አቶ ዠ ከጸሃፌ-መፈክር ወደ ጸሃፌ-ተውኔት እሸጋግራለሁ ብለው መፈከራቸው እንዳለ ሆኖ፣ ይንን አስመልክቶም ለኢሃዴግ ፍቅር ቴአትር ቤት ሥራ አስቀማጭ ደብዳቤ መላካቸው እንዳለ ሆኖ፣ ... ከወራት በኋላ የአቶ ዠ ባለቤት ወይዘሮ ዘ ቡና አፍልተው ከአቦል እስከ በረካ ተጠጥቶ እንዳለቀና ሥኒ እያጠቡ እያለ... ወይዘሮ ዘ ገረሙህ?“ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል” ሲባል አልሰማህም?ባላቸው ዠ ከሆኑ እሳቸው ከ ዘ ሌላ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?ዠ እኮ ባርኔጣ የደፋ ዘ ነው።ከምሬ ነው። ካላመንከኝ ሥለ ቃላትና ፊደላት የሚፈላሰፉ “ዲባቶ”ዎች ፈልግና ጠይቅ። ሥምህ ጨ ከሆነ የምታጫትና የምታገባት ኮረዳ ጠ ነው የምትባለው። እና ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ፣ አቶ ዠ ከባለቤታቸ ጋር “ጨዋታ” ጀመሩ። “ጨዋታ“ው ሲያልቅ ጻፉት፣ አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት። ገጸ-ባህርያት ዠ እና ዘ ብለው ጀመሩ። ዘ … [Read more...] about አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት
Right Column - Primary Sidebar
እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!
ቀኑ፡ እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓም/February 14, 2016 ሰዓቱ፡ 1:00 - 5:00 PM ቦታ፡ Sheraton Silver Spring Hotel 8777 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20910 ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓ.ም./ February 14, 2016 ከ1:00 - 5:00 PM በሚያደርገው የእኛ ለእኛ ሕዝባዊ ውይይት ላይ እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ዋናው የትኩረት ሃሳብ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ግፍ፣ እስር፣ ግድያ፣ እንዲሁም የአየር መዛባትና አስተዳደራዊ ብልሹነትን ተከትሎ የተከሰተው ችጋር፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየጨመረ የመጣውን ሕዝባዊ ዓመጽ ወዴት አቅጣጫ ሊወስደን ይችላል? የሚል ሲሆን ከዚህ አንጻር በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ ወራት፣ … የሚከሰተው ነገር የኢትዮጵያን … [Read more...] about እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!
የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች
ክፍሉ ከኮሪደሩ ላይ ከተንጠለጠለ አምፖል በሚመጣ ብርሃን ፈገግ ብሏል፡፡ እኔም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ወደ ክፍሉ ስገባ ከክፍሉ አንደኛው ጫፍ ላይ አንድ ቀጠን ያለ ሰው ድምፁን በትንሹ ከፍ አድርጎ ቁርዓን ‹እየቀራ› ነበር፡፡ በክፍሉ ሌላኛው ጫፍ ላይ ደግሞ አንድ ፍራሽ፣ አንድ የውሃ ጀሪካን እና ትንሽ ልብሶች በፌስታል ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡ በሌላኛው የክፍሉ ጫፍ ደግሞ የሽንት ባልዲ - ሽታውን ለመቀነስ ሲባል በግማሽ ውሃ ተሞልቶ ተቀምጧል፡፡ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁ አንዱ ጫፍ ላይ ትንሽ ቆም ካልኩ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ያገኝሁት ብቸኛው ሰው ፍራሹ ላይ እንድቀመጥ በእጁ ሲጠቁመኝ ቁጭ አልኩ፡፡ ፍራሽ ላይ እንደተቀመጥኩ በፍራሹ ጫፍ ላይ የጆን ግሪሻም ‘The Last Juror’ መፅሃፍ ተቀምጦ አየሁት፤ አንስቼ ስመለከተው ክፍሉ ውስጥ ያገኘሁት ሰው ቁርዓን መቅራቱን ጨርሶ እንግሊዝኛ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሙስሊም ፈተና በ224 ደቂቃዎች
ከሰርቢያው ነውጥ አልባ ትግል ውጤታማነት ኢትዮጵያችን ምን ትማራለች?
ከክሮሺያ እና ከቦስኒያ ጋር በሁለት ጦርነቶች ተሸንፎ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያደቀቀው የሚሎሶቪች መንግስት በህዝቡ ዘንድ ይሁንታን ባጣበት ሁኔታ ላይ እያለ እ.አ.አ በ1996 ዓ.ም በተካሄደው የክልል ከተሞች ምርጫ በስርቢያ አጠራር ዛየኖ ወይም ቱጌዘር የተሰኘው ፓርቲ በ40 የክልል ከተሞች ውስጥ ማሸነፍ ችሎ ነበር። ሚሎሶቪች ግን ለምርጫ ቦርዳቸው ውጤቱን እንዳያጸድቅ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ። በዚህም ሳቢያ ተማሪዎች ለ55 ቀናት እለት በእለት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ተቃውሞ የመንግስት ተወካይ ከተማሪዎች ተወካይ ጋር ባደረጉት ስምምነት ለዛየኖ ወይም ቱጌዘር ለተባለው ፓርቲ በማን አለብኝነት ተነፍጎ የነበረውን 40 መቀመጫዎች መልሶ ማግኘት ቻለ። በተገኘው ድል መጠነኛ የስነልቦና ጥንካሬን ያገኙት እኚሁ ሰልፈኛ ተማሪዎች ለሚሎሶቪች ውድቀት ዋና ተዋናይ ለሆነው ኦትፖር ለተሰኘው ድርጅት … [Read more...] about ከሰርቢያው ነውጥ አልባ ትግል ውጤታማነት ኢትዮጵያችን ምን ትማራለች?
ጥምቀትና ጎንደር Vs የትዝብት ወግ
“ጥምቀትን በጎንደር መታደም መባረክ ነው” ይህ የብዙሃኑ የእምነቱ ተከታዮች የምስክርነት ቃል ነው፡፡ ጥምቀትና ጎንደር የገጠሙ እለት እንኳንስ ለጎብኝዎች ለነዋሪዎችም ታይተው አይጠገቡም፡፡ የጎንደር ጥምቀት በዓል ከመላ ኢትዮጵያ አከባበር የሚለይባቸው በሁለት ተያያዥ ምክንያቶች ይመስለኛል፡፡ ከቀድመው የመሳፍንት እና የአፄዉ ስርዓት ጋር በተያያዘ ከተማዋ ለረዥም ዓመታት መናገሻ ከተማ ሆና መቆየቷ፣ በጊዜው የነበረው ኃይማኖታዊ መንግስት በመሆኑ አብዛኛው ነዋሪ ጥብቅ የኦርቶዶክስ ክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከሌላው አካባቢ (ከተማ) በተለየ መልኩ “የአርባ አራቱ ታቦታት” መገኛ መሆኗ የመጀመሪያው ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ምስረታ በኋላ ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ በኩል አራት … [Read more...] about ጥምቀትና ጎንደር Vs የትዝብት ወግ
የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በተለይ በምዕራብ ጎጃም አካባቢ የደነገገው አዲስ የበርበሬ አዋጅ ችግር እያስከተለ መሆኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ አስታውቀዋል፡፡ እንደ እማኝ ዘጋቢው ከሆነ አዋጁ የወጣው በ2002ዓም ሲሆን በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በዚህ ዓመት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ በበርበሬ ላይ ብቻ የተደነገገው አዋጅ ዋና ምክንያቱን በውል ለማወቅ የሚያዳግት ቢሆንም እንደ እማኝ ዘጋቢው አስተያየት በርበሬው ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚላክ በመሆኑ በተለይ የትግራይ ነጋዴዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጥቀም ታስቦ እንደሆነ ከሚሰጡት ግምቶች የላቀው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እማኝ ዘጋቢያችን የላኩልን መረጃ እንዲህ ይነበባል፡- “በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ በፍኖተ ሰላም በሺንዲ … [Read more...] about የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ተቃዋሚው ሕብረት የኢትዮጵያ ፌድራላዊ አንድነት መድረክ፤ በአገሪቱ እየታየ ያለውን ቀውስና ሌሎች ነባር ችግሮች አስመልክቶ አሳስበውኛል፤ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል። “የሕዝቦቻችንን ጥቅሞች ማዕከል ያላደረጉና ሕዝብን ያላሳተፉ በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ እንጠይቃለን።” መድረክ። መድረክ መፍትሔ ያላቸውን ባለ አምስት ነጥብ ደብዳቤ መነሻነት የድርጅቱ ሊቀ መንበር ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ። … [Read more...] about በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
“የናፈቀ ሰዉ በር በሩን የታከተ ሰዉ መስኮቱን ይመለከታል” በዕዉቀቱ ስዩም
ከዓመታት የንባብ ብህትዉና በኃላ በቀጣይ ሳምንት በመጽሃፍ መልኩ ብቅ የሚለዉ በዕዉቀቱ ስዩም፣ በርከት ያሉ ሞጋች ሃሳቦችን በሥነ-ጽሁፋዊ ለዛ እያዋዛ ወደ አደባባይ እንደሚያወጣ ጥርጥር የለዉም፡፡ "ከአሜን ባሻገር" ምን አለ? . . . የመራቂዉን ማንነት መፈተሸ …? ጥልቅ መጠይቅ …? ወይስ ለየት ያለ ፍንገጣ? ... ብቻ ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ በተለይ ጽዮን ተኮር ኃይማኖታዊ ባህልና መስመር ያለፈ ጥብቅ ብሄርተኝነት ስላጎበጣት ኢትዮጵያ "ከአሜን ባሻገር" ብዙ የምትለን ይመስለኛል፡፡ ታሪክን ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት እና ከኃይማኖታዊ ጥብቅና በጸዳ መልኩ ለማየት የሚጥረዉ በዕዉቀቱ፣ ንባብ የፈጠረለት አቅሙን ተጠቅሞ በግሉ ከደረሰበት የታሪክ ምልከታ አኳያ የሚያካፍለን ብዙ ነገር እንደሚኖር እጠብቃለሁ፡፡ ባለመርማሪ ልቦናዉ በዕዉቀቱ፣ የጊዜችን ቋሚ ሽፍቶችን በተመለከተ ሽሙጥን በተሻገረ … [Read more...] about “የናፈቀ ሰዉ በር በሩን የታከተ ሰዉ መስኮቱን ይመለከታል” በዕዉቀቱ ስዩም
የኢትዮጵያ ፈርስ–ት ባለቤትን ይተዋወቁት!
ቤን እባላለሁ። EthiopiaFirst የሚባል ለሕወሓት/ኢሕአዴግ ጭፍን ወገንተኛ ሆኖ የሚሠራ “የሚዲያ” ተቋም አለኝ። EthiopiaFirst የሚለው ያው ደርግ ‘ኢትዮጵያ ትቅደም’ እንዳለው ወይም ናዚዎች ‘ጀርመን ትቅደም’ እንዳሉት ሰው ማባበያ ስያሜ ነው። ኢትዮጵያ ፈርስት እያልኩ የምጠራውን የሚዲያ ተቋምን ተጠቅሜ ኢሕአዴግ የጠላውን ጠልቻለሁ፣ ኢሕአዴግ የወደደውን ወድጃለሁ። ለምሳሌ የዞን፱ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሲታሰሩ “እሰይ! አገር ሊያተራምሱ ሲሉ ተያዙ” እያልኩ፣ እየማልኩ እና እየተገዘትኩ ፕሮግራም ሠርቼ ተመልካች ለማሳሳት ጥሬ ነበር። በዜግነቴ ካናዳዊ ነኝ፤ ቢሆንም ግን ለውጭ ዜጎች የማይሰጠው ዕድል የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወዳጅ ስለሆንኩ ተሰጥቶኝ አንዳንዴ በየወሩ የሚታተም «ኅብረ–ብዕር» የተባለ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጅ ሆኛለሁ። በመጽሔቴ ላይ ‘አብይ ጉዳይ’ የሚባል አምድ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ፈርስ–ት ባለቤትን ይተዋወቁት!










