• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት

January 29, 2016 08:47 am by Editor 1 Comment

አቶ ዠ ከጸሃፌ-መፈክር ወደ ጸሃፌ-ተውኔት እሸጋግራለሁ ብለው መፈከራቸው እንዳለ ሆኖ፣ ይንን አስመልክቶም ለኢሃዴግ ፍቅር ቴአትር ቤት ሥራ አስቀማጭ ደብዳቤ መላካቸው እንዳለ ሆኖ፣ … ከወራት በኋላ የአቶ ዠ ባለቤት ወይዘሮ ዘ ቡና አፍልተው ከአቦል እስከ በረካ ተጠጥቶ እንዳለቀና ሥኒ እያጠቡ እያለ…

ወይዘሮ ዘ ገረሙህ?“ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል” ሲባል አልሰማህም?ባላቸው ዠ ከሆኑ እሳቸው ከ ዘ ሌላ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?ዠ እኮ ባርኔጣ የደፋ ዘ ነው።ከምሬ ነው። ካላመንከኝ ሥለ ቃላትና ፊደላት የሚፈላሰፉ “ዲባቶ”ዎች ፈልግና ጠይቅ። ሥምህ ጨ ከሆነ የምታጫትና የምታገባት ኮረዳ ጠ ነው የምትባለው። እና ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ፣ አቶ ዠ ከባለቤታቸ ጋር “ጨዋታ” ጀመሩ።

“ጨዋታ“ው ሲያልቅ ጻፉት፣ አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት። ገጸ-ባህርያት ዠ እና ዘ ብለው ጀመሩ።

ዘ     እኔ የምልህ?ጠባብ ብሄርተኝነት ምንድነው?

ዠ    ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ያልሆነ ማለትነው?

ዘ     “ውሃ ሲወቅጡት እምቦጭ አለ” አሉ። ልዩነቱ ምንድነው?

ዠ    ጠባብ ብሄርተኝነትማ ልክ እንደምታጥቢው ሥኒ ማለት ነው።(አሉ አቶ ዠ የሚታጠበውን ሥኒ እያዩ።)

ሥኒ ውስጥ ከጀበና ቡና ብትቀጂበት ያው ያቺኑ የተቀዳችውን ብቻ ነው የሚይዘው። ከዚያ በላይ አይችልም። ጠባብ ነዋ! በተፈጥሮው፣ ባሰራሩ ጠባብ ነዋ!ያ እንግዲህ የጠባብ ብሄርተኝነት ምሳሌ ሊሆን ይችላል።

ዘ     አሃ!(የገባቸው አይመስሉም፣ ወ/ሮ ዘ)

ዠ    ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ደግሞ እንደ ጀበናሽ ነው። የያዘውን ሁሉ የሚያከፋፍል። አየሽ ጀበና ታጋሽና ለጋሽ ነው። እሳት ላይ በዝምታ ተጥዶ፣ ቡና ተፈልቶበት፣ ያን ሁሉ ችሎ፣ በኋላ ለሥኒዎች ሁሉ የያዘውን ያከፋፍላል።

ዘ     አሃ!ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት እንደ ጀበና ነው?ከሰል ላይ እንደምጥደው ጀበና ነው?እሳት ጠግቦ ግንፍል ግንፍል እንደሚለው ጀበናዬ ነው?

ዠ    ኤዲያ ያንቺ ነገር፣ ቢገነፍል ባይገነፍል የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት መብቱ ነው።

ዘ     እንግዲህ ቡናዬን በሰላም ለመጠጣት፣ ግንፍል ግንፍል ባዩን ጀበናዬን፣ ከፊሉን ቡናዬን አፍሳሹን ጀበናዬን፣ በዚህም ምክንያት ከሰሌን የሚያዳፍነውን ጀበናዬን፣ ከከሰል አውርጄው እሲኪሰክን በዝምታ መጠበቅ ያለብኝ ጀበናዬ ነው የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ምሳሌ ነው የምትለኝ?

ዠ    እንዴ ይሄን ሁሉ አመት ታግሰሽ ኖረሽ የለም እንዴ?“ግንፍል፣ ግንፍል የሚለውን፣ ሁሌ እሲሰክን መጠበቅ ያለብኝን” ብለሽ የምትታዘቢው?

ዘ     ህምምምምም… እሱስ ልክ ነው። ታግሼ ችየዋለው። ሲሟሽ፣ ሲሟሽ ከከረመ፣ ከዛሬ ነገ ይሻለዋል ብዬ ችየዋለሁ።

(ጀበና ትተው የወሬ ርዕስ ቀየሩ፣ ወ/ሮ ዘ)

እኔ የምለው? ምሥር ደግሞ “ኢትዮጵያን እወራለሁ፣ አባይ ይነካና ዋ!” ብላ ትፎክራለች አሉ። እኔ እንኳን ጭምጭምታ ነው የሰማሁት። እሳት ላይ ተወርቷል አሉ። “ይቼ ጥሬ፣ ይቺ ምሥር፣ ካደረች አትቆረጠምም” አሉ አበው።

ዠ    ዛሬ ደግሞ ከበደ ሚካኤልን መሆን አማረሽ እንዴ?ምነው ተረትና ምሳሌ አበዛሽ?። ግብጽ በማለት ፈንታ ምሥር የምትይውና የምትተርቺው?ደግሞ የእሳት ወሬ አታምጭብኝ። እሳት ማለቴ “ኢሳት ይፋጃል” ሲባል አልሰማሽም?ሲፈጃቸው እኔ ዠ የእሳቱ ማብረጃ፣ ማጥፊያ መሆን አልፈልግም። “ግብጽ ብትመጣ እንዘምታለና!ግብጽ ምናባቷ እንዳትሆን ነው?እስኪ ትምጣና እናያለና!” ነው የሚባለው።

ዘ     ፉከራ!መፈከር ብቻ!

ዠ    መፈከር ሥራዬ እንደነበር አጣሽው እንዴ?

ዘ     ዘመቻ?ዘመቻ?የምንበላው የሌለን ሰዎች በባዶ ሆዳችን ነው የምንዘምተው?አሃ!

(አሉ ወ/ሮ ዘ ወደሰማይ አንጋጠው፣ መንግስተ ሰማያት ተከፍቶ የሆነ ነገር የነገራቸው መስለው ተናገሩ።)

አሃ! ስኳር! ስኳር ፋብሪካ ይስፋፋ የተባለው ለዚህ ነው ለካ!ስኳር እየበላን እንዘምታለና። ኢሃዴግ ስኳር እየቃመ ተዋግቶ አይደለም እንዴ ነጻ ያወጣን?ከተመክሮ የተገኘ መላ ነው። የስኳር ፋብሪካ ይስፋፋ!

(አቶ ዠ ለመናገር አፋቸውን ከፈቱ። ልክ ያኔ…)

ዠ   ደግሞ ይህንን ግንፍል፣ ግንፍል ባይ፣ ገሚሱን ቡናዬን ደፊ ጀበና ከዛሬ ጀምሮ አልፈልግም ብለው ጀበናውን ወለሉ ላይ ከሰከሱት።

አቶ ዠ ይህንን “ጨዋታ” ጻፉና ወረቀቱን ኪሳቸው ውስጥ ከተው ወደ ኢሃዴግ ፍቅር ቴአትር ቤት አቀኑ። በመንገዳቸው ላይ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ቆሞበት የነበረው ቦታ ላይ አንድ ሰውዬ ቆመው አዩ። ሰውዬ የአቡኑን ሃውልት የሚፈልግ ይመስላሉ። አቶ ዠ አልፈዋቸው ሊሄዱ ሲል ሰውዬው ጮክ ብለው ተናገሩ። የተናገሩት መንገደኛው፣ አላፊ አግዳሚው እንዲሰማቸው አልነበረም። አቶ ማሞ፣ ወፍጮ ቤታቸውና መኖሪያ ቤታቸው ለባቡር መሄጃ ተብሎ የፈረሰባቸው፣ አቶ ማሞ ለራሳቸው ተናገሩ።

“እኔና የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት የትም ወድቀን መቅረታችን ነው?”

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature, Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Gilentufagonji says

    January 30, 2016 12:15 am at 12:15 am

    Please speak freely, you are born free.So,why you go all around?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule