ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስምንት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በብዙ ትያትር - የመድረክ ዝግጅት ዝናን ያተረፉ - ቀርበው በመታየት «የአዛውንቶች ክበብ» - በተለይ ሲነሳ እስከዛሬ ድረስ - ያላጡ ሙገሳ አስካለ አመንሸዋ - ማለት እኚህ ናቸው ከእድሜው በረከት - አሁንም ይስጣቸው። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፱
Left Column
“ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት”
“. . . ይህንን የትግሉን ህዝባዊ ገፅታ ችላ ብለን እነዚህን ሚሊዮኖች የሚያካትት ህዝባዊ የትግል ማእበል ለመቀስቀስ፣ መቀስቀስ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለን የጋራ ስትራቴጂ አውጥተን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር “በእኛና በእነሱ” መሃከል በተወሰነ የትግል ክፈፍ ከብረት ድስትና ከሸክላ ድስት ፍልሚያ፤ ሸክላ በአሸናፊነት ይወጣል በሚል የአጉል ህልም ዓለም ውስጥ ነን ማለት ይሆናል፡፡” ዶ/ር ነገደ ጎበዜ በምርጫ 97 ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማቸው ውስጥ ተቃዋሚዎችን ለመወንጀል እየተንጨረጨሩ ያነሱት ስም ነገደ ጎበዜ የሚለውን ነበር። ያ ስም እንደገና ተመልሶ መጥቷል። አሁንም ከመጽሐፍ ጋር ነው የመጣው። ዶ/ር ነገደ ጎበዜ “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” የሚል አዲስ መጽሐፍ ይዘው መጥተዋል። ቀደም ሲል “ሕገ መንግሥት ምርጫና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ (ከትላንት ወዲያ … [Read more...] about “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት”
“መሰበር” የማይቀር ነው
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ “በድርብ አኻዝ አድጓል፤ እያደገም ይሄዳል፣ ይቀጥላል፣ ይመነደጋል” እየተባለ “በተዘመረበት” ዓመታት ሁሉ በአንጻሩ በገሃድ ያለውን እውነታ ቁልጭ ባለ መልኩ የሚያሳዩ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል፤ እየወጡም ይገኛል፡፡ ሆኖም እነዚህ ዘገባዎች በሥልጣን ላይ ያሉትን ሁለቴ እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው እንደሚገባ ቢነገርም ምላሹ የተለመደው “የልማት ጸሮች” ያወጡት፣ “የአሸባሪዎች እጅ ያለበት”፣ “የኒዎ-ሊበራል አቀንቃኞች ዘገባ”፣ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምኞት”፣ ወዘተ ከሚል አልፎ አያውቅም። በተደጋጋሚ የሚወጡ ዓለምአቀፋዊ መረጃዎች አገራችን በመክሸፍ ወይም በመሰበር አደጋ ላይ እንደምትገኝ ይናገራሉ። እነዚህ ጥናቶች በአብዛኛው የሚወጡት በምዕራቡ ዓለም በሚገኙ የጥናት ተቋማት በመሆናቸው ከላይ እንዳልነው “የወገኑ ናቸው”፣ “የልማታችንና የህዳሴያችን ተቃዋሚዎች ናቸው”፣ “ሚዛናዊ … [Read more...] about “መሰበር” የማይቀር ነው
ሰውና ልማት
ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ በአለው አቅምና ችሎታ አነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ይጥራል፤ ይህ ቀላል አይደለም፤ ቀላል የማያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንደኛ፣ የሰውም፣ የእንስሳም፣ የእጸዋትም ሁሉ መኖሪያና መመገቢያ ምድር አንድ ነች፤ ስለዚህ ውድድሩ ከባድ ነው፤ በዚች ምድር ላይ እየኖሩ፣ ምድር የምታፈራውን እየተመገቡ፣ ውሀዋን እየጠጡ በሰላም መኖር … [Read more...] about ሰውና ልማት
የኔኛው
አንዱ አንበሳ ነው. . . ወገኑ ሲነካ ዘራፍ ነው የሚለው። ሌላው ደግሞ ጅብ ነው. . . የሚበላ አግኝቶ ግዳይ የጣለ ዕለት፥ ወገኑን ሳይጠራ ጭራሹን አይነካት። የኔኛው ውሻ ነው ለያውም ተናካሽ፥ የራበው ወንድሙን ወገኑን አስለቃሽ። የሞተ አግኝቶ በልቶ ይጠግብና፥ ወገኖቹ ውሾች እንዳይበሉ ይልና፥ እዛው ጋር ይተኛል እያባረራቸው፥ ትንሽ እንዳይቀምሱ ሊከለክላቸው። ግን ቁራና ጭልፊት ከሰማይ የሆኑት፥ ምንም አይላቸው ስስቱን ሲበሉት። ----- (By Gemechu Merera) 23/11/2009 … [Read more...] about የኔኛው
መርፌ
አንድ ቀን ተነስቶ፣ መርፌ ተቆጥቶ፣ መርፌ ተበሳጭቶ፣ አልሰጥም ያለ ቀን - ያንን ቀዳዳውን፣ ክር አንጀቴን በላኝ - እንጃለት መግቢያውን። … [Read more...] about መርፌ
እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሰባት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ማራቶን ማራቶን ማራቶን ልዕልቷ አበበና ማሞ ሆኑ ባለቤቷ ማራቶን ደንግጠሽ አቤን ብትቆጪ ዕድሉ የኛው ነው የትም አታመልጪ ብለው ያወደሱ - ሜክሲኮን ኦሎምፒክ የኳስ ስም ሲነሳ - የሚታውሱ ሰርክ ግጥም ያቀበሉ - ለብዙ ዘፋኞች ዝናን ያተረፉ - በስፖርት ዓለም ሰዎች አገር የሚሸበር - ድምጻቸው ሲሰማ እኚህ ሰው ነበሩ - ስለሞን ተሰማ፡፡ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፰” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
“ጎንደር ቤተ መንግስት ውስጥ ኦሮሚኛ ቋንቋ ይነገር ነበር”
በተለያዩ ድረ-ገፆች በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚያንሸራሽሩት ሃሳብ ይታወቃሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያኒዝም፣ ስለ ፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴዎች የተለያዩ ምልከታዎችና ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ ተሰሚነት ካላቸው ኢትዮጵያዊያን ምሁራን አንዱ ናቸው - ፕ/ር ማሞ ሙጬ፡፡ ሰሞኑን ጐንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 60ኛ አመት በዓል ሲያከብር “Towards Innovative Africa: The Significance of Science, Technology, Engineering and Innovation for Sustainable Development” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በአሁን ሰአት በደቡብ አፍሪካ ሊዋኔ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ባለፈው ሳምንት በጐንደር … [Read more...] about “ጎንደር ቤተ መንግስት ውስጥ ኦሮሚኛ ቋንቋ ይነገር ነበር”
ዛፎች
ከዛፎች መካከል ዛፎች ሲቆረጡ ዎዮው ላሽሟጠጡ፡ ዎዮው ላላገጡ፡ የተጨፈጨፉት የተቆረጡቱ፡ ለምሣር እጄታ ተገጥመው ሲመጡ። … [Read more...] about ዛፎች
መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!
የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ … [Read more...] about መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!










