በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረውና በደርዘን ለሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው እንቅስቃሴ አሁን ባለው አዲስ ሁኔታ በአጀንዳውም በተሳትፎውም እየሰፋ ሲሄድ እየታዘብን ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በወያኔ/ኢህአዴግ ግፈኛ አገዛዝ በተሰጠው የጭፍጨፋ ምላሽ የተነሳ ንቅናቄው በአጠቃላይ ቁጣን በተላበሰ መልክ ለዴሞክራሲ ወደሚለው ጥያቄ እየተቀየረ ነው፡፡ እንደዚህ በመሆኑም በአንድ በኩል በዚያው በኦሮምያ ክልል ከተማሪዎቹ ባሻገር ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከትግሉ እየተቀላቀሉ ሲሄዱ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ወጣቶች አንድነት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ፍትህና ዴሞክራሲ ለሚለው ለዚህ የጋራ የሆነ አጀንዳ የመንቀሳቀስ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለጋራ አላማ ለጋራ ትግል
Right Column - Primary Sidebar
“አንከፋፈልም!” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
መንግስት ህዝብ ሳያምንበት ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ አደርጋለሁ በማለቱ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደማይከፋፈሉና በአንድነት እንደሚቆሙ በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ፡፡ ተማሪዎቹ ዛሬ ታህሳስ 8/2008 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ለአንድነት እንቆማለን፣ አማራን እንወዳለን፣ ጉራጌን እንወዳለን፣… አንከፋፈልም…..›› ሲሉ ከሌሎች ጋር ግጭት ውስጥ እንደማይገቡና በአንድነት እንደሚቆሙ አሳውቀዋል፡፡ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በተነሳው ሰፊ ተቃውሞ ጭንቀት ውስጥ የገባው መንግስት ተቃውሞው ‹‹የብሄር ግጭት›› እንዳስነሳ በተደጋጋሚ የገለፀ ሲሆን ይህ የመንግስት ክስ ተቃውሞውን ለማኮላሸት የተወጠነ እንደሆነ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መንግስት ተቃውሞውን ለማኮላሸት ያቀረበው ክስ መሆኑን በመግለፅ ለአንድነት … [Read more...] about “አንከፋፈልም!” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
ሳይቃጠል በቅጠል
በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ትግልና እንቅስቃሴ ሲካሄድ ቆይቷል። ከተካሄዱት ትግሎች ውስጥ የአገርን ነጻነት በማስከበሩ ከውጭ ወራሪ ሃይሎች ጋር የተደረገ የነጻነት ትግል የሚያኮራ ውጤት ሲያመጣ በውስጥ አስተዳደር ዙሪያም ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን ባላባታዊ ስርዓት ለመለወጥ የተደረገ ትግል ሙሉ ለሙሉም ባይሆን መለስተኛ ድሎችን አስመዝግቦ አልፏል። ከአርባ ዓመት በፊት በተፈጠረለት አጋጣሚ ለአስራ ሰባት ዓመት በስልጣን ላይ በቆየው፣ በአምባገነኑ የደርግ የገዳዮች ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የተደረገው ህብረብሔራዊ እንቅስቃሴ ከሽፎ በውጭ ሃይሎች የታገዘ አገር አፍራሽ የሆነ ሃይማኖትንና ጎሳን (ብሔርን) ያማከለ ታጣቂ የጎሳ ስብስብ ስልጣኑን ቀምቶ እስከአሁን ለመቆየት ችሏል። ምንም እንኳን ሕብረብሔሩ ትግል በገጠመው ውስጣዊና ውጫዊ … [Read more...] about ሳይቃጠል በቅጠል
“ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” ህወሃት
ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ግምባር ሲገዛ የኖረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች የተከፈተውን የተማሪዎች ሰላማዊ ተቃውሞ “የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ” በማለት በኢትዮጵያ ስም በተሰየመው የቴሌቪዥን ፕሮግራም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በ1997 ምርጫ ሽንፈት ለመቀበል ጥቂት የቀረው ህወሃት ሞት በወሰዳቸው መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ አማካኝነት የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ሥር ይሆናል በማለት በቀጥታ የህወሃት ታዛዥ በማድረግ በ197 ንጹኃን ዜጎች ላይ በአልሞ ተኳሾች ደረትና ግምባራቸውን በማለት እንደገደለ አሁንም “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት በተማሪና ነዋሪዎች ላይ ለመውሰድ ያቀደውን ፍጹም ኢሰብዓዊ እርምጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከህወሃት የጭከና ታሪክ አንጻር የመግለጫው ትርጉም ለመቀጣጫ እንዲሆን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የመግደያው ጊዜ … [Read more...] about “ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ ይወሰዳል” ህወሃት
ኦሮሞው ኢትዮጵያዊ ያነሳውን የትግል ችቦ ሌላው ኢትዮጵያዊም ተቀብሎ ያበራል!
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከዚህች ከአዲስ አበባዋ የመሬት ነጠቃ ጥያቄ በጅጉ ገዝፎ የሄደ ነው። ከፍተኛው ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ህወሃት ይህን ዘረኛ ፖለቲካውን ተሸክሞ አዲስ አበባ ከገባ በሁዋላ በተለይ ኦሮሞንና አማራን ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የተጠቀመው ዘዴ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ከታች እስከ ላይ ያሉትን ባለስልጣናት በአልተማሩና የማስተዳደር ችሎታ በሌላቸው ነገር ግን ታዛዥ ብቻ በሆኑ ሰዎች መሙላት ነበር። ወያኔዎች ይህን ያደረጉበት ምክንያት ህወሃት ይዞት የተነሳው ጥያቄ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የዴሞክራሲ ጥያቄ ባለመሆኑና ዋናው ዓላማው የሆነ የራሱን ክብ ለመጥቀም በመሆኑ እነዚህን ክልሎች አፍኖ የሚይዝለት አስተዳደራዊ መዋቅር ስላስፈለገው ነው። ህወሃት ያሻውን ያደርግ ዘንድ “የራሴ” የሚለውን ክብ ለመጥቀም ይችል ዘንድ በየክልሉ የራሱን መጠቀሚያዎች መፈለግ … [Read more...] about ኦሮሞው ኢትዮጵያዊ ያነሳውን የትግል ችቦ ሌላው ኢትዮጵያዊም ተቀብሎ ያበራል!
ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
ሰማያዊ ፓርቲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በመስጠት፣ መንግስት የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመከታተል ለማጋለጥ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎችን በጋራ ለማካሄድ እንደተስማሙ ምክትል ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ከመድረክ ጋር እንዲሰራ በወሰነው መሰረት ዛሬ ከኦፌኮ ጋር በተደረገው ውይይት በሰማያዊ ፓርቲ በኩል ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጋሻው መርሻና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ … [Read more...] about ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
“እኛ አማራ ነን እንጂ ትግሬ አይደለንም” የወልቃይት ሕዝብ
* “(ችግራችን) ትግሪኛ መናገር፤ ትግሪኛ መጻፍ፤ በትግሪኛ መዝፈን፤ አለብህ የሚል ነው፤ እኛ መሽከርከር አንችልም” የወልቃይት ሕዝብ “እኛ አሁን የምናቀርበው ምንድነው ማንነት ነው፤ አማራነት በማመልከቻ ለማምጣት አይደለም የተነሳነው፤ አማራ ነን፤ ትላንት አማራ ነን፤ ነገ አማራ ነን፤ ለዘላለም አማራ ነን፤ ይኼ አያሳፍረንም፤ እኛ ስንዘፍን፣ ስናለቅስ፣ ስንፎክር፣ ስንሸልል፣ ለቅሶ ስንደርስ፤ ስናመሰግን ለማንኛውም የምንገልጸው በአማርኛ ነው፡፡ ይህ አማርኛችን ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የገኘነው ነው፤ አያሳፍረንም፡፡ “የወልቃይት ሕዝብ አንዲት ጎጆ ተከዜ ተሻግሮ አልቀለሰም፤ ስለዚህ ይህ ምን ማለት ነው፤ የምን ስሜት ነው፤ ሠርጋችንን፤ ሃዘናችንን፤ ደስታችንን የምናወሳውም እንዲሁ ነው፡፡ ለቅሷችንን የሚያውቅ፤ ደስታችንን የሚያውቅ፤ እንጂ በእኛ ላይ አናታችን ላይ መጥቶ አይደለህም፤ … [Read more...] about “እኛ አማራ ነን እንጂ ትግሬ አይደለንም” የወልቃይት ሕዝብ
ወያኔ በራሱ ወጥመድ
ራስን ሳያታልሉ ሌላውን ማታለል አይቻልም፤ ለራስ ካልዋሹ ለሌላ ሰው መዋሸት አይቻልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደቤት እንደሚባለው ዞሮ ዞሮ ማታለልም ሆነ ውሸት ማደሪያ ሲያጡ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፤ ያኔ ፈጣሪና ፍጡር ይፋጠጣሉ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ይቆማል፤ በከመረው ውሸት መጠን ነቀፌታ ተሸክሞ ያቃስታል፡፡ የታወሩት ዓይኖቹ ይከፈቱና ሕይወት ነጠላ አለመሆኑን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ውጣ-ውረድ መኖሩን፣ ጥላቻና ፍቅር፣ ጤንነትና ሕመም፣ ደስታና ሐዘን መፈራረቃቸውን፣ የግለሰብ ሕይወት በሞት ተሸንፎ መሻሩን፣ ገንዘብ የማይገዛው ነገር መኖሩን፣ ገንዘብ በከበደ መጠን ማቅለሉን አለማወቅ፣ ገንዘብ የማይመክተው ጦርና በገንዘብ ሊታጠቀው የማይችል መሣሪያ መኖሩን አለማወቅ፣ የደከመ እንደሚያይልና ያየለ እንደሚደክም፣ ዓለማችን በጣም የተያያዘና የተቆራኘ በመሆኑ አንዱን … [Read more...] about ወያኔ በራሱ ወጥመድ
የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
አቶ ዠ ደብዳቤ ጻፉ። 40 አመት ሙሉ መፈክር ሲጽፉ ኖረው፣ ኖረው፣ ኖረው አሁን አርቲስት ለመሆን የሚያበቃውን ዝግጅት የጨረሱ መስሎ ተሰማቸው። ሰሞኑን ለወጣው ማስታወቂያ “ብቁ ነኝ” ብለው አሰቡ። ይድረሥ፣ ለ“ኢሃዲግ ፍቅር” ቴአትር ቤት “ሥራ አስቀማጭ”፣ ይቅርታ በቀድሞ ሥሙ የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመባል ለሚታወቀው ... ሥራ አስኪያጅ፣ ጉዳዩ፣ በ 23/2/2008 የወጣውን ማስታወቂያ አስመልክቶ፣ ከታች እንደሚታየው፣ የተለያዩ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ “ልማታዊ” ፍላጎትን ሥለመግለጽ። የወጣውን ማስታወቂያ አስታኮ የተለያዩ ልማታዊ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ 40 አመታት ሙሉ ተዘጋጅቻለሁ፣ ብቃት ያለኝም ነኝ። ከዚህ ኪነጥበባዊ ሥራ የሚገኘው ገቢም በከፊል ለታላቁ “ውዳሴ” ግድብ ቦንዳ (ይቅርታ “ቦንድ”) መግዣ እንዲውል ለመስማማት በገዛ ፍላጎቴ እገደዳለሁ። ይቅርታ … [Read more...] about የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
የተቆለፈበት ቁልፍ!
ከዶ/ር ምህረት ደበበ፣ የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት፣ እ.አ በ2005 ዓ.ም የተጻፈ መጽሀፍ፣ 438 ገጽ ትችት! በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፣ የስልጣኔ ተመራማሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያ! ይህን መጽሀፍ አግኝቴ ለማንበብ እድል ያጋጠመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ባለቤቴ ወደ ኢትዮጵያ ሄዳ ስትመለስ ይዛልኝ ከመጣች በኋላ ነው። በዶ/ር ምህረት ደበበ የተጻፉ ሁለት ወፈፍራም መጽሀፎች ሲሆኑ፣ አንደኛው መጽሀፍና በቅርብ የወጣውን የሽፋኑ ሰዕል ደስ ስላለኝ እንደ አጋጣሚ አንስቼ ካገላበጥኩኝ በኋላ፣ እስቲ ብዬ ደግሞ ሌላውን ሳገላብጥ አቀራረቡ ደስ ስላለኝ ሃሳቡን ይበልጥ ለመረዳትና ለመገምገም ሆነ ወይም ለመተቸት እንዲያመቸኝ በሚል በመጀመሪያ ያገላበጥኩትን በመተው ቀደም ብሎ የታተመውን ማንበብ ጀመርኩኝ። እንደ ዕውነቱ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ የሚመጡ በአማርኛ ቁንቋ የተጻፉ መጽሀፎችን … [Read more...] about የተቆለፈበት ቁልፍ!










