በመጀመሪያ "የለውጡን (ሥሌት) የሰራሁት እኔ ነኝ" አለ - በዝምታ "አዎ ነህ" ተባለ ቀጠለና "እዚህ ሀገር ሁለት መንግሥት ነው ያለው የአብይ እና የቄሮ [የኔ]" አለ አሁንም በዝምታ "አዎ ልክ ነህ" ተባለ መንግሥት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጃዋር መንግሥት በንግግር ብቻ ሳይገታ ውሳኔዎችን መሻር ማሳለፍ ጀመረ - በዝምታ መንግሥትነቱ ተረጋገጠለት እነሆ አሁን ደግሞ ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የመንግሥት ሰዎች፣ አኩራፊዎች እና ጥገኛ ባለሀብቶች በተቀነባበረ ሴራ "ኢመደበኛው መንግሥታችሁ ሊገረሰስ ነው" ተብሎ (“የመግደል ሙከራ” በሚል ፈጠራ) 67 ንፁሃን ምስኪኖች ያልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይፀና፤ ምሽጉም ይጠነክር ዘንድ መስዋዕት ሆነው ቀረቡለት። ይሄን ጊዜ በዝምታ አያልፉም ስንል - ተናገሩ! ምን አሉ "አንተ ዐይን ነህ - እንደ ብሌናችን … [Read more...] about እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች! የኢትዮጵያን ሕዝብ በአፈና፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ ጥሰት ሲገዛ በነበረው ህወሓት እና በሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቡድኖች በገዥነት ዘመናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል አገርን ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ተረድተናል። በተለይም አሁን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ ሌሎች አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ የሚያደርገው ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን የውህደት እንቅስቃሴ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ከማጣጣል ጀምሮ፣ የተለያዩ የትርምስ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን … [Read more...] about “የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
በተለያየ አጋጣሚ ከሚያጋጥሙኝ አስተያየቶች አንዱ ጃዋር መሃመድን መነጋገሪያችን ማድረጉን እንተው፤ግለሰቡ የሚሰጠንን አጀንዳ አንስተን በመተንተን ሰውየው የሚፈልገውን ክብር በመስጠት ተፅኖ ፈጣሪነት እንዲሰማው አናድርግ የሚል ነው። በግሌ ስራየ ብሎ ሰውን ማጉላትንም ሆነ ሆን ብሎ ሰውን ማሳነስን ብቻ አላማ አድርጎ መጓዙ የብልህ መንገድ አይመስለኝም። ጠቃሚው ነገር የሰው ስራ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩ ይመስለኛል። በዚህ ሁኔታ ግባችን ግለሰቦች ሳይሆኑ የግለሰቦች ሃሳብ እና አካሄድ የሚያመጣው በጎ ወይ መጥፎ ተፅዕኖ ነው። በጎ ወይም መጥፎ ተፀዕኖ ያመጣውን የሰዎችን ስራ በተመለከተ ስንነጋገር የሰዎችን ስም ማንሳታችን ደግሞ አይቀርም። በጎውን ስራ ስናወድስ፤ መጥፎው ስራ ወደ ባሰ መጥፎ እንዳያድግ ልንነጋገርበት ስናነሳሳው ከግለሰቦች ጋር የተለየ ፀብ ወይም … [Read more...] about ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!
ማነው የዋሸው? ጃዋር? የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወይስ የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር? መንግሥት በሕዝብ ገንዘብ ጥበቃ የሚያደርግለትን ጃዋርን በሌሊት የሚከብበት ምን ምክንያት አለ? ማለቴ ተከቦ የተቀመጠው በመንግሥት ጠባቂዎች አይደለም ወይ? ለምን ጃዋርስ ተፈጠረ የተባለውን ነገር ሆን ተብሎ በመንግሥት የተቀነባበረና “እኔን ለማጥቃት የተፈጸመ ድርጊት ነው” አለ? ማለቴ ይህ ዓይነት ጥርጣሬ ካለው እንዴት በመንግሥት ታጣቂዎች እየተጠበቀ ዕንቅልፍ ወስዶት ያድራል? እንዴት እንዲህስ ሊያስብ ይችላል? ወይስ ጠባቂዎቹን የራሱ አድርጓቸዋል? ከመቼ ወዲህ ነው የመንግሥት ታጣቂዎች በመንግሥት ተመድበው ሳለ ራሱ መንግሥት፤ ለዚያውም እንደ ጃዋር አገላለጽ ዋናው ኮማንደር ለቃችው ውጡ ሲላቸው እንቢ ሊሉ የቻሉት? ከመንግሥት ይልቅ ታዛዥነታቸው ለጃዋር ያደላ ነው ማለት ነው? በዚህ ዓይነት … [Read more...] about ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!
ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“… ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም አንድ ጎረምሳ ልንለው እንችላለን። ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ በመሆኑ የጃዋር ሚዲያ የተመዘገበው በዚህ ጎረምሳ ስም ነው። ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚቀመጠው በዚሁ ልጅ ስም ነው። መኪኖችና አንዳንድ ንብረቶች የሚገዙትም በዚሁ ስም ነው። ይህ ጎረምሳ አዲስ አበባ እጅግ መንዛሪና በከፍተኛ ቅንጦት እንደሚኖር የሚያውቁት ነገረውኛል። የቄሮ አካልም አልነበረም። ቄሮ ከድል በኋላ ቤቱ ሲመለስ የጠበቀው ማሳውና መደቡ ሲሆን እነ ጃዋርና ስማቸውን የሚጠቀሙባቸው ጎረምሶች በሚሊዮኖች እየረጩ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይሸምታሉ፤ ንብረት ያከማቻሉ፤ ሰዎች ሰላም ሰፍኖ በተረጋጋ መልኩ እንዳያስቡ ቀውስ ይመረትላቸዋል። ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ እንደማይታወቅ በዓሉንም፣ ልደቱንም፣ በሚዲያ እያስጮሁ ያሳብዱታል። ይህ ወጣት የሰከነ ዕለት ለጃዋር የሚቀርብለት ጥያቄ ስለሚታወቅ … [Read more...] about ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ጃዋር መሃመድ ለድርጅቱ በጀት እንዲመደብና በቋሚነት እንዲረዳ ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ታወቀ። የጎልጉል የኦዲፒ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የድጎማ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ጃዋር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በኦዲፒ ላይ የጥላቻ ሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚሠራ መናገራቸውን አመልክተዋል። በተያያዘ ጃዋር የሚመራው ኦ.ኤም.ኤን. ለሸዋ ተወላጅ ኦሮሞዎች መድረክ እንደማይሰጥና ኦነግ በንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያም ሽፋን እንዲሰጥ እንደማይፈቅድ ተገልጿል። እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ጃዋር ለሚመራው “የትግል ሚዲያ” ከፍተኛ በጀት የጠየቀው ሚዲያው ለተገኘው ለውጥ ትልቁን ሚና ተጫውቷል በሚል ነው። ኦ.ኤም.ኤን. በትግሉ ወቅት የአንበሳውን ድርሻ በመጫወቱ የኦሮሚያ ክልልም ሆነ መንግሥት ሊደጉመው እንደሚገባ በተደጋጋሚ … [Read more...] about መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
“ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
“ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እንዲያስፈራ ተደርጎ ተሰርቷል” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሐምሌ 26/2011ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጠኛ ምህረት ሞገስ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። “ድንቁርና እና ድህነት እሳት ነው፤ አገር ያቃጥላል” በሚል ርዕስ የወጣውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አስፍረነዋል። በዚህ ጥያቄና መልስ አቶ ኦባንግ ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መልሶችን ሰጥተዋል፤ ጎሰኝነትን፣ ብሔረተኝነትን፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ወዘተ በመሳሰሉ ርዕሶች ላይ ሊነበብ የሚገባው መልሶችንና ዕምነታቸውን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን፡– የካናዳ የትምህርት ህይወት እንዴት … [Read more...] about “ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው። ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል የጅምላ ጥሪ ነበር። መረጃው የነፍስ ጉዳይ በመሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ክፉኛ ናጣቸው። ይህንን አሸባሪ መረጃ ለመከላከል የፓሪስ አካባቢ ኃላፊዎች መግለጫ እንዲሰጡ አስገደዳቸው። በመሆኑም አርብ ሐምሌ 12፤ 2011 (ጁላይ 19) ተመረዘ የተባለው ውሃው እንደተባለው እንዳልተመረዘና ለመጠጥም ቢሆን ምንም የማያሰጋ መሆኑን አስረግጠው ተናገሩ። ይህ የሐሰት መረጃ ፓሪስን … [Read more...] about የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”
አገራችን ከህወሓት አፋኝ የግፍ አገዛዝ ወጥታ በለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች። ሆኖም በአፋኙ ዘመነ ወያኔ እንኳን ሆኖ በማያውቅ መልኩ በአሁኑ ጊዜ አገራችንን እያፈረሰ የሚገኘው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው የሃሰትና የፈጠራ ዜና ነው። ለዚህ ደግሞ በርካታ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ቀንተሌት ተግተው የሚሠሩ “የሳይበር ወታደሮች” ተመድበዋል። እነዚህ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በትጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ዓላማቸው መረጃ ማዛባት፤ የሃሰት መረጃ መበተን፤ የሚወጡ መረጃዎችን ማወዛገብ (ሕዝብ እውነቱንና ሐሰቱን እንዳይለይ ማድረግ)፤ ወዘተ ናቸው። ይህ በዕዝና ቁጥጥር የሚመራ ኃይል ዋና ትኩረት የሚያደርገው በለውጡ ዙሪያ ያሉትን አመራሮች ማጠልሸት፤ የሕዝብ ድጋፋቸውን ማምከን፤ ከተቻለም ሕዝብ እንዲነሳባቸው ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ረቂቅ ስልት በሚበትኑት መረጃ … [Read more...] about ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”
“ሥራ ፈላጊው” ገብረሕይወት አስማረ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሕገወጥ መልኩ ሲያዘዋውር ተያዘ
“ሥራ ፈላጊው” ገብረሕይወት አስማረ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሕገወጥ መልኩ ሲያዘዋውር ተያዘ። “ገንዘቡ የተያዘው ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገዳማ ከጠገዴ ወረዳ ሾርካ ንዑስ ወረዳ መፈተሻ ኬላ ላይ ነው” ብሏል ፖሊስ ለአብመድ በሰጠው መረጃ። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ምክትል ኮማንደር አስማማው ካሴ እንደገለጹት አቶ ገብረሕይወት አስማረ የተባለ ተጠርጣሪ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በቦርሳ ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥ ሥር ውሏል። የተጠርጣሪው መታወቂያ “ሥራ ፈላጊ” የሚል መሆኑንም ነው ምክትል ኮማንደር አስማማው የተናገሩት፡፡ ግለሰቡም ከጎንደር ወደ ሁመራ ተጓዥ እንደነበር መናገሩም ተሰምቷል። ከ110 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በተጨማሪ የእንግሊዝ ፓውንድ መገኘቱንም ነው የወንጀል ምርመራ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቱ … [Read more...] about “ሥራ ፈላጊው” ገብረሕይወት አስማረ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሕገወጥ መልኩ ሲያዘዋውር ተያዘ










