ኢትዮጵያ እመ-መከራ የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ መውደቅማ ነበር ያባት እንደ ያሬድ እስከ ሰባት እንደ በላ ብላቴና፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ… አጤ ካሌብ የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባንድ ወቅት በቅድመ-እስልምና የመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ባንድ ያይሁድ ገዥ መዳፍ ስር መማቀቃቸው አስቆጥቶት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ተበቅሎላቸዋል። የዛሬውን አያድርገውና፣ እንኳን ለቤት ለጎረቤት ጥቃት የሚቆረቆር ንጉሥ ማፍራት ችለን ነበር፤ አንኳን ለቤት ለጎረቤት እርዳታ የሚበቃ ጉልበት ማካበት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ጊዜ ከካሌብነት ወደ ከልብነት ደረጃ አውርዶናል። (“ከልብ” በግዕዝ ውሻ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዘይቤ አንድ ሰው ያለ ካሳ ያለ ጉማ ደሙ ፈሶ ሲቀር ደመ ከልብ ሆነ ይባላል)። አቅመ-ቢስ ሕዝቦች በጉልቤ ሕዝቦች መዳፍ … [Read more...] about ከካሌብነት ወደ ከልብነት
Left Column
“ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
ሰውየው ያገባት ሚስቱ ቤተሰቦቿ ሃብታሞች ነበሩ። እሱ ደግሞ መናጢ የሚባል ደሃ ነበር። አንድ ቀን የማይቀረው ሞት የሚስቱን አባት ነጠቀና ቀብር ወጡ። አስከሬን እየተከተሉ ሲያለቅሱ ባል ሚስቱ ጎን ሆኖ ልክ እንደሷ "አባቴ አባቴ" በማለት ያለቅስ ጀመር። ሚስትም " የት የወለደህን ነው አባቴ የምትለው" በማለት አፍታ ወስዳ ባሏን ገሰጸችው። ባል ለቅሶውን ቀየረና "አባቷ፣ አባቷ …” በማለት ያስነካው ጀመር። ይህን ጊዜ ሚስት አሁንም ለቅሶዋን ቆም አድርጋ "የበላኸው ጨማ፣ የጠጣኸው ጠጅ አያንቅህም? አባቷ አባቷ የምትለው" አለችው። ባልም ደንግጦ ላፍታ ዝም በማለት ካሰበ በኋላ "አረ እኔስ ጨነቀኝ፣ አረ እኔስ ጨነቀኝ … ” በማለት እያለቀሰ የባለቤቱን አባት ሸኘ። ይህ አጠር ተደርጎ የቀረበ የቀድሞ ምሳሌ ነው። ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ይወዳሉ። አገራቸውን በልጅ፣ በሚስት፣ በእናት፣ … [Read more...] about “ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉት 24 ተከሳሾች ክስ መሰማት ጀመረ
የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል። ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት … [Read more...] about በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉት 24 ተከሳሾች ክስ መሰማት ጀመረ
የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው። በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው። ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው። ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ … [Read more...] about የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?
የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!
ዛሬ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመ አንድ ዓመቱ ነው። ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ የደገፉን፣ ያበረታቱን፣ አስተያየት በመስጠት ያረቁንና በመድረካችን የተሳተፉ ያሉትን ያህል የምንሰራውን ስራ ለመቆጣጠር፣ የተመሰረትንበትን ግልጽ መስመር ለማስቀየር የሞከሩና ጨዋነት በጎደለው መልኩ የተዛለፉም አጋጥመውናል። ለሁላችም እንኳን ለአንደኛው ዓመት አደረሰን!! “ወፌ ቆመች በሉን" በማለት ከዓመት በፊት የሚዲያውን ሰፈር በአሃዱ ብለን ከተቀላቀልንበት ጊዜ አንስቶ የሰራነውን ስራ በጥሞና ለመመልከት ሞክረናል። ሌሎች ሚዲያዎችንና ብሎጎችንም ዳሰናል። የራሳችን ደካማ ጎን ስንፈትሽ እግረ መንገዳችንን ዙሪያችንን ስንቃኝ የሚዲያ ተሃድሶ (ሪፎርም) አስፈላጊ እንደሆነ ተረድተናል። አምነናል። "መቼ" ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ዛሬ፣ አሁን፣ አሁኑኑ የሚል ነው። ድክመታችን ስንጀምር በዘረጋናቸው … [Read more...] about የ፩ኛ ዓመት መልዕክት – የሚዲያ ተሃድሶ ግድ ነው!!
የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
እርቅን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን ለማውረድ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ቁልፍ ሚና አላቸው። በር ዘግተው ይጸልያሉ። ያስታርቃሉ። ይገስጻሉ። ያስጠነቅቃሉ። እንዲህ አይነት ለሌሎች ብርሃን ለመሆን የሚቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ያሏቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? በተቃራኒው የአምላክ ባሪያዎች፣ የየእምነታቸው ባሪያዎች፣ የምዕመናን መንፈስ መጋቢዎችና ጠባቂዎች፣ ወዘተ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ በይፋ ተነገረን። "በተገንጣይ ነጻ አውጪ" ስም እየተጠራጠረና እየተጸየፈ አገራችንን ከሚመራ ከሃዲ ድርጅት ጎን ለመቆም የሃይማኖት መሪዎች መነሳታቸው ለፈረደባት ኢትዮጵያና ለህዝቧ ከዚህ በላይ ሃፍረት የለም!! ችግሩ በውስጥም በውጭም ያለውን ይመለከታል። ይህንን ስንል ምክንያታችንን ህዝብ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። በሰማያዊውም ሆነ በምድራዊው ዓለም “መተፋት” አለ። የሃይማኖት አባቶችና … [Read more...] about የ“አምላካችሁ ባሮች” የሆናችሁ “ሰላማዊ ሰልፈኞች” ቅድሚ የምትሰጡት ለማን ነው?
የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!
“ከፍትህ ጋር ተቀነባብሮ ያልተፈጸመ ዕርቅ ዘላቂነት የለውም፤ ሁላችንም ሰላም እንዲሰፍን ተስፋ የምናደርግ ብንሆንም የምንመኘው ሰላም በፍትህና በሕግ ላይ የተመሠረተ መሆን ይገባዋል እንጂ በተገኘው ሁኔታ ይሁን የምንለው መሆን የለበትም” የቀድሞ የፊሊፕንስ ፕሬዚዳንት ኮራዞን አኪኖ፡፡ ወደ ሥልጣን የተጠጉና ለመጠጋት የሚያስቡ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዲሁም ሥልጣንን የተቆጣጠሩ ወዘተ በአገራችን ዕርቅ እንዲመጣ ሲመኙ፣ ሲያቅዱ፣ ፕሮግራም ሲያወጡ፣ ዲስኩር ሲሰጡ፣ … ቢያንስ አራት አሥርተ ዓመታትን አስቆጥረናል፡፡ “ብሔራዊ ዕርቅ፣ አገር አቀፋዊ ዕርቅ፣ … ” እየተባለ ሲነገር የሰማነው አሁን አይደለም፡፡ እስኪሰለቸን ሰምተናል። እርቅን ያህል ታላቅ ጉዳይ "የፖለቲካ ሃይሎጋ ሆ" አስመስለው ሲጫወቱበት የቆዩ፣ አሁንም ድረስ "ባገር ሽማግሌነት" ስም የሚቆምሩ የትውልድና ያገር "ችግር ቁልፍ … [Read more...] about የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!
ከእሁድ እስከ እሁድ
ነዋሪዎች በውሃ እጦት ተሰቃየን አሉ በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል፡፡ በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ መሆኑን የሚልፀው የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ፤ የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የአንዳንድ ሰራተኞች እንዝህላልነት፣ ለመንገድ ግንባታ የሚቆፈሩ ቧንቧዎች እንዲሁም በከንቱ የሚባክን ውሃ መብዛቱ የውሃ እጥረትን እንዳባባሱ ይናገራል፡፡ የአገሪቱ እንዲሁም የአህጉሪቱ መዲና በሆነችው ከተማ፣ ለዚያውም በሰለጠነ ዘመን በርካታ ነዋሪዎች የዝናብ ውሃን ደቅኖ ለማጠራቀም ሲሯሯጡና በጀሪካን ተሸክመው ውሃ ሲያመላልሱና የፎቅ ደረጃዎችን ለመውጣት ሲውተረተሩ ማየት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
እንዴት እንኑር!
… ለመሆኑ ከየት መጣን?…. ወዴት እንሄዳለን? …እንዴትስ እንኑር? የሚሉትን የፈላስፋውን ጥያቄ ስናነሳ፣ ግሪክ አገር አቴን ከተማ የዓለም ፈላስፋዎች ሰሞኑን ተሰብስበው “ስለ ዓለም ሁኔታ ይነጋገራሉ” ብለን አልገመትንም ነበር። እኛ በዚህ እትማችን ሰለ ዓለም ሳይሆን ስለ እኛው ስለ ራሳችን ችግር ነው አንዳንድ ነገሮቸን አንስተን ከግንዛቤ ውስጥ አስገብትን መለስ ብለን ለመመልከት የተነሳነው። “…እንዴት እንኑር? ” የሚለው ጥያቄ ሲሰነዘር የሚያስቆጣቸው ሰዎች እንደሌሉ ተስፋ እናደርጋለን። አንደንድ ጊዜ ከረጅም መላ-ምትና ግራ ከሚያጋቡ ጠማማ ጽንሰ-ሓሳቦች፣ ከቲዎሪ ዎች ይልቅ ቀላልና ጥሩ ጥያቄ ማቅረብ ፣ሌላውም ጎረቤት አገር ሆነ ራቅ ያሉ ሰዎች “እነሱስ እንዴት ይኖራሉ ?”ብሎ እራስን መጠየቅ ከብዙ ድካምና መነከራተት ያድናል። ግን ደግሞ ወደፊት ዘልቃችሁ እንደምታነቡት ፣ … [Read more...] about እንዴት እንኑር!
የሚፈራው መጣ!!
ኢትዮጵያችን ታማለች። ኢትዮጵያችን ተወጣጥራለች። ኢትዮጵያችን በአደገኛ መርዝ ተበክላለች። ኢትዮጵያችን ውስጧ ነፍሯል። ኢትዮጵያችን እየቃተተች ነው። ቆዳዋ ሳስቷል። የሚሰማትና የሚደርስላት ስላጣች የያዘችውን ይዛ ልትነጉድ ከጫፍ ላይ ነች። እናም ቅድሚያ ለመቀመጫ፤ ቅድሚያ ለእምዬ ኢትዮጵያ!! ማጣፊያው ሳያጥር ሁሉም መንገዱን ይመርምር!! ኢትዮጵያ በጭንቀት ጣር ውስጥ ስለመገኘቷ ማብራሪያ የሚጠይቁ ዜጎች ያሉ አይመስለንም። ምናልባት ሳያውቁ እየተፈረደባቸው ያሉ ህጻናት ካልሆኑ በስተቀር፤ ችግር ፈጣሪውም፣ የችግሩ ሁሉ ሰላባ የሆነው ህዝብ፤ ሁሉም ከበቂ በላይ መረጃ አላቸው። ኢትዮጵያ ህመሟ ወደ "ሚድን ካንሰርነት" መቀየር የሚችል ስለመሆኑ ዜጎች ያለ "ሰበር ዜና" ይረዱታል። የሚድን ስንል በቀላል አገላለጽ ችግር ፈጣሪው ኢህአዴግ፣ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት፣ የህወሃት አገልጋዮች፣ … [Read more...] about የሚፈራው መጣ!!










