“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 … [Read more...] about አድዋ! 120 ዓመት!
Right Column - Primary Sidebar
ፍቅር እና የትብብር መንፈስ የታየበት ጉባኤ
በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ እሁድ ፌብሩዋሪ 14 ቀን፣ 2016 ከቀኑ 2:00pm 7:30 pm በሳን ሆዜ ከተማ ማሶኒክ ሴንተር፤ የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አራት ተናጋሪ እንግዳወች፣ የእምነት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሰሜን ካሊፎርኒያ ከተሞች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ሲሆን ከፍተኛ የሐገር ፍቅር ስሜት እና የትብብር መንፈስ በታየበት ሁኔታ ተጠናቋል። አዘጋጅ ኮሚቴውን ወክለው ስብሰባውን የመሩት ዶ/ር አበበ ገላጋይ፤ የውይይቱ ትኩረት ለሱዳን ስለተሰጠው የሀገራችን ለም መሬት፣ በወገናችን ላይ ስለደረሰው የድርቅና የረሀብ አደጋ፣ ስለሰብአዊ መብቶች መጣስ፡ የህዝብ መፈናቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ የአብሮነት ትስስሮች ላይ መሆኑን ገልጸው፤ አላማውም በተለያዩ ምክንያቶች የተራራቀውን ማህበረሰባችን በማቀራረብ የጋራ ችግሮቹን በጋራ ተወያይቶ … [Read more...] about ፍቅር እና የትብብር መንፈስ የታየበት ጉባኤ
በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ
የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016 3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤ 2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታቸው የሚያስመሰግን ነው። እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ ለመያዝ ነው። አስተናጋጁ ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ፤ "ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር … [Read more...] about በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ
ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ ለሰላምና ለዲሞክራሲ መስፈን ታጋይነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ስለ ሰላም የሰበኩ ያስተማሩና የጻፉ ቀንዲል ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ድህነትና በሽታ፣ ርሐብና ስደት፣ አምባገነንትና ጦርነት እያለ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበር፣ የሰብአዊ መብት መረጋገጥ፣ ዲሞክራሲና ሰላምን ማስፈን አይቻልም በሚል እምነታቸው በጽናት ታግለው ያታገሉ የዘመናችን ጣይቱ ነበሩ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመናገር የመጻፍ የመሰብሰብ የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የማሰማት መሠረታዊ መብቶች እውን እንዲሆኑ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ለሃገራችን ሰላም፣ የሃገራችን የፖለቲካ ችግር በዲሞክራሲ፣ በመቻቻልና በሰከነ ውይይት እንዲፈታ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሜያቸውን ሙሉ ታግለው ያታገሉ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
የማላውቃቸው፣ የማውቃቸው ሰውዬ
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበው ሆዴ? ይህ ታሪክ አይደለም። ታሪክ ያለፈ ነው ነገር፣ ያለፈ ጉዳይ ነው። ታሪክ ከከርስቶስ ልደት በፊት፣ የምንሊክ ንግሥና ጊዜ፣ የጣሊያን ወረራ ጊዜ፣ የመንግሥቱ ንዋይ ግርግር ጊዜ፣ ወያኔ አዲሳባ የገባች ጊዜ ተብሎ ይጀመራል .... እና ያልቃል። አዎን ያልቃል። እንኳን ሌላው ቀርቶ ሰማይና ምድር ያልፋሉና! ይህ የማላቀቸው ሰውዬ ታሪክ ነው ብዬ ብጀምር ይቀለኝ ነበር - ታሪክ ያለቀ ነገር ነውና! ያለቀ ነገር ህሊናን አይቦረቡርም። መጥፎ እንኳን ቢሆን የሚያጽናና ነገር ትቶ ያልፋልና። ምሳሌ፣ ጣልያን አቡነ ጴጥሮስን በግፍ ገደለ። የአቡኑ መሰዋት ግን ሺዎችን ለነጻነታቸው አነሳሳቸው። ይህ መጽናናትን ይሰጣል። የማላቀቸው ሰውዬ ታሪክ ግን አላለቀም። የማያልቅ ነገር ምን ይባላል? ምን ተብሎ ይጀመራል? ህንጻው ንግሥተ ነገስታት ዘውዲቱ … [Read more...] about የማላውቃቸው፣ የማውቃቸው ሰውዬ
“በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
ነሐሴ 21/2003 ከምሠራበት ቦታ በስልክ ተጠርቼ በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ ከሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስጄ ከአንዲት ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከተወረወርኩ በኋላ በማግስቱ አራዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቀርቤ የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብኝ ተፈቅዶላቸው፣ ያም ሲያልቅ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ የማይመለከቱኝን ጥያቄዎች ስጠየቅና ስመልስ ቆይቼ ጥቅምት 3/2004 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቤ የክስ ወረቀት ደርሶኝ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተልኬ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ዞን አንድ ቅጣት ቤት ተብላ በምትጠራው ቤት እገኛለሁ፡፡ የቀረበብኝ ክስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 241 የተመለከተውን በመተላለፍ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ሲሆን ዝርዝሩ፡- “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦ.ነ.ግ./ … [Read more...] about “በመጨረሻም ፍትሕ ከጎናችን ትቆማለች”
ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
ከኖቬምበር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል በጉልበት እያፈነው እንደሚገኝ ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ አስታወቀ፡፡ ከ2016 ዓ.ም. መነሻ ጀምሮ በእየለቱ ሰዎች እንደሚገደሉ እና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል፡፡ የወታደራዊ ሰራዊትን ያካተተው የጸጥታ ሃይል ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ቀጥታ በመተኮስ ገድሏል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ያለምንም ክስ እንደታገቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተቃውሞው ድግግሞሽ የቀነሰ መስሎ ቢታይም አፈናው ግን ቀጥሏል፡፡ “ኦሮሚያን በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች የማጥለቅለቅ እርምጃ የሚያመለክተው በተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ ባለስልጣን አካላቱ በከፍተኛ ሁኔታ አለመፈለጋቸውን … [Read more...] about ተቃውሞ አድራጊዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም
Representatives of Diverse Ethiopians formed:
Executive Summary: On February 14, 2016, the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) announced the formation of the Ethiopian Council for Reconciliation and the Restorative of Justice (ECRRJ) at a public meeting held at the Sheraton Hotel in Silver Springs, Maryland. The Council’s formation was the outcome of a strategic planning retreat held over the course of three days previous to the meeting. Those attending the retreat were representatives of diverse Ethiopians. The ECRRJ is a … [Read more...] about Representatives of Diverse Ethiopians formed:
ጋኔኑ ማነው?
“ጋኔን ልክ ማስገባት የሚችለው … መንግሥት ነው” ጌታቸው ረዳ ታኅሳስ 6፤2008 ዓም “የታጠቁ ወንበዴዎች በየመንገዱ በየመንደሩ እየዞሩ ህዝብን የሚያሸብሩበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፤ ወደለየለት ሽፍትነት ተገብቶ ነው ያለው፡፡ እነዚህ ሰዎች የተላለፈላቸው መመሪያ ይሄ ነበር ወይስ አልነበረም ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ በሀገራችን ላይ ሁከት የጠራ ወገን፣ ጋኔል የጠራ ወገን ጋኔሉን ስለመቆጣጠሩ እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡ አሁን የጠሯቸው ሰዎች የጠሩትን ጋኔል ስለመቆጣጠራቸው እርግጠኛ አይደሉም፡፡ ይህንን ጋኔን ልክ ማስገባት የሚችለው የተደራጀ ህዝብና መንግስት ብቻ ነው፡፡” አፈቀላጤ ጌታቸው የካቲት 11፤2008ዓ.ም ይህንን አሉ: “እኔ ሁከት የጠሩ ወገኖች ነው (ጋኔን) ያልኩት። ሁከቱን ስለማይመልሱት ሕዝብና መንግሥት ይህንን ሁከት መመለስ ይገባቸዋል፤ በአጋጣሚ የእንግሊዝኛን አባባል ወደ … [Read more...] about ጋኔኑ ማነው?
የዘመነ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምት
በዛሬው ርዕስ ሥር የማነሳው ጉዳይ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምትን ይመለከታል። በርግጥ ይህን ርዕሰ ጉዳይ በቅርቡ ከተቋቋመው የ EDF (Ethiopian Dialogue Forum) ድርጅት ዓባላት ጋር በነበረን ቴሌ ኮንፈረስ ላይ ለውይይት አቅርቤው ነበር። ዛሬ ደግሞ በቀለም ቀንድ ጋዜጣ በኩል ከሃገር ቤት ወገኖቼ ጋር ለውይይት ይሆነን ዘንድ መረጥኩት። እንግዲህ በዓለም ላይ እጅግ ብዙዎቹ አገራት ወይ በባህል ወይም ደግሞ በሃይማኖት ብዙሃን ሆነው አንድ አገር መስርተው ይኖራሉ። አንዳንዶቹ ሃገራት እጅግ ብዙ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖችን ይዘው በአንድ የፖለቲካ ጠገግ ውስጥ ይኖራሉ። ለምሳሌ ናይጀሪያ ወደ 250 ብሄሮችን ይዛ እነዚህ ብሄሮች በአንድ ፌደራል ሪፐብሊክ ናይጀሪያ የፖለቲካ ጠገግ ስር ተጠልለው ይኖራሉ። ኢንዶኔሽያን የመሰረቱ ቡድኖች ደግሞ ወደ 300 ቡድን ናቸው። … [Read more...] about የዘመነ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቅርምት










