• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!

August 24, 2013 02:52 am by Editor 3 Comments

“ከፍትህ ጋር ተቀነባብሮ ያልተፈጸመ ዕርቅ ዘላቂነት የለውም፤ ሁላችንም ሰላም እንዲሰፍን ተስፋ የምናደርግ ብንሆንም የምንመኘው ሰላም በፍትህና በሕግ ላይ የተመሠረተ መሆን ይገባዋል እንጂ በተገኘው ሁኔታ ይሁን የምንለው መሆን የለበትም” የቀድሞ የፊሊፕንስ ፕሬዚዳንት ኮራዞን አኪኖ፡፡

ወደ ሥልጣን የተጠጉና ለመጠጋት የሚያስቡ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዲሁም ሥልጣንን የተቆጣጠሩ ወዘተ በአገራችን ዕርቅ እንዲመጣ ሲመኙ፣ ሲያቅዱ፣ ፕሮግራም ሲያወጡ፣ ዲስኩር ሲሰጡ፣ … ቢያንስ አራት አሥርተ ዓመታትን አስቆጥረናል፡፡ “ብሔራዊ ዕርቅ፣ አገር አቀፋዊ ዕርቅ፣ … ” እየተባለ ሲነገር የሰማነው አሁን አይደለም፡፡ እስኪሰለቸን ሰምተናል። እርቅን ያህል ታላቅ ጉዳይ “የፖለቲካ ሃይሎጋ ሆ” አስመስለው ሲጫወቱበት የቆዩ፣ አሁንም ድረስ “ባገር ሽማግሌነት” ስም የሚቆምሩ የትውልድና ያገር “ችግር ቁልፍ ተወናዮች” እንዳሉ ህዝብ ያውቃል። ለይቶ በስም ይጠራቸዋል።

በአገራችን ከትዳርና መሰል ማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ግጭቶች ሲከሰቱ ተጣዪ ወገኖችን ለማስታረቅ ሽማግሌዎች ይመረጣሉ፡፡ እነዚህ ሽማግሌዎች ተናግረው የሚያሳምኑ፣ ነገራቸው ተቀባይነት ያለው፣ ኅብረተሰቡ የሚያከብራቸው፣ ቃላቸው መሬት ጠብ የማይል፣ ከፍ ያለ የመንፈስ ልዕልና የተጎናጸፉ፣ የተከበሩ፣ እውነተኛና ዋንኛ ዓላማቸው በኅብረተሰቡ ዘንድ ሰላምና ዕርቅ የማስፈን ብቻ የሆኑ ናቸው፡፡

ይህንን ዓይነቱን አገራዊ ቅርስ ወደ ፖለቲካው በማምጣት ሙሉውን ሃሳብ ሳይሆን ቁንጽል የሆነውን “ሽምግልና እና ዕርቅ” የሚለውን ሃሳብ ብቻ በመውሰድ በርካታ የፖለቲካ ሰዎች የዕርቅን ሃሳብ ሲያራምዱ ቆይተዋል፡፡ እኛም እንጠይቃለን – ለምን አልተሳካላቸውም? መልሱ ቀላል ነው – የዕርቅንና የሽምግልና መስፈርትን ስለማያሟሉ ወይም ማሟላት ስላልቻሉ ነው!!

ሥልጣንና ወንበር በቀን ቅዠትና በሌት ሕልማቸው ዕረፍት የነሳቸው፣ ኅብረተሰቡ ሙሉ እምነት ሊሰጣቸው የማይችሉ፣ የማይታመኑ፣ ከዚያም አልፎ በተደጋጋሚ ቀይ ካርድ የተሰጣቸው፣ እውነትና ሐቅን ይዘው ሳይሆን ቂምንና በቀልን ቋጥረው የተነሱ፣ ሲናገሩ ሕዝብን ሊያሳምንና ሊያቀራርብ የሚችል ሃሳብ ሳይሆን የበለጠ የሚያራርቅና የሚያጨካክን መርዝ የሚረጩ፣ ላመኑበት ዕውነት እስከመጨረሻ የመቆም ወኔ ያላቸው ሳይሆኑ ከየቦታው ለሚወረወርላቸው ቁራሽ የተገዙና ኅሊናቸውን የሸጡ፣ ዕድሜያቸው ዓመታትን ከመቁጠር በስተቀር “ሽማግሌ” ተብሎ ለመጠራት ማዕረግ ያልበቁ፣ ተምረናል፣ አውቀናል፣ ተፈላስፈንበታል ቢሉም ሲናገሩ ግን አፋቸው ደም የሚሞላ፣ … ዝንተዓለም ዕርቅ፣ ብሔራዊ ዕርቅ፣ … እያሉ ቢሰብኩ እንዴት ለሽምግልናና ዕርቅ ሹመት ይበቃሉ? እንዴትስ ሕዝብ አመኔታውን ይሰጣቸዋል?

ስለዚህ የዕርቅ ሃሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ አልሆነም ብቻ ሳይሆን የምንለው መልዕክቱም በትክክለኛ ሰዎች አልተሰበከም፡፡ ወደ ሕዝብ ጆሮ አልደረሰም፡፡ ህዝብ እንዲሰማ አልተደረገም። ሕዝብ እንዲሰማ የተደረገውና የሚደነቁርበት “እንግዴ” የሆነ እርቅ በመሆኑ ችግርን ከማክረር የዘለለ መፍትሄ አላስገኘም። በጉቦ፣ አንጃ በመፍጠርና ድርጅትን በመሰንጠቅ የሚደረጉ መስማማቶች መካን ሆነው ቀርተዋል። ሽምግልናውን ጭምር ያቆሸሸው ኢህአዴግ ቀና ከሆነ አሁንም ተስፋ አለ። ሕዝብ አልተጣላምና!!

ከቀድሞው አለቃቸው በተለየ መልኩ መንፈሣዊ እንደሆኑ የተነገረላቸው ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያምም ሃሳቡን የገለጸን ሁሉ “አሸባሪ፣ አክራሪ፣ …” በማለት ሳይሆን ያነበቡት ቅዱስ መጽሐፍ ባስተማራቸውና አምነዋለሁ በሚሉት መልኩ ታሪክ በመሥራት የኢትዮጵያ ታዳጊ ለመሆን ጊዜው አላለፈባቸውም፡፡ ከአለቃቸው ሞት ብዙ የሚማሩት እንደሚኖር እናምናለን፡፡ ሕዝብ ተመርሮና፣ ስቃይ የዕለት ተዕለት ኑሮው በሆነበት በአሁኑ ወቅት ለማርገብ ያልሞከሩት ውስብስብ ችግር ማሰሮው ተሰብሮ ጂኒው ከወጣ በኋላ የገነቡት “ታላቅ የመከላከያ ሠራዊትም ሆነ የፌዴራል ኃይል” መልሶ ወደ ማሰሮው መመለስ አይችልም፡፡ እናም አቶ ሃይለማርያም ራሳቸውን ለመስዋዕት እስከማቅረብ ድረስ በመሔድ ኢትዮጵያ ላይ የረመጠውን ረመጥ ለማስወገድ የእርቅ ዋጋ እንዲከፍሉ ለማሳሰብ እንወዳለን። እሳቸውና የሚመሩት ኢህአዴግን ጨምሮ ሰላም የሚሹ በርካቶች አሉና እርቅን እንደሚቀበሉ ለማወጅ ይዘጋጁ። አሁን የቀረው አንድ መፍትሔ እርቅ ብቻ ነውና!!

ከላይ ከጠቀስናቸው ሌላ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ አሉ፡፡ የመንፈስ ልዕልናቸው እጅግ ከፍ ያለ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ መታመን የሚችሉ፣ የአገራቸውን ሰላምና ጸጥታ እንጂ ሌላ ዓይነት የሥልጣንም ሆነ የግልጥቅም የሌላቸው፣ የዕርቅን ሃሳብ ከልባቸው የሚያምኑና ተበድለውም እንኳን ለመጪው ትውልድና ለአገር ጥቅም ሲሉ በደላቸውን ውጠው ልባቸውን ለዕርቅ ክፍት ያደረጉ፣ በእርግጥ ሽማግሌ የሚለው ሥልጣንና ሹመት የሚገባቸው – በዕድሜ ስለበለጸጉ ሳይሆን ሃሳባቸው ጽዱ፣ አመለካከታቸው ቅን፣ ምኞታቸው ግልጽ የሆኑ የአገር ልጆች አሉ፡፡

እንዲህ ዓይነት ሰዎች በተቃዋሚው ጎራ ወይም በሃይማኖት ድርጅት ብቻ ሳይሆን በገዢው ኃይልም ውስጥ አሉ፡፡ “ከአነሳሳችን ኢትዮጵያን እንደዚህ ለማድረግ አይደለም” የሚሉና እስካሁን ከቁጭት ባላለፈ ምንም ሳያደርጉ የተቀመጡ ግን አጋጣሚ የሚጠብቁ አሉ፡፡ የሚደረገው ነገር ሁሉ ያቅለሸለሻቸውና መውጫውን የሚፈልጉ ወይም አስተማማኝ መውጫ ከሚያሳያቸው ጋር ለመሰለፍ ፍላጎት ያላቸው አሉ፡፡

በሁሉም ወገን ያለው ሚዲያ ሰክሮና ሕዝቡንም እያሰከረ ባለበት ባሁኑ ወቅት ዕድል ፈንታ ያልተሰጣቸው ቅን ሰዎች መኖራቸው ሊያስደንቀን አይገባም፡፡ የሃይማኖት መሪዎች ካድሬ በሆኑበትና ወንጌላውያን ለብጣሽ ዳቦ አዳሪ በሆኑበት ዘመን ኢትዮጵያ አሁንም ሃቀኛና ትሁት ሰዎች አሏት፡፡ ለእነዚህ ኢትዮጵያውያን የእኛም ጥሪ ከተደበቃችሁበት ውጡ! ለኅሊናችሁ ተገዙ! ለአገራችሁ የዕርቅን መፍትሔ በመተግበር ከዚህ በፊት ተሰርቶ ያልታወቀ ታሪክ ሥሩ! የሚል ነው፡፡ ለአገራችን የወደፊት ዕጣ የቀረን አንድ የመጫወቻ ካርድ ዕርቅ ነው፤ እንዳይባክን ማድረግ በዓላማው የሚያምኑና ሕዝብ የሚቀበላቸው ሽማግሌዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ሕዝብ እንደማይቀበላችሁ እያወቃችሁ እንደማንኛውም የፖለቲካ ፕሮግራምም ሆነ ተሞክሮ ዕርቅን በመሞከር ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ለመልከፍ የምትፈልጉ ሁሉ እስካሁን ያልተሳካላችሁ ለምን እንደሆነ በመመርመር ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ከማትደበቁት ህሊናችሁ ጋር በመስማማት ቀናውን ውሳኔ እንድትወስኑ ለመመወከር እንወዳለን።

እናንተ በተለያየ ምክንያት ራሳችሁን ደብቃችሁ ያላችሁ ለዚህ ክቡር ዓላማ በመነሳት አገራችሁን አድኑ፤ ኢትዮጵያን የዕርቅ ተምሳሌት አድርጓትና ደም መፋሰስን በየቀኑ የሚመኙላትን የውስጥና የውጭ ኃይሎች አሳፍሩ! በሽፍንፍን፤ በአዝሃለሁ – ተቀበል አካሄድ፤ ለሥልጣን ባተኮረ ድብቅ ዓላማ፣ … ሳይሆን በእውነትና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ ዕርቅ ለአገራችሁ አምጡ፡፡ እንደ አንድ የሚዲያ አካል ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣም ከጎናችሁ ይቆማል፡፡


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ®” አቋም ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Editorial Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. anoole wako says

    August 24, 2013 05:56 am at 5:56 am

    tekekelagna ena waktaw malekt naw ! Joro yalaw yesma ! Ayn yalaw yanbeb ! Lebona yalaw yasalasel !

    Reply
  2. koster says

    August 24, 2013 10:46 am at 10:46 am

    Do not expect peace from a puppet, the question is when will he be slaughtered by the home grown fascists.

    Reply
  3. gishay says

    August 27, 2013 07:09 am at 7:09 am

    Yes it is time for reconcilliation . hulum beashenafinet liweta yemichelew bezih menged bicha new . qenenet kale hagerachin be ereqe menged tedenalech . ethiopiawi meftehe bicha new yemiyadenen . golgul please be the mouth of this noble idea. thanks

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule