የክልሉ መንግስት ምላሽ ቢጠየቅም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ትላንት አምስተኛ ቀኑ አልፏል በትግራይ ክልል የሕንጣሎ ወረዳ ነዋሪዎች በአዲሱ የአስተዳደር መዋቅር ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን ተቃውመዋል። “በአቅራቢያችን መተዳደር እንፈልጋለን” በማለትም ከመቀሌ ከተማ ወደሳምረ በሚወስደው ደንጎላት በሚባል አካባቢ መንገድ ዘግተው የክልሉ መንግስትን ምላሽ በመጠባበቅ አራተኛ ቀናቸውን ደፍነዋል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ የ“ወረዳችን ይመለስልን” ጥያቄ በማቅረብ ከህብረተሰቡ በተወከሉ ነዋሪዎች አማካኝነት ላለፉት ስድስት ወራት ያክል ወደክልል አስተዳደር ተመላልሰው ቢጠይቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪ አቶ መሀሪ ገብረ፤ “ህብረተሰቡ ሌላ ሃሳብ የለውም፣ ዓላማው ወደክልሉ ቢሮ … [Read more...] about አምስተኛ ቀኑን ያሳለፈው የሕንጣሎ ወረዳ ተቃውሞ ቀጥሏል
tigray
ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
ቅዳሜ በህወሓት አስገዳጅነትና ተለማማጭነት አሁን በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ የመቃወም እንደምታ ያለው ሰልፍ ተጠርቷል። እስካሁን ድረስ በርካታ መረን የወጣ ሌብነት የፈጸሙ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶችን የጣሱና ሌሎች ተፈላጊ ወንጀለኞችን በትግራይ ደብቆ የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በኤፈርት አልባሽነት ቅዳሜ "ሰላማዊ" ያለውን ሰልፍ በመቀሌ፣ ትግራይ ጠርቷል። ሌብነትን እንቃወማለን ለማለትም በአንዳንዶች ዘንድ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” የተባሉ አነስተኛና ጥቃቅን ሌቦች ላይ ፍርድ አስተላልፏል። የመቀሌ ከተማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የሰልፉ አንዱ ዓላማ “ህገመንግሥቱ ይከበር” የሚል ነው ብሏል። ይህ በህወሓት አነጋገር ከአንቀጽ 39 ጀምሮ በርካታ ነገሮችን ሊያስብል የሚችል አገላለጽ፤ ህወሓት ከሁለት ዐሥርተ … [Read more...] about ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው ብለውታል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ገብተዋል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኝት የጎንደርና አካባቢውን ታሪካዊ ቦታዎች ለመመልከትና በባህር ዳር ውበት ለለመሰጥ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ኢሳያስ በተደጋጋሚ በትግራይ አመራር ላይ ካሉት የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጥያቄ ችላ በማለት ከህወሓት ጋር … [Read more...] about አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?



