• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በኢትዮጵያ የዘር የበላይነት ሳይሆን የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል” ኦባንግ ሜቶ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ

December 23, 2018 07:43 pm by Editor 1 Comment

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችለው ለሀገራቸው ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን እንዲወጡ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠየቁ።

አቶ ኦባንግ ሜቶ በሀገራዊ  አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል ዙሪያ ትላንት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

“በሀገራችን  በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለው ግጭት ባለፉት 27 ዓመታት ለኢትዮጵያዊ አንድነት ትኩረት አለመስጠታችን ነው፣ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የነገይቱ ባለራዕዮችን እየተፈታተነ ይገኛል” ሲሉ ገልጸዋል።

ወደዚህች ምድር ብሔርን ምርጫ አድርጎ የመጣ ማንም እንደሌላ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ሰው ማየት የሚገባው ሰው  መሆኑ እንጂ በዘርና በብሔር መሆን እንደማገባም አመልክተዋል።

በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንጂ የዘር የበላይነት ሊኖር እንደማይገባ ጠቁመው ኢትዮጵያ እንድትለወጥ እያንዳንዱ ዜጋ ከብሔር አመለካከት ነፃ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል።

“በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች የኢትዮጵያ እንጂ ተዋጽኦ አይደሉም፣ ደግሞ አንዳችን ያለአንዳችን መኖር አንችልም ስለዚህ ተማሪዎች የጥላቻ ሳይሆን የአንድነት ነፀብራቅ ልሆኑ ያገባቸዋል” ብለዋል።

በሀገሪቱ የተለያዩ ግጭቶች ቢኖሩም የዴሞክራሲ መሠረት እየተጣለ መሆኑን የገለጹት አቶ ኦባንግ የተፈጠረው በነፃነት የመናገር ዕድል  በመጠቀም ለሀገሪቱ አንድነት፣ ለሰላምና መቻቻል ሞጋቾች እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ባለቤት እንደመሆኗ ባለፉት ጊዜያት በአንድነት ሳይሆን በልዩነት ላይ ትኩረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

“ቀደምት አባቶቻችን በአንድነት ወግ ያደጉ በመሆናቸው የተለያዩ የሀገራችን ፈተናዎችን በድል ተወጥተው ለእኛ አስረክበዋል” ብለዋል።

ወደ ቀድሞ የአንድነት ታሪክ ለመመለስ የመሪነት ሚና መጫወት ያለባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ መሆናችንን መዘንጋት እንደሌለባቸውም አመልክተዋል።

“ብሔራዊ መግባባትና አንድነት ላይ ባለመሠራቱ በክልል የታጠሩ ነፃ አዉጪ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተፈጠሩ እንጂ ብሔራዊ አመለካከት ያላቸው ጥቂቶች ናቸው” ያለው ደግሞ በዩኒቨርስቲው የፕሮዳክሽን ምህንድስና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ግሩም አጅሬ ነው።

ተማሪ ግሩም እንዳለው የዘር ፖለቲካ ባመጣው ጠባብ አመለካከት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችሎ ለመኖር እየከበዳቸው ይገኛል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላምና መቻቻል አቶ ኦባንግ ገለፃ መስጠታቸው ራሱን እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ተናግሯል።

የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና የአራተኛ ዓመት ተማሪ ሪሐና ኑሩ በበኩሏ “ሀገራችን በዘርና በብሔር በሽታ የታመመችው ከእኛ የተነሳ ነው” ብላለች።

ሆኖም አቶ ኦባንግ በአንድነትና ሰላም ዙሪያ ያደረጉት ገለጻ በካምፓስ ህይወታችን አንድነት በመፍጠር ተባብረው ለመኖር እንደሚያግዝ ተናግራለች።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Belayneh sergoalem says

    January 13, 2019 03:33 pm at 3:33 pm

    I am what I have said justice ,justice ,justice before everything , everything with out justice is nothing !!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule