ስለ ብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ አጠር ምጥን ተደርጎ የተዘጋጀውን ባለ አምስት ነጥብ የዳሰሳ ጥናት (survey) ለዚሁ ጉዳይ ሲባል ብቻ ወደ ተዘጋጀው ድህረገፅ እዚህ ላይ በመጫን በመሄድ ድምፅዎን ያሰሙ። የዝምተኛው ብዙሃን ድምፅ ጭምር ሳይቀር እስቲ ይሰማ! ፖለቲካውንና ፍልስፍናውን አርባ አመት አውጠንጥነን አረጀንበት። እንዲሁ ስንባዝን እድሜያችን አልቆ አንድ ባንድ ወደ ሞት ልንሄድ ነው። እርቅና መግባባትን ማን ጠላ? መላው ጠፍቶብን እንጂ። አይ መላውም አልጠፋን እንደ እውነቱ ከሆነ። ኢትዮጵያ መፍትሔ ሊያመጡ የማይሳናቸውን ልጆች ወልዳ ሳለ እንደ መካን ቁጭ ብላ መቆዘም አይገባትም። እስቲ የልበ ሰፊው፦ የአስተዋዩና የጨዋው ሕዝብ ድምፅ እንስማው። ባለስልጣኑ በራሱ ጡንቻ ተማምኖ ተቃዋሚውን ከመንጫጫት በላይ ምን ያመጣል ብሎ ሲንቅ፦ ተቃዋሚው ምንም ይሁን ምን ባለስልጣኑ … [Read more...] about የብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ
Left Column
The perils of outsourcing the fight for freedom
I could have titled this piece ‘Obama and his Africa peace keepers’ but that would not be fair. Anybody with half a brain can see that I am trying to make my issue to be his problem. Excuse me just because fighting for my right is beneath my dignity there is no reason to impose on him that I am unable to do for whatever reason. Dear Mr. President we Africans are not amused! This is what appeared on The Guardian ‘According to President Obama, who announced a series of American support and … [Read more...] about The perils of outsourcing the fight for freedom
የግልና የመንግሥት ለቅሶ
(ሃዘንን በሳቅና በፈገግታ ካላሳለፉት መሪር ይሆናል) አቶ መለስ ያረፉ ሰሞን በየሰፈሩ ድንኳን ተጥሎ ነበር። በዚያው ሰሞን አንድ ሌላ ለቅሶ ሳሪስ አካባቢ አንድ ቤተሰብ ልጃቸው አርፋ ለቅሶ ተቀምጠው ነበር። በዚህ ጊዜ አንዷ በስህተት (የአቶ መለስ ድንኳን መስሏት) "ራዕያቸው"፤ "ራዕያቸው" እያለች እያለቀሰች ለቅሶ ቤት ስትገባ ልጃቸው ያረፈችባቸው አባት በንዴት "ይህ የግል ለቅሶ ነው የመንግስት ለቅሶ አይደለም የመንግስት ከፈለግሽ ወዲያ ተሻገሪ" ብለው አመነቃቅረው አባረሯት። (ከHayle Adam ፌስቡክ የተገኘ) … [Read more...] about የግልና የመንግሥት ለቅሶ
ክደራና ክየና
አንድ ብልጣብልጥ ባለተራ ፤ ከያኔ ነኝ የሚል ጽፎ በእሱ ቤት የማላውቅበት ፤ መከደሩን ለንብ ቀፎ በየሔደበት ያወራል ፤ ጸሐፊያንን ነቃቅፎ ጋዜጣ መጽሔት ድረ ገጽ ፤ ወደዛ! እያለ ተጸይፎ አታንብቡ አትስሟቸው ፤ ብሎ ያርቃል አንባቢ የጌቶቹ ጉድ እንዳይወጣ ፤ እንዳይገለጥ ሸባቢ እንዴት ምን ነካህ? ለሚሉት ፤ ተገርመው በጭፍን ትችቱ ችግር መኖሩ መች ጠፋን ? ይሄ ሀገር የሚሻው በብርቱ መፍትሔውን ቢነግሩን ነው ፤ ይላል ልሳኑን አስልቶ መፍትሔው እንዳልተጻፈ ፤ ከችግሮቹ ጋር ጎልቶ፡፡ ይሄው አይደሉ እነሱ? ማደናቆር መተጣጠፍ ምን እነግራለሁ ለእናንተ ፤ ታውቋቸው የለ ከወደአፍ? በዐይን የሚታየው በጉልህ ፤ የሚጨበጠው ተይዞ ካሳበቃቸው ጭራሽ የለም ፤ በቃ የለማ ማን አዞ? የማይታየው የሌለው ፤ ምናባዊውን ሕልም እንጀራ ብሉ ጠጡ ጥገቡ … [Read more...] about ክደራና ክየና
ጭቃና ውኃ
ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ያረፈደው አያ ከጭቃው ገበያ ያውና ብቅ አለ ከጭድ መሃል ወጣ በጨመለቅ እጁ ሊጨብጠኝ መጣ። 'መቼም ከጭቃ ነው ተፈጥሮ ስሪቴ' ብዬ እንዳልጨብጠው 'እምቢኝ!' አለኝ ቤቴ "ጭቃማ አይደለሁም! _ ነኝ እንጂ ውብ ሸክላ ታሽቶና ተቦክቶ በውቅ የተኮላ ይታጠብ በቅድሚያ አቅርብለት ውሃ ለጨቀየው ነፍሱ በነገር ቤት ዝሃ" ብሎ ይሞግተኛል ተላላው መንፈሴ ውሃውን ረስቼ ጭቃን በማንገሴ እነሆኝ በል እንካ አንተ ጭቃ ለዋሽ ኮዳዬን ዘቀዘቅኩ ለእድፍህ አባሽ። የመንፃት ቀንህን አታርቀው ጓዴ ውሃዬን ተጠቀም ላፍስልህ ላንዴ ከዚያም ልጨብጥህ ደርሳለሁ ዘመዴ ጭቃ እያቦካ ጭቃ እየለወሰ ጭቃ እየጋገረ ጭቃ እየጎረሰ ስንቱ ሰው መሰለህ ደግሞ የታደሰ ከመቡካት በኋላ ውበት የለበሰ። … [Read more...] about ጭቃና ውኃ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፱” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ዘጠኝ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያንና መልሱን አዘጋጅተው ልከው ላቆየንባቸው ወለላዬ ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ ትንሽም ቢሆኑ - ቁጥራቸው ባይበዛ የድሮ ዘፋኞች - ነበራቸው ለዛ ከነዛ መካከል - በድፍን ከተማ ታዋቂ ነበሩ - እሳቱ ተሰማ ምስጋና አቀርባለሁ - መልስ ለሰጣችሁ እሳቱን እወቁ - ደግሞ ሌሎቻችሁ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲
የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊመብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነው መቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽ ሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል፡፡ ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባት የምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰት እድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁን ግን ክሱ አንድ … [Read more...] about የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
“ፋክት መጽሔት”
ከሁለት ሳምንታት በፊት በ9-11-2006ዓ.ም. አንድ የፋክት መጽሔት ደንበኛ የሰፈር ሰው አንድ ጸሐፊ በፋክት መጽሔት ላይ አንድ ጽሑፌን መነሻ አድርጎ ያልኩትንም ያላልኩትንም እየቀላቀለ አብጠልጥሎኝ ኖሮ ይሄ ቁጭት ፈጥሮባቸው ስለነበር ባገኙኝ ጊዜ “ባይ ባይ ምንም የለም ለምንድን ነው መልስ የማትሰጠው?” ሲሉ ጠየቁኝ፡፡ ለማን? ስል መለስኩላቸው ፋክት መጽሔት ላይ ስምህን ላጠፋው ሰው ነዋ! አሉኝ፤ ማን ነው ስሜን ያጠፋው? ስላቸው እንዴ! አላየኸውም ማለት ነው? አንዱ እኮ ጻፈብህ አሉኝና ወደ ቤታቸው ገብተው መጽሔቱን ይዘው መጡ ያሉትን ጽሑፍ አነበብኩት ልክ ወያኔ ዜጎችን “የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ” እያለ እንደሚያሸማቅቀው ሁሉ ይሄም ሰው እኔን “ባረጀውና ባፈጀው መንገድ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል ሰው፣ የብሔረሰቦችን እኩልነት የማይቀበል” ምንትስ እያለ እንደ ወያኔ በፈጠራ ክስ … [Read more...] about “ፋክት መጽሔት”
አበሻና ጽሕፈት
በቅርቡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስለኢየሩሳሌም ማኅበር ስናወራ መሥራቹ አቶ መኮንን ዘውዴ ትዝ አሉኝና ስለሳቸው ውለታ ሳወራ ነበር፤ ከሳቸው ጋር ተያይዞም ከዚህ በፊት አይ አበሻ! በሚል አጠቃላይ ርእስ አበሻና ልመና ወዘተ. እያልሁ መጻፍ ጀምሬ የነበረው ትዝ አለኝ፤ አንዳንድ ስላልገባቸው ነገር ሁሉ መጻፍ የሚወዱ ሰዎች አቅጣጫውን ሊለውጡት ሙከራ ሲጀምሩ ትቼው ነበር፤ አሁን የመክሸፍን ጉዳይ ደግሜ ለመጻፍ ስጀምር አንዳንድ በጣም መሠረታዊ የሆኑ የመክሸፍ መገለጫዎችን ስጽፍ በመጽሐፍ መልክ እስኪወጣ አላስችል አለኝና አንዱን ሀሳብ አደባባይ ለማውጣት ወሰንሁ፤ በዚያውም አቶ መኮንን ዘውዴን ማስታወሻ ይሆነኛል። ወደ 1935-36 ግድም በአዲስ አበባ ውስጥ ክፉ ችግር ቸጋርን አስከትሎ ነበር፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ገና ከስደት ከተመለሱ ሁለትና ሦስት ዓመት መሆኑ ነው፤ አገር አልተረጋጋም፤ የኢጣልያኑ … [Read more...] about አበሻና ጽሕፈት
ጥሩ ምግባር ሁሌም ያስመሰግናል!
ለእኔ ለፈጣሪ በታች በጎ ለሚሰሩ የሰው ዘሮች በሙሉ የሚሰጥ ምስጋና ቃል ይስበኛል። ብዙ ጊዜ የመልካምና የበጎ ምግባር ፋና ወጊዎች ስራ ተመልክቸና መስጦኝ ለቀሪው አርአያ፣ ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ምንጭ ነው ብየ ካሰብኩና ካመንኩበት የምስክርነት ቃሌን የምሰጠው ምስጋና በማቅረብ ነው። ይህን ካልኩኝ ዘንዳ የዛሬ የእኔን ምስጋና በአስተዋሽ አመስጋኙ አይታክቴ ለፌስ ቡክ ወዳጀ Eduardo Byrono፣ ለወጣቷን ድምጻዊ ሃኒሻ ሰሎሞን ያላቋረጠ ድጋፍ አድርጎ ለውጤት ላበቃ ጋዜጠኛ ወዳጀ ለጋዜጠኛ ድልነሳው ጌታነህ እና ለድምጻዊ ሃኒሻ እጅ በመንሳት ምስጋና በማለዳ ወጌ ላቀርብ በቀኝ ጎኔ ተነስቻለሁ! ዘመኑ ረቅቋል፣ ጊዜ ወስደን የምናዘጋጃቸውን ማናቸውም መረጃዎቸ በሰከንድ ልዩነት ከአንዱ ከአድማስ አድማስ መርጨት በቀለለበት ዘመን ላይ እንገኛለን። በማህበራዊ ድህረ ገጾች የሚተላለፉ … [Read more...] about ጥሩ ምግባር ሁሌም ያስመሰግናል!










