የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችለው ለሀገራቸው ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን እንዲወጡ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠየቁ። አቶ ኦባንግ ሜቶ በሀገራዊ አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል ዙሪያ ትላንት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል። “በሀገራችን በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለው ግጭት ባለፉት 27 ዓመታት ለኢትዮጵያዊ አንድነት ትኩረት አለመስጠታችን ነው፣ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የነገይቱ ባለራዕዮችን እየተፈታተነ ይገኛል” ሲሉ ገልጸዋል። ወደዚህች ምድር ብሔርን ምርጫ አድርጎ የመጣ ማንም እንደሌላ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ሰው ማየት የሚገባው ሰው መሆኑ እንጂ በዘርና በብሔር መሆን እንደማገባም አመልክተዋል። በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንጂ የዘር የበላይነት … [Read more...] about “በኢትዮጵያ የዘር የበላይነት ሳይሆን የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል” ኦባንግ ሜቶ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
News
ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
ቅዳሜ በህወሓት አስገዳጅነትና ተለማማጭነት አሁን በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ የመቃወም እንደምታ ያለው ሰልፍ ተጠርቷል። እስካሁን ድረስ በርካታ መረን የወጣ ሌብነት የፈጸሙ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶችን የጣሱና ሌሎች ተፈላጊ ወንጀለኞችን በትግራይ ደብቆ የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በኤፈርት አልባሽነት ቅዳሜ "ሰላማዊ" ያለውን ሰልፍ በመቀሌ፣ ትግራይ ጠርቷል። ሌብነትን እንቃወማለን ለማለትም በአንዳንዶች ዘንድ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” የተባሉ አነስተኛና ጥቃቅን ሌቦች ላይ ፍርድ አስተላልፏል። የመቀሌ ከተማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የሰልፉ አንዱ ዓላማ “ህገመንግሥቱ ይከበር” የሚል ነው ብሏል። ይህ በህወሓት አነጋገር ከአንቀጽ 39 ጀምሮ በርካታ ነገሮችን ሊያስብል የሚችል አገላለጽ፤ ህወሓት ከሁለት ዐሥርተ … [Read more...] about ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?
“አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” በማለት “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” (ኦዴግ) ODF የሚባል አዲስ ግንባር መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) ያቋቋሙት የቀድሞው የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የቀድሞውን ኦህዴድ የአሁኑን ኦዴፓን ተቀላቅለዋል። ከኦነግ ተገንጥሎ ኦዴግ የሆነው የሌንጮ ለታ ፓርቲ ኦዴፓን መቀላቀሉና በኢህአዴግና በግንቦት 7 ላይ የሚያስከትለው የፖለቲካ ተጽዕኖ ገና አልጠራም። ከዳውድ ኢብሣ ኦነግ ጋር እቀላቀላለሁ ያለው የመረራ ጉዲና ኦፌኮም መጨረሻው አልታወቀም። የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ ከብሪታንያ፣ ከስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት ላይ ስለ ኦዴግ ማብራሪያ የሰጡት ሌንጮ አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች … [Read more...] about ከኦነግ የተገነጠለው ኦዴግ ከኦዴፓ ጋር መቀላቀል ኢህአዴግን እና ግንቦት 7ን ወዴት ያመራቸዋል?
የህወሓት ግፍ በጥቂቱ የተገለጸበት የፍርድቤት ውሎ
በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘው ህወሓት (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ላለፉት 27ዓመታት በግፍ በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በሚገዛበት ጊዜ ለጥቅሙ ባሰማራቸው አረመኔዎች የተፈጸመው ግፍ ጥቂቱ ፍርድቤት ተነግሯል። ሪፖርተር ባወጣው የዜና ዘገባ መሠረት በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠርጥረው የተያዙት የህወሃት የደኅንነት አባላት በሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ መርማሪ ቡድኑ ሲያቀርብ ጥቂቱን ግፍ በዚህ መልኩ ገልጾታል። “… በጨለማ ቤት ውስጥ ለረዥም ጊዜ በማሰርና በመደብደብ ማሰቃየት፣ እግርና እጅ በሰንሰለት አስሮና ጣሪያ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ በኤሌክትሪክ ገመድ መግረፍ፣ በሙሉ አካላቸው ታስረው በደረሰባቸው ደብደባ አካላቸው ጎድሎ በዊልቸር፣ በዱላና በሰው ተደግፈው እስከሚሄዱ መደብደብ፣ ራቁታቸውን አስሮ ገንዳና ቆሻሻ ቦታ ውስጥ … [Read more...] about የህወሓት ግፍ በጥቂቱ የተገለጸበት የፍርድቤት ውሎ
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለውን የህወሓት ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያደረገው ኦሞት ኦባንግ ሞቷል
በወንበዴው የህወሓት ቡድን ትዕዛዝ 424 አኙዋኮችን የጨፈጨፈው ኦሞት ኡባንግ ኡሎም ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ መሞቱ ታውቋል። ከመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በመቀበል ለ424 የአኙዋክ ተወላጆች የግፍ ዕልቂት ተጠያቂ የነበረው ኦሞት ኦባንግ በስደት በሚገኝበት ፊሊፒንስ ሞቷል። የሞቱ ምክንያት ኤችአይቪ ኤድስ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ኦሞት ኦባንግ የዛሬ 15 ዓመት አካባቢ በታኅሳስ ወር ከህወሓት ሹሞች ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል ጭፍጨፋውን በፈጸመበት ወቅት የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ ነበር። ለዚህም ኢሰብዓዊ ድርጊቱ ሽልማት ይሆን ዘንድ የወንበዴው ህወሓት መሪዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾመውታል። ጋምቤላን እንደፈለገ ሲፈነጭባት የኖረው ኦሞት ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓም ጀምሮ ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ዜናዊ በላከው አስገምጋሚዎች ለሳምንት … [Read more...] about “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም” የሚለውን የህወሓት ትዕዛዝ ተፈጻሚ ያደረገው ኦሞት ኦባንግ ሞቷል
በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር 102.1 እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል። የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል። ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ … [Read more...] about በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
የ5ሺ 160 ዓመት እስር ፍርድ ለሳንቶስ ሎፔዝ
ጓቲማላዊው የቀድሞ ወታደር በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በተፈጸመ ጭፍጨፋ እጁ አለበት በሚል ከ5 ሺህ 160 ዓመት እስር ተፈረደበት። በፈረንጆቹ 1982 ጓቲማላ ውስጥ ዶስ ኤሬስ በተባለች ሀገር በተፈጸመ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በ36 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት አሳዛኙ አጋጣሚ ነው ተብሏል። የቀድሞው ወታደር ሳንቶስ ሎፔዝ በአሜሪካ ስልጠና የተሰጣቸው የጓቲማላ ካይበለስ ሃይሎች አባል እንደነበር ተገልጿል። ሎፔዝ በመንደሯ ከሞቱት ሰዎች መካከል በ171ዱ በእያንዳንዳቸው 30 ዓመት እስራት የተቀጣ ሲሆን በህይወት የተረፈች ሴት ልጅ እንድትገደል በነበረው ሚና ተጨማሪ 30 ዓመት ተቀጥቷል። በጓቲማላ ህግ መሰረት ማንኛው ግለሰብ በእስር ከተቀጣ ከፍተኛው ቅጣት 50 ዓመት ነው። ከአውሮጳውያኑ 1960-1996 በቆየው የ36 ዓመታት የጓቲማላ … [Read more...] about የ5ሺ 160 ዓመት እስር ፍርድ ለሳንቶስ ሎፔዝ
ሌብነት፣ ውንብድ፣ ግፍና ውርደት ልክ እንደ ጌታቸው
“የእኔ ሀብት ሰውነቴ ብቻ ነው የተመዘገበው ሀብት የእኔ አይደለም” ክንፈ ዳኘው የያሬድ ዘሪሁን አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን፣ በተጠረጠሩበት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ፈጽመውታል የተባለ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ። አቶ ያሬድ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር ሲገባቸውና ሕዝብ እንዲያገለግሉ የተሰጣቸውን ሥልጣን ወደ ጎን በመተው፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ከነበሩት አለቃቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚቀበሉትን ትዕዛዝ ለበታቾቻቸው ኃላፊዎችና ሠራተኞች በማስተላለፍ፣ ዘግናኝና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውንና እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ … [Read more...] about ሌብነት፣ ውንብድ፣ ግፍና ውርደት ልክ እንደ ጌታቸው
አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው ብለውታል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ገብተዋል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኝት የጎንደርና አካባቢውን ታሪካዊ ቦታዎች ለመመልከትና በባህር ዳር ውበት ለለመሰጥ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ኢሳያስ በተደጋጋሚ በትግራይ አመራር ላይ ካሉት የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጥያቄ ችላ በማለት ከህወሓት ጋር … [Read more...] about አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼
ከጥቂት ቀናት በፊት በደሴ ከተማ አንድ የሰባት አመት ታዳጊ ለቀናት ከጠፋች በኋላ፤ ተገድላ መገኘቷን ተከትሎ የተቆጡ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። በወቅቱ ታዳጊዋ ከመገደሏ በፊት መደፈሯን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተያያዘ ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል። አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ። በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል። የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ … [Read more...] about የሰባት አመቷ ህፃን በፀሎት ብርሃኑ – ተሰርቃ፣ ተደፍራ በግፍ የተገደለች‼










