• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

November 24, 2018 05:33 am by Editor 1 Comment

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር 102.1 እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል።

የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል ነው ተብሏል።

ዘርፉ እየተለየ ምርመራ የማድረግና ተጠያቂዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የ100 ቀን እቅድ አውጥቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እየሰራ መሆኑን ተሰምቷል።

በዚህ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፌስቡክ ገጽ ላይ በተሰጠው የባለአንድ ገጽ ዕቅድ በአገራችን የተጀመረውን ለውጥ ዳር ለማድረስ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በፈፀሙ ሰዎች የሕግ ተጠያቂነት የማረጋገጥ፣ የታራሚዎችን መብት አያያዝ ማሻሻል፣ የይቅርታና ምህረት አሰጣጥ ሥርዓቱን በተሟላ መልኩ ለመተግበር፣ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ የሚታዩ የጥላቻ ንግግር ወንጀል ሕግ ማውጣትና መተግበር እንዲሁም ሕገ ወጥነት፣ ስርዓት አልበኝነትና የመንጋ ፍትህን ለመቆጣጠር ከአሁን በፊት ታይተው የማይታወቁ ህጎችን የማርቀቅና የማሻሻል ሥራዎችን አቅዶ ውጤታማ ለመሆን የሕግና የፍትህ አማካሪ ምክር ቤት በማጠናከርና የሰው ሀይል በማደራጀት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን ኅዳር 14፤ 2011ዓም መግለጫ የሰጡት አቶ ዝናቡ አስታውቀዋል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. መሀመድ says

    November 25, 2018 02:32 am at 2:32 am

    እጅግ በጣም አስደሳች የለውጥ ጅማሮ ነውና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።በተጨማሪ ወደ ክሊሎች፡ዞኖች እና ወራዳም ድረስ በተዋረድ መውረድ አለበት ምክንያቱም በየዩንቨርሲቲዎች ደህንነት በመሆን የመብት ጥያቄን የጠየቁ ተማሪዎች ደብዛቸውን ያጠፉ ማኒነታቸውን ደብቀው ዞኖች ወርደው ህዝብ ለህዝብ ሲያጋጩ የነበሩ ለምሳሌ የቀድሞው የሀላባ ዞን አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ኑር ሳሊያ በመቀሌ ዩንቨር በተመደበ ወቅት ብዙዎችን አሰውሩዋል ።በሚመረበት ዞን ትንሽዬ ከተማ ፌክ ISIS ፈጥሮ ሚስኪን ስረ አጥ ወጣቶችን ደካማ ወላጆቻቸውን ለመርዳት ከሚታትሩበት የቀን ሥራ ከሚሠሩበት ቦታ ISIS ነቸው በሚል አሳስሮ ቶርች አስደሪጉዋ ይህን በደል በመሸሽ የተሰደዱት ቁጥር ስፍር የላቸውም።የሀላባ ህዝብ ይህችን እስከፃፍኳት ደቂቃ ድራስ በፀራ ለውጥ ሀይሎች በመመራት ላይ ያለች ከተማ ናት።ከዝህ ቀደም የዶ/ር አብይ ን ምስል የያዛ ቲ ሸርት የለበሱትና ኮኮብ አልባ ባንድራ ያዛችሁ በሚል በወጣቱ ላይ የበቀል ዱላ በዘበት የፍትህ ያለህ!!!!’

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule