ይሄንን ጽሑፍ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ “ጆሲ ኢን ዘ ሀውስ” የተሰኘው በዮሴፍ ገብሬ እየተዘጋጀ ኢ.ቢ.ኤስ በሚባል የኬብል ቴሌቪዥን (የመስመር ምርዓየ-ኩነት) የሚቀርበው የጥዕይንተ ወግ ዝግጅት ነው፡፡ ወደዚህ ትዕንተ ወግ ጉዳይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በብዙኃን መገናኛዎች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች ውስጥ የትዕይንተ ወጎችን (Talk shows) ያህል የመወያያ፣ የመገናኛ፣ የመቀራረቢያ፣ የመደማመጫ፣ የመተዋወቂያ እንዲሁም አሳታፊ ዐቢይ መድረክ የለም፡፡ እነዚህ መድረኮች ጠቀሜታቸውና ሚናቸው ጎልቶ የመታየት ዕድል የሚያገኙት ግን ካለው ምቹ የአሥተዳደር ሥርዓት የተነሣ በምእራቡ ዓለም ሀገራት ነው፡፡ መቸም ከመወያየት የማይገኝ ጥቅም የማይፈታ ችግር የለምና እነዚህ ዝግጅቶች በእነዚህ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያበረከቱ የማይተካ ሚናቸውንም እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ከጠቀሜታቸው ጥቂቶቹን … [Read more...] about ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን
Left Column
“ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
መግቢያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። መባል ስላለበት ነው። ያለፈውማ ዓመት አንደኛውን ጥቁር ዓመት ተብሏል። ሲያንሰው ነው። ወያኔ ከመቼው በበለጠ ጥቃቷን በኢትዮጵያ ልጆች ላይ በሁሉም አቅጣጫ ያጧጧፈችበት ዓመት ነበር። ነጻውን መገናኛ ብዙሀን ከጨዋታ ውጪ አድርጋለች። ብዙ ጋዜጠኞች በማሠሯ ወህኔ ቤቱ ጠቧል መሰለኝ፣ አሁን አሁን የያዘችው ዜዴ፣ በቁጥጥሯ ሥር ከሌሉ፣የፋሺን ጋዜጠኞችም ሳይቀሩ ማዘዣ ሳይደርሳቸው፣ በሬዲዮዋና በጋዜጦቿ “ከስሼአቸዋለሁ!” በማለት፣ ነጭ ሽብር እየነዛችባቸው በርግገው ከአገር እንዲጠፉ ማሳደዷን በሰፊው ተያይዛቸዋለች። በዓመቱ መጨረሻ ወር ብቻ 21 ጋዜጠኞች ተደናብረው አገር ጥለው እግሬ አውጪኝ ብለዋል። ሲሸሹም እያየች አታስቆማቸውም። ብቻ ሲወጡላት፣ “እስየው ተሰደዱልኝ!” ብላ “ደቁሴ ንሬ፣ ተባራብሬ!”ዋን ትደልቃልች! ወንድማችን እስክንድር ነጋ፣ … [Read more...] about “ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
The Ethiopian Diaspora and consciousness
The Bay Area that currently is home away from home for thousands of Ethiopians is nothing like any other place that I have known. I was born in a small village on the southern part of Ethiopia and have resided in Addis Abeba, Oregon and Seattle Washington before moving here. The Bay Area is unique. I thank the Gods and celebrate my luck whenever I have a chance. The place where I originated from is not known for such movement of people from one location to another. As much as I remember the … [Read more...] about The Ethiopian Diaspora and consciousness
“ክልክል ነው”
ማጨስ ክልክል ነው ማፍዋጨት ክልክል ነው መሽናት ክልክል ነው ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል የቱ ነው ትክክል? ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ "መከልከል ክልክል ነው"፤ የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡ (በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000) … [Read more...] about “ክልክል ነው”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ከምንጊዜም በላይ - ብዙ ሰው ተሳትፎ ማንነታቸውን - እንዳሳየን ጽፎ በጀግንነታቸው - መቼም ያልተረሱ እኚህ ስው ነበሩ - ደጃዝማች ገረሱ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ ጥያቄ ድጋሚ ተወልደው - በህይወት ቢኖሩ የምንፈልጋቸው - ብዙዎች … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፪
በግ አሳራጅና አራጅ
አቶ ኑሮ ውድነህ አምና የአዲስ ዘመን በዓልን አስመልክቶ ቤተሰባቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላቸውን ገንዘብ አሰባስበው ገበያ ይሄዱና የበግ ዋጋ ይጠይቃሉ። ሆኖም የበጎቹን ዋጋ ሲሰሙ የሚሮጡት የርቀት መጠን በሜትር እየተነገራቸው እንጂ መሸጫ ዋጋቸው አልመስል እስኪላቸው ድረስ አስደንጋጭ ይሆንባቸዋል። አውጥተው አውርደው ግን ለቤተሰባቸው መጠነኛም ብትሆን በግ በመግዛት ሃሳባቸው ላይ ፀንተው ረከስ ባለ ዋጋ እጅግ ቀጫጫ የሆነች ግልገል በግ ተከራክረው ይገዛሉ። እናም ወደቤታቸው እየሄዱ እያለ በግ አራጅ ይመለከታሉ። እሳቸውም ወጉ እንዳይቀርባቸው: አቶ ኑሮ ውድነህ: ኮራ ጀነን ብለው "ስማ አንተ በግ አራጅ . . . እስኪ ና ወዲህ" ይሉታል። በግ አራጅ: ወደ ሰውየው እየተጠጋ "አቤት?" አቶ ኑሮ ውድነህ: በኩራት እንድ ሁለቴ ካገሱ በኋላ "ይህቺን በግ ስንት ትገፍልኛለህ?" … [Read more...] about በግ አሳራጅና አራጅ
ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ
በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሽብርተኝነት ያለው አረዳድ እና ወያኔ ሽብርተኝነትን የሚተረጉምበት መንገድ ለየቅል ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብርተኝነት ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ ተይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ መነጋገሪያ የሆነው በ1934 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ነው። በዛሬው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተተካው የሊግ ኦፍ ኔሽን በሽብርተኝነት ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ በ1937 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና ለመቅጣት የሚያስችል አንድ ድንጋጌ (Convention for the prevention and punishment of terrorism) አጽድቋል። ከዚህ ድንጋጌም በኋላ ከ14 የሚበልጡ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ስምምነቶች በተባበሩት መንግስታት ጸድቀዋል። የእነዚህ ሕጎች ዋነኛ አላማም መንግሥታት ሽብርተኝነትን በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲዋጉ ለማስተባበር ብቻ ሳይሆን ሽብርተኝነትን … [Read more...] about ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ
የከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሰባ (ሳባ) ደረጃና ቅኔው
“በሰባ (ሳባ) ፈረጃ” ሰሞኑን ከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን የለቀቀው ነጠላ ዜማ ነው፡፡ የዘፈኑ (የሙዚቃው) በነገራችን ላይ ሙዚቃ የአማርኛ ቃል አይደለም ሚውዚክ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በሀገርኛ አማርኛ ሲጠራ ነው ልክ school አስኳላ እንደተባለው ማለቴ ነው፡፡ እናም ቴዲ ይሄንን ነጠላ ዘፈን እንደለቀቀ ያው እንደሚታወቀው ቴዲ ዝም ብሎ ዘፋኝ አይደለምና ማለትም የሥነ-ኪንን ዓላማና የዜግነት ግዴታን ጠንቅቆ የሚያውቅ የተረዳ በሥራዎቹም ላይ በተደጋጋሚ ይሄንን ያሳየ ከያኔ ነውና በዚህ ነጠላ ዜማው “ምን ብሎ ይሆን?” በሚል ጉጉት አድማጩ ያተኮረው በስንኞቹና መልእክታቸው ላይ ነበር፡፡ ለሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ይህ ነጠላ ዜማ ቴዲን የማይመጥን ብላሽ ዓይነት ዘፈን ነው የሆነበት፡፡ አንዳንዶችማ ጭራሽ “ቴዲ እንዴት ቢንቀን ነው እንዲህ ዓይነት ፍሬ ፈርስኪ የሆነ ዘፈን በነጠላ ዜማ … [Read more...] about የከያኔ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሰባ (ሳባ) ደረጃና ቅኔው
2007-A year of decision
Happy New Year Ethiopia (መልካም እንቁጣጣሸ) Meskerem is a special month. We love and honor Meskerem so much that we name our children by it signifying a new beginning for the long journey ahead. Meskerem is the end of the rainy season and our high mountains and valleys adorn themselves in bright yellow flowers as far as the eye can see, totally overwhelming our senses. For a Diaspora, Meskerem in a strange land, is another hard pill to swallow as an exile from a precious homeland. The physical … [Read more...] about 2007-A year of decision
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስር ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ (እንደተለመደው በየሳምንቱ መልሱን ተከታትለን ባለማቅረባችን ለአንባቢያን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን::) መልስ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ - እኔ ነኝ ተዘራ የማስደስታችሁ - ከክራሬ ጋራ ብለው የዘፈኑ - በገዛ ስማቸው ድምጻዊ ተዘራ - ማለት እኚህ ናቸው ላሁኑ ደግሞ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፩










