• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!

October 24, 2019 09:39 am by Editor Leave a Comment

  • ማነው የዋሸው? ጃዋር? የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወይስ የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር?
  • መንግሥት በሕዝብ ገንዘብ ጥበቃ የሚያደርግለትን ጃዋርን በሌሊት የሚከብበት ምን ምክንያት አለ? ማለቴ ተከቦ የተቀመጠው በመንግሥት ጠባቂዎች አይደለም ወይ?
  • ለምን ጃዋርስ ተፈጠረ የተባለውን ነገር ሆን ተብሎ በመንግሥት የተቀነባበረና “እኔን ለማጥቃት የተፈጸመ ድርጊት ነው” አለ? ማለቴ ይህ ዓይነት ጥርጣሬ ካለው እንዴት በመንግሥት ታጣቂዎች እየተጠበቀ ዕንቅልፍ ወስዶት ያድራል? እንዴት እንዲህስ ሊያስብ ይችላል? ወይስ ጠባቂዎቹን የራሱ አድርጓቸዋል?
  • ከመቼ ወዲህ ነው የመንግሥት ታጣቂዎች በመንግሥት ተመድበው ሳለ ራሱ መንግሥት፤ ለዚያውም እንደ ጃዋር አገላለጽ ዋናው ኮማንደር ለቃችው ውጡ ሲላቸው እንቢ ሊሉ የቻሉት? ከመንግሥት ይልቅ ታዛዥነታቸው ለጃዋር ያደላ ነው ማለት ነው? በዚህ ዓይነት መንግሥት በሌሎች ሥፍራዎች ያሉትንስ ወታደሮች ማዘዝ ተስኖታል? ከመቼ ወዲህ ነው መንግሥት የመደበው ፖሊስና ወታደር ትዕዛዝ የሚቀበልበትን ሰዓት የሚመርጠው? ምነው ስንቱን በእኩለ ሌሊት ቤቱን ሰብረው እያዳፉ ይወስዱ የለምንዴ?
  • ይሄ ትእዛዝ ሰጠ የተባለው ዋና ኮማንደር ማን እንደሆነስ አይታወቅም ወይ? ከታወቀስ መንግሥት እንዴት አላውቅም አለ?
  • የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የግል ጥበቃዎችን ስናነሳ ቆይተናል ብለው ቀድሞም የተወሰነ ነገር መሆኑን ገልጸዋል፤ በጃዋር ላይ ግን ይህ ትዕዛዝ አልተሰጠም ካሉ ታዲያ ማን አዘዘ? ለምንስ ከተወሰነ በጃዋር ላይ ቀድሞ ሳይፈጸም ቀረ? ወይስ ትዕዛዝ ተላልፎለት ጭለማን ተገን ለማድረግ አድፍጦ ይጠብቅ የነበረ የመንግሥት አካል ነበር?
  • አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የመንግሥት የደህንነት ባለሥልጣን ድርጊቱ በሌሊት መፈጸሙ ልክ ባይሆንም ትእዛዙ ግን ቀድሞ መሰጠቱን ከተናገሩ ክፍተቱን የሚጠቀም ድብቅ ኃይል በመንግሥት ውስጥ መኖሩን አያሳይም ወይ?
  • የአቶ ሽመልስ ይቅርታስ መነሻው በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ ስህተት ነው ከሚል ነው? ወይስ በሌሊት መፈጸሙ? ጥበቃው ይቀጥልልሃልን ምን አመጣው? እንዲያ ከሆነ ለምን የመንግሥት አካላት እርስ በርሱ የሚጋጭ መግለጫ መስጠት አስፈለጋቸው?
  • ጃዋርስ የተፈጠረውን ነገር ለመንግሥት ባለሥልጣናት በተለይም ከኦዴፓ ሰዎች ጋር ካለው ቅርበት አንጻር ችግሩን በውስጥ መስመር ከእነሱ ጋር መነጋገር እና መፍታት እየቻለ ለምን በማህበራዊ ድረ ገጽ ለደጋፊዎቹ የድረሱልኝ ጥሩ አቀረበ? አቅሙን ሊያሳይ? ወይስ በፍርሃት ከመደናበር?
  • ጃዋር ቤት አካባቢ ደረሰ የተባለው ከበባ ምሽቱን ከሆነ የተፈጸመው ለምን ፖሊስና የመንግሥት አካላት ሌሊቱን ሁኔታውን በማረጋጋት ሕዝቡ ወደ አደባባይ ሳይወጣ በፊት አፋጣኝ ምላሽ አይሰጡም ነበር? የአቶ ሽመልስ ካመሻሸ መግለጫ መስጠት ምን ይሉታል? ከተበጠበጠ በኋላ ማንን ሊያረጋጉ ነው?
  • በሕዝቡ መካከል የእርስ በርስ ግጭት እንዲነሳ፣ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት ማነው ተጠያቂው?
  • መንግሥት በምን ምክንያት ነው ኪሱ በዶላር ላበጠ ሰው ከድሃ ሕዝብ በተገኘ የግብር ገንዘብ ደሞዝ እየከፈለ ለጃዋር ለዚህን ያህል ጊዜ ጥበቃ የሚመድበው?
  • ጃዋር በቅርቡ ለህወሃት ያቀረበው የአጋርነት ጥያቄ፣ በLTV ቀርቦ ዐቢይ ላይ ያንጸባረቀው አቋም እና ድንፋታ፣ የጃዋር የድረሱልኝ ጩኸት እንዳሰማ ህወሃት በመግለጫ አለሁልህ ማለቷ ብዙዎች እንደሚሉት የተጠነሰሰ ነገር ይኖር ይሆን? ክስተቱ ከዐቢይ የውጭ ጉዞ ጋርስ ይገናኙ ይሆን? ተደጋግሞ እንደተስተዋለው በአገሪቱ የተከሰቱ ዋና ዋና ሰበር ዜናዎች ዐቢይ እግሩ ወጣ ማለቱን ተከትለው የሚመጡ ስለነበሩ ነው። እንግዲህ የእኔ አዕምሮ ውስጥ እነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ እየተንገዋለሉ አብረውኝ ያድራሉ። ለተጎዱት ሰዎች ከማዘን ባለፈ ምን ለማለት ይቻላል።

ከላይ የተዘረዘሩት ጥያቄዎች ምላሻቸው ምንም ይሁን ምን መንግሥት ግን በአገሪቱ ውስጥ የሕግ የበላይነት ለማስፈን የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። ሕዝቡም ለመብቱ ብቻ ሳይሆን ለሕግ አክባሪነትም አብሮ ሊቆም ይገባል።

ያሬድ ሃይለማርያም (የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule