የምሁር መሃይም - ተባይ አላዋቂ፤ የመሃይም ኩፍስ - አስመሳይ አዋቂ፤ የጅብ ባለ ጊዜ - ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤ ያንበሳ ልክስክስ - ልፋጭ የሚያላምጥ የቁራ ዕርግብ መሳይ - ሠላምን አብሳሪ፤ የፈረስ አዝጋሚ - የግመል ሰጋሪ፤ ንጹህ ሰው ታሳሪ - በፈጠራ ወንጀል፤ ፍርደ ገምድል ዳኛ - ፈራጅ በቂም በቀል፤ የባዕድ ባለቤት - የነባር ባይተዋር፤ ሥልጡን ሥራ ፈቶ - ሞያ ቢስ ሲገብር፤ ልማድ ሆኖ ቀረ - አቀርቅሮ መኖር፤ በተወሇድንባት በጦብያ ምድር :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጀግና ውለጅ እባክሽ !
Right Column - Primary Sidebar
ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
እሁድ እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። … [Read more...] about መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?” ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም... የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።” እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤ ጨዋታውም ተቀየረ። “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን.... የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ … [Read more...] about ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ባለፈው እሁድ ትንሽ ትልቅ፣ ወንድ ሴት፣ ከተሜ ገጠሬ፣ ሳይል የጎንደር ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ ከተማዋን ባጨናነቀ መልኩ የህወሓት አገዛዝ የፈጠረውን የሽብርና የፍርሃት አጥር ሰብሮ በመውጣት የተቃውሞ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ አሰምቶ ወደቤቱ ተመልሷል። ምንም እንኳን አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ማናቸውንም እርምጃዎች ቢወስድም፣ ግፍ የበዛበት፣ የቆረጠና የተባበረን ሕዝባዊ ማዕበል የሚመክተው አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለምና ከፍተኛ ጨዋነት በተሞላው መልክ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰምቷል። በዕለቱ ካስተጋባቸው መፈክሮች ውስጥ "በኦሮሚያ የሚደረገው የወገኖቻችን ግድያ ይቁም" የሚለው የጎንደር ሕዝብ ምንጊዜም በኢትዮጵያዊነትና በሀገር አንድነት ላይ ያለው የሚታወቀውን ጠንካራ አቋሙን ያሳየበትና የትግል አጋርነቱን በግልጽ ያንጸባረቀበት ነው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የሕዝብ … [Read more...] about ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ከሰልፉ በኋላስ ….?
ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን እንደ ዴሞክራሲያዊ መብት በመውሰድ የትኛውም ወገን በሚፈልገው ጉዳይ አቋሙን ለመግለጽ ሰልፍ ለማድረግ ‹‹ማሳወቅ››ብቻ እንደሚጠበቅበት ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ከዚህ እጅጉን ያፈነገጠ በመሆኑ የጎንደሩ ደማቅ ሰልፍ የተከናወነው ከእውቅናው ውጪ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ‹‹እውቅናውን ››ባልቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የታየውን የህዝብ ጨዋ ድርጊት በመንተራስ ‹‹ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነው››ወዘተ በማለት ሰልፉን ‹‹እውቅና በመስጠቱ የተደረገ ››ለማስመሰል ካድሬዎቹ በሶሻል ሚዲያዎች የሚያደርጉትን መንፈራገጥ እውነታውን በመግለጽ ማስቆም ይገባናል፡፡ ሰልፉ ከኢህአዴግ እውቅና ውጪ መደረጉ በራሱ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ህዝብን ከጀርባው … [Read more...] about ከሰልፉ በኋላስ ….?
አንድ ህዝብ አንድ ሀገር!
ሰው ነፃነት ይፈልጋል። ነፃነት ላለመፈለግ ራሱ ነፃነት ይጠይቃል። ስለዚህ ነፃነቱን የሚቃወም አይኖርም። ምክንያቱም ነፃነትን በራስ መቃወም በራሱ ነፃነት ነው። ሰው ነፃ ለመሆንም ላለመሆንም ነፃ መሆን አለበት። ሰው ነፃ ላለመሆን የመወሰን ነፃነት አለው። ዋናው ጉዳይ ዉሳኔው የራስ መሆን አለበት፤ የሌላ አካል ጣልቃ ገብነት ሊኖረው አይገባም። ነፃነት የሰው ነው፤ የራሳችን ሃብት ነው። በሌሎች ጣልቃ ገብነት ሊገደብ ግን ይችላል። ስለዚህ ነፃነታትችን ከፈለግን መጠበቅ ይኖርብናል። ነፃነታችንን ለመጠበቅ ፈፃሚ ተቋም ያስፈልጋል። ፈፃሚ ተቋም ወይ ስርዓት የሚኖረው መንግስት ሲኖር ነው። መንግስት የሚኖረው ሀገር ሲኖር ነው። ሀገር የሚኖረው ህዝብ ሲኖር ነው። የምንፈልገው ነፃ ህዝብ ነው። ነፃ ህዝብ የሚኖረው ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖር ነው። ዴሞክራሲያዊ መንግስት የሚኖረው የዴሞክራሲ … [Read more...] about አንድ ህዝብ አንድ ሀገር!
በወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ ክስ ተመሠረተ
* ዐማራ ነኝ ማለታቸው እና በአውሮፕላን የተጓዙበት ቲኬትም በወንጀል ማስረጃነት ቀርቧል የትግራይ ክልል የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎችና የማኅበረሰብ አባላት ላይ የመሠረተው ክስ ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ ሆኗል፡፡ የትግራይ መንግሥት በ34 የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ የመሠረተው ክስና ማስረጃ ብሎ ያቀረበው ባለ 250 ገጽ የትግርኛ ድርሰት በግልጽ እንደሚያሳየው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ‹‹እኔ ዐማራ ነኝ›› ማለታቸው፣ የተለያየ ጊዜ ለሚመለከታቸው አካላት ማመልከቻዎችን ማስገባታቸው፤ በባንክ ገንዘብ ማንቀሳቀሳቸው ብሎም አንደኛው ተከሳሽ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን መጓዙ በወንጅል ከተከሰሱባቸውን የወንጀለኛነታቸው ማስረጃ ሆነው ቀረበዋል፡፡ በምስክርነት በዳንሻና በአካባቢው በሠፈራ የመጡ ትግሬዎችና የሕወሓት አመራሮች ተዘርዝረዋል፡፡ … [Read more...] about በወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ላይ ክስ ተመሠረተ
THE MASSACRE OF CHRISTIANS IN THE CITY OF GONDAR: AN UPDATE
It is to be remembered that scores of innocent church-goers who were on penance and prayer at Adebabay Eyesus church in Gondar were massacred in cold blood by the Tigrean army of the EPRDF . It was then reported that 65 people were killed and around 300 wounded. The Tigrean minority government has tried to water down or downplay the scale of the massacre and has even tried to mislead the world community regarding the massacre of Amharic speaking Christians in the historic Ethiopian city of … [Read more...] about THE MASSACRE OF CHRISTIANS IN THE CITY OF GONDAR: AN UPDATE










