ባልተረጋገጠ የዶክትሬት ማዕረግ ራሱን የፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ ሸልሞ የሚጠራው ጸጋዬ አራርሣና ጓደኞቹ በቀጣሪያቸው ጃዋር መሃመድ መካከል የነበረው ውል መፍረሱን ራሱ ጸጋዬ ይፋ አደረገ። ጃዋር ያልተለመደ ተግባር እንዳላደረገ በቅርብ የሚከታተሉት ይመሰክራሉ። በተለምዶ በእንግሊዝኛው “down under” ወይም “እንጦሮጦስ” ተብሎ ሊጠራ ከሚችለው አውስትራሊያ ያለማቋረጥ በጥላቻ የተሞላውን መርዝ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያስተላልፍ ነው። ያለመታከት በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በኦሮሚኛ ይጽፋል፤ በማንኛውም ሚዲያ ከተጠራ እምቢ ማለትን አያውቅም፤ በተለይ ጸረ-ኢትዮጵያ አቋም ባለው ሚዲያ ላይ ደጋግሞ ቢቀርብ አይጠግብም፤ ከጃዋር መሃመድ ጋር የገጠመው አገርንና ሕዝብን ሊያድን ለሚችል ትልቅ ዓላማ ሳይሆን በጥላቻ ሰላምና ዕረፍት ያጣችውን ነፍሱን በበቀል ለማርካት ነበር። ጸጋዬ ረጋሣ አራርሣ ይባላል፤ … [Read more...] about ውሉ ፈርሷል
omn
ጃዋር ዕቁብ በልቶ ከጨዋታው ወጣ – “አበደን” ተተገበረ
በተለያየ የቅጽል ማዕረግ የሚሞሸረው ጃዋር መሐመድ “ስለቀጣዩ የፖለቲካ ሂደትና አዲስ ስትራቴጂ” ለመነጋገር አዲስ አበባን ሲለቅ በምርጫ እንደሚሳተፍ ለሚከተሉት ሁሉ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትር” በሚል ደጋፊዎቹንና እየለመነ አበል የሚሰጣቸው የሚዲያ ባለሟሎቹ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል። አዲስ ፓርቲ ያቋቁም ወይም ካሉት ፓርቲዎች ጋር የመቀላቀል ሃሳብ እንዳለው ለጊዜው እንዳልወሰነ፣ ነገር ግን ወደ ምርጫ የመግባቱ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ ጃዋር ያስታወቀው ከምርጫው በፊት የድምጽ ስሌትን በማስላት እንደሆነ በይፋ አስታውቆም ነበር። በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ በካናዳ፣ በኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ጀርመንና እንግሊዝ የቅስቀሳ ዘመቻውንና የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባሩን ካከናወነ በኋላ ለጀርመን ድምጽ በሰጠው ቃለ ምልልስ ወደ ምርጫ ለመግባት አለመወሰኑን … [Read more...] about ጃዋር ዕቁብ በልቶ ከጨዋታው ወጣ – “አበደን” ተተገበረ
ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“… ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም አንድ ጎረምሳ ልንለው እንችላለን። ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ በመሆኑ የጃዋር ሚዲያ የተመዘገበው በዚህ ጎረምሳ ስም ነው። ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚቀመጠው በዚሁ ልጅ ስም ነው። መኪኖችና አንዳንድ ንብረቶች የሚገዙትም በዚሁ ስም ነው። ይህ ጎረምሳ አዲስ አበባ እጅግ መንዛሪና በከፍተኛ ቅንጦት እንደሚኖር የሚያውቁት ነገረውኛል። የቄሮ አካልም አልነበረም። ቄሮ ከድል በኋላ ቤቱ ሲመለስ የጠበቀው ማሳውና መደቡ ሲሆን እነ ጃዋርና ስማቸውን የሚጠቀሙባቸው ጎረምሶች በሚሊዮኖች እየረጩ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይሸምታሉ፤ ንብረት ያከማቻሉ፤ ሰዎች ሰላም ሰፍኖ በተረጋጋ መልኩ እንዳያስቡ ቀውስ ይመረትላቸዋል። ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ እንደማይታወቅ በዓሉንም፣ ልደቱንም፣ በሚዲያ እያስጮሁ ያሳብዱታል። ይህ ወጣት የሰከነ ዕለት ለጃዋር የሚቀርብለት ጥያቄ ስለሚታወቅ … [Read more...] about ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ጃዋር መሃመድ ለድርጅቱ በጀት እንዲመደብና በቋሚነት እንዲረዳ ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ታወቀ። የጎልጉል የኦዲፒ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የድጎማ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ጃዋር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በኦዲፒ ላይ የጥላቻ ሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚሠራ መናገራቸውን አመልክተዋል። በተያያዘ ጃዋር የሚመራው ኦ.ኤም.ኤን. ለሸዋ ተወላጅ ኦሮሞዎች መድረክ እንደማይሰጥና ኦነግ በንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያም ሽፋን እንዲሰጥ እንደማይፈቅድ ተገልጿል። እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ጃዋር ለሚመራው “የትግል ሚዲያ” ከፍተኛ በጀት የጠየቀው ሚዲያው ለተገኘው ለውጥ ትልቁን ሚና ተጫውቷል በሚል ነው። ኦ.ኤም.ኤን. በትግሉ ወቅት የአንበሳውን ድርሻ በመጫወቱ የኦሮሚያ ክልልም ሆነ መንግሥት ሊደጉመው እንደሚገባ በተደጋጋሚ … [Read more...] about መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ




