• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የናፈቀ ሰዉ በር በሩን የታከተ ሰዉ መስኮቱን ይመለከታል” በዕዉቀቱ ስዩም

January 12, 2016 09:27 pm by Editor 2 Comments

ከዓመታት የንባብ ብህትዉና በኃላ በቀጣይ ሳምንት በመጽሃፍ መልኩ ብቅ የሚለዉ በዕዉቀቱ ስዩም፣ በርከት ያሉ ሞጋች ሃሳቦችን በሥነ-ጽሁፋዊ ለዛ እያዋዛ ወደ አደባባይ እንደሚያወጣ ጥርጥር የለዉም፡፡ “ከአሜን ባሻገር” ምን አለ? . . . የመራቂዉን ማንነት መፈተሸ …? ጥልቅ መጠይቅ …? ወይስ ለየት ያለ ፍንገጣ? … ብቻ ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ በተለይ ጽዮን ተኮር ኃይማኖታዊ ባህልና መስመር ያለፈ ጥብቅ ብሄርተኝነት ስላጎበጣት ኢትዮጵያ “ከአሜን ባሻገር” ብዙ የምትለን ይመስለኛል፡፡

ታሪክን ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት እና ከኃይማኖታዊ ጥብቅና በጸዳ መልኩ ለማየት የሚጥረዉ በዕዉቀቱ፣ ንባብ የፈጠረለት አቅሙን ተጠቅሞ በግሉ ከደረሰበት የታሪክ ምልከታ አኳያ የሚያካፍለን ብዙ ነገር እንደሚኖር እጠብቃለሁ፡፡ ባለመርማሪ ልቦናዉ በዕዉቀቱ፣ የጊዜችን ቋሚ ሽፍቶችን በተመለከተ ሽሙጥን በተሻገረ መልኩ መረር ያለ ሂስ እንደሚሰነዝር እሙን ነዉ፡፡ በተለየም የነጻዉ ፕሬስን ቅርቃር በነገስታቱ ዘመን ለአዝማሪዋች ይሰጥ ከነበረዉ ነጻነት አኳያ እያነጻጸረ ትዝብቱን እነደሚያካፍለን ግምቴ ነዉ፡፡ የሃገሪቱን ዳቦ አልባ ልማት፣ እንደ ግዙፍ ፋብሪካ አንድ አይነት ምርት እያመረቱ ስላሉት ዩኒቨርስቲዎቻችን፣ የንፉቅቅ ሚሄደዉን “ዴሞክራሲ” ያችንን በቸልታ የሚያልፋቸዉ አይመስልም፡፡ ማህበራዊ ሞገድ የሚንጠዉን የከተሜ ነዋሪ በሥነ-ጽሁፋዊ ለዛ እያዋዛ በብዕሩ ለስላሳ ኩርኩም የሚያሳርፈዉ በዕዉቀቱ፣ በዚህ ሥራዉም የእሽባይነት (አሜን ባይነት) ዝማሜውን በተመለከተ የሚያነሳችዉ ጭብጦች የመጽኃፉ አንኳር ሃሳብ እንደ ሚሆን ይጠበቃል፡፡

በሎንደን ኦሎምፒክ ከራሞቱ፣ በሰሜን አሜሪካ የሾዉ ጉዞና በብራዉን ዩኒቨርስቲ የፌሎዉሺፕ ምርምር ከፊል ቆይታዉ ከዳያስፖራዉ ማህበረሰብ የታዘባቸዉን ማህበረ-ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ከምዕራባዊያኑ ነባራዊ ክስተቶች ጋር እያዛመደ የሚያወጋን ጉዳይ መኖሩ አይቀርም፡፡

amenየበዕዉቀቱ የፍንገጣ ጽሁፍ ለጽዮን ብሄርተኞች የሚመች አይደለም፡፡ አሰላሳዩ ልጅ ብዕሩን ማንሳት ሲጀመር በድብድብ የጽድቅ በር የሚከፈት ይመስል የኃይማኖት “አርበኛች” ራሳቸዉን ለዱላ ያዘጋጃሉ፡፡ የነገር ጂራፋቸዉ የተፈተለ ነዉና ዘለፋና ስድብ ከአንደበታቸዉ አይጠፋም፡፡ ሃሳብን በሃሳብ መመከት የከሸፈዉ በገዢዎቻችን በኩል ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ጎረምሳ “ኃይማኖተኛች” ጭምር ነዉ፡፡ ንግድና ክህነትን አጣምረዉ የሚጓዙ ምግባረ-ክብሪት የሆኑ ዲያቆናት የዚህ መሰል ድረጊት አራጋቢዎች ናቸዉ፡፡ ነገር በማቀጣጥሉ ረገድ የቤንዚልን ሚና ያስንቃሉ፡፡ ለአንዳንዶቹማ ከክህነት ትምህርቱ ጋር አብሮ የተሰጣቸዉ እስኪመስል ድረስ የነገር አራጋቢነት “ችሎታ”ቸዉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡

ለሁሉም፤ ድብርት ተጫጭኖት ለከረመዉ የኢትዮጲያ ሥነ-ጽሁፍ ገበያ ጥሩ መነቃቃትን የሚፈጥር መጽሃፍ ገበያዉን ለመቀላቀል እያኮበኮበ ያለበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ፡፡ እናም የመታከት ወራት እያለፉ ነዉና አይናችንን ከመስኮቱ ወደ በሩ እናማትር፤ ልትናፈቅ የሚገባት ድርሳን ቀርባለችና፡፡ የቀኑ ሰዉ ይበለን፡፡ “አሜን” እያልን “ከአሜን ባሻገር”ን እንጠብቅ፡፡

ሙሉአለም ገ.መድህን

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Firew Ayenachew says

    January 18, 2016 05:48 pm at 5:48 pm

    I hop will read it.

    Reply
  2. Yikir says

    January 19, 2016 07:01 pm at 7:01 pm

    Nuro tefnegona asro adirgognal ye ferenj doro.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule