ፊታዉራሪ ገበየሁ ዉልተታቸዉምም እድገታቸዉም ብሎም የእምዬ ምኒልክ የጦር ሚንስተር እስከመሆን የበቁት እዚሁ አንጎለላ ነዉ።እኚህን ጀግና ስናስታዉስ ኢትዮጵያዊነት ምን ያክል እረቂቅ መሆኑን እንረዳለን ፊታዉራሪ ስለሀገራቸዉ ደማቸዉን የገበሩ ጀግና የጦር አበጋዝ እንደነበሩ ታሪክ ይነግረናል። የንጉሰ ነገስቱ የመሀል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረገው በሁሉም ጦርነት የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ፡፡ የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር በጣሊያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደውል ያሰሙት እና ዋናው የድሉ ባለቤት እሳቸው ነበሩ

በዚህም ምክንያት በወቅቱ የፈረንሳይ ጋዜጦች “የአምባላጌው የኢትዮጵያ ጀግና” በማለት እንዳወደሷቸው ተክለፃዲቅ መኩሪያ ፅፈዋል፡፡ የመቀሌውንም ጦርነት በደንብ ተካፍለው በጀግንነት ሲዋጉ እጃቸውን የቆሰሉ ሲሆን ፣ ከጦርነቱ በፊትም ራስ መኮንን ስለ እርቅ ጉዳይ በሚነጋገሩበት ጊዜ ገበየሁ እየተዋጉ ስላስቸገሩ እንደ አምባላጌው እንዳይዋጉ አስረዋቸው ሳለ በኋላ ግን ላይዋጉ አስምለው አስለቀቋቸው፡፡ በኋላም ጦርነቱ ሲጀመር የአምባላጌ የገፈቱ ድል ቀማሽ ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራ ነበር።

በእለቱ ታሞ ስለነበር ዱላ እየተመረኮዘ ነው ገደሉን የወጣው፤ ግና ይህ ሁኔታው ድልን ከመቀዳጀት አልከለከለውም። ስሙን ትንሹም ትልቁም ወዲያው አወቀው እና ገጣሚም እንዲህ ሲል አሞገሰው፦

የንጉሥ ፊታውራሪ ያ ጎራው ገበየሁ አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው

ለምሳም ሳይደርሱ ቁርሥ አደረጋቸው  

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ የአድዋ ድል ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በጦርነቱ ላይ የተሳተፉ ጀግኖች ኢትዮጵያውያንም እንዲሁ፡፡ የአደዋ ጦርነት የተጀመረው በየካቲት 23 ቀን 1888ዓ.ም ከማለዳው ነበር፡፡ ውጊያው ከጠዋቱ 11፡30 ላይ በአራት ጄኔራሎች የሚመራው የጠላት ጦር በፊታውራሪ ገበየሁ ፣ በዋግሹም ጓንጉል ፣ በራስ ሚካኤል እና በራስ መንገሻ ጦር ላይ በሰነዘረው ጥቃት ተከፈተ፡፡

ፊታውራሪ ገበየሁ በዚህ ጦርነት ፊት ለፊት የገጠሙት በእንዳ ኪዳነ ምህረት በኩል የመጣውን እና በጄኔራል አልበርቶኒ የሚመራውን የጠላት ጦር ነበር፡፡ በጦርነቱ ፊታውራሪ ገበየሁ ከሰራዊቶቻቸው በመለየት ጎራዴያቸውን መዘው በዋናው የትግል አውድማ ፣ በተፋፋመ እና በቀለጠው ውጊያ ላይ ተወርውረው ገቡ፡፡ ዘለው እንደገቡም ከጀግናው ጓደኛቸው ከቀኝ አዝማች ታፈሰ ጋር እየፎከሩ የጠላትን አንገት በጎራዴ ሲቆርጡ እና ሲገነድሱ ቆይተው ከርቀት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ወደቁ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ስለ ፊታውራሪ ገበየሁ አዲስ አበባ ድረስ ተማርኮ መጥቶ የነበረው የኢጣልያ መኰንን ፣ጆቫኒ ቴዶኒ የጻፈው ማስታወሻ እንዲህ ይላል….. “በቢያን ኪኒና በማዘቶ ለሚመሩት መድፎች እየተመቱ አበሾች ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ አይቶ “ፈሪ እንዴት ትሸሻላችሁ? እኔ እንዴት እንደምሞት ለንጉሱ ሄዳችሁ ንገሩ” በማለት ፈረሱን በአለንጋ አስነስቶ በግልቢያ በሚዘንበው የመድፍ ጥይት መካከል ገባ፡፡

 እንዲያውም በተክለ ፃዲቅ መኩሪያ መፀሃፍ ላይ እንደተከተበው ፦ “ጦርነቱም አጅግ በበረታ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦረኞች ወደ ሇላ እንደማፈግፈግ ሲል ቀይ የክብር ልብስ የለበሰዉ ፊታዉራሪ ገበየሁ “ወደ ሸዋ በህይወት የተመለሰ አሟሟቴን ይናገር” ብሎ ዘሎ ወደ ተፋፋመዉ ዉጊያ ገባ በዚያም እየተዋጋ ሳለ ተመትቶ ወደቀ የጣልያንም ወተደሮች አብረዉ ወድቀዉ ሬሳዉን አከበሩት ድሉም ለኢትዮጵያ ሆነ።” እሱን ሲያይ ሁሉም እየሮጠ ተከታትሎ ገብቶ ከመድፈኞቹ ጋር ተጨፋጭፎና ገድሎ መድፈኞችን ማረከ፡፡ የገበየሁ ሬሳ ከወደቀበት ቦታ የእኛዎቹ ጀግኖች አብረው በመውደቅ የእርሱን ሬሳ አከበሩት” በማለት ገልጾታል፡፡

ፊታውራሪ ገበየሁ ገና ወደ አድዋ ሲዘምቱ ተናዘውም ነበር “ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፣ እኔ እንደ አባቶቼ አይደለሁምና ወግ አይገባኝም፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን እሬሳዬን /አፅሜን/ ትውልድ ቦታዬ ውሰዱልኝ” አሉ፡፡ እንደተባለውም ሆነ በፅኑ ሲፋለሙ ስለ ሀገራቸው ነፃነት አደዋ ላይ ወደቁ፡፡ በሕይወት እያሉ:-“የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው” የተባለላቸው ገበየሁ(በአካባቢው አጠራር ጎራው ገበየሁ)፤ አድዋ ሥላሴ ተቀብረው ከቆዩ በኋላ አፅማቸው ወደ አምባላጌ ጊዮርጊስ ተወሰደ፡፡ በቃል ኪዳናቸው መሠረት ከሰባት ዓመት በኋላም አፅሙ በትውልድ አካባቢያቸው በአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አረፈ፡፡

ከአድዋ ድል በኋላ በጃንሜዳ የጦር አበጋዞች በፈረስ ሲያልፉ የፊታውራሪ ገበየሁ ፈረስ ብቻውን ከፊት ሲያልፍ ያዩት አፄ ምኒልክ ተንሰቅስቀው እንዳለቀሱም ይነገራል፡፡ ፊታዉራሪ ገበየሁ ነፍሱን ሰጥቶ ሀገሩን በታላቅ ተጋድሎ ያከበራት ጀግና ነዉ።ይህ ጀግና የሰራዉን ገድል ያክል አልተዘመረለትም በስሙም የተሰየመ ቤተ መዘክር እንኳን የለም የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን ያስከበሩንን ጀግኖቻችንን እናክብር። የገበየሁ እንጉርጉሮ የሚለውን መነባንብ ለማድመጥ ይሄንን ሊንክ ይጫኑና ያድምጡ።

ምንጭ፡ ዕውቀት

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Left Column, Social Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. gi haile says

    March 2, 2020 06:40 pm at 6:40 pm

    ይህ የታሪክ መዛባት ነው የሚያሳዝነን። ሁሉንም ጠቅለል አድርጎ የሚፅፍ ታሪክ በለመኖሩ የሁሉም ርብርብ ዐፄ ምንሊክ ላይ ሆነ የዛሬው የእርስበርስ መቃቃር ምንጩ የታሪክ መዛባት ነው። የኢትዮጵያ ታሪክ ፀሓፊዎች ሊያስቡበት የሚገባ ትልቅ ኃላፊነት ነዉ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule