በጅዳ ቆንስላ ጸ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” የተሰኘው ቡድን ጽ/ቤቱ ለሕዝብ መሥራት ከሚገባው ጉዳይ በመውጣት በግለሰቦች ማንነት እና ሃይማኖት ላይ ጽንፈኛ አቋም እየያዘ መምጣቱ ታወቀ፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት “በመልካም አስተዳደር ሽፋን” ዙሪያ ይካሄዳል ተብሎ የተጠራው አሁን ካለው የከረረ ሁኔታ አኳያ ግጭት ያስነሳል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ በተለያዩ ሁኔታዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት “በመልካም አስተዳደር” ዙሪያ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ጥቂት የደቡብ ተወካይ ነን የሚሉ ግለሰቦች አማራውን በብሄር እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በሃይማኖት በመከፋፈል የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ ጅዳ እና አካባቢዋን ስጋት ውስጥ ከቷል። በተለይ እራሱን “ወገን ለወገን” እያለ የሚጠራው በአቶ ሰመሩ እና ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ የሚመራው የቆንስላ ቡድን የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በቆንስላው … [Read more...] about ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” ቡድን አፍራሽ ተግባሩ ቀጥሎበታል
“ማንነት እንጂ ብሔር የለኝም!” አቤል ዋበላ
". . . እኔ ማዕከላዊ በነበርኩኝ ጊዜ አንድ ቀን የተደበደብኩት ብሔርህን ተናገር በሚል ነው። እኔ አዲስ አበባ ነው ተወልጄ ያደኩት። እናትና አባቴ ከሁለት ብሔር ነው የመጡት አንድ ብሔር መርጬ እኔ የዚህ ብሔር አባል ነኝ የምለው ብሔር የለኝም . . . ብሔሮችን አልጠላም. . . እኔ ጥቅል ማንነት ነው እንጂ የሚገዛኝ የአንድ ብሄር ማንነት ታርጋ የግድ ሊለጠፍብኝ አይገባም . . . መጨረሻ ላይ ከመርማሪው ጋር ተማምነን ብሔር የለውም ብሎ ባዶ አድርጎት ነው የተለያየነው . . ." ከዞን 9 ጦማሪያን ውስጥ አቤል ዋበላ ከእስር ከተፈታ በኋላ ከSBS ራዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ የተናገረው። ቃለ ምልልሱን ለመስማት ይጫኑ። … [Read more...] about “ማንነት እንጂ ብሔር የለኝም!” አቤል ዋበላ
እኔ እንዳዳመጥኩት
መቼም ሰው ይናገራል። እኔ ደግሞ ጆሮ ፈጥሮብኛልና እሰማለሁ። የምሰማውና የማዳምጠው ግን ይለያያል። ባለፈው ሰሞን ቁጥር 00 ሰውዬ ሲናገሩ ሰማሁ፣ “የዛሬ አሥር አመት ከ80 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሥራ እናስይዛለን” ብለው ሲናገሩ ሰማሁ። እና አዳመጥኩ፣ “የዛሬ አሥር አመት ከ80 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሥራ እናስይዛለን፣ ምክንያቱም አሁን እየቀጠርናቸው ያለነው ቻይናውያን፣ ህንዳውያን፣ ብራዚላውያን፣ ወዘተርፈዋውያን . . . የዛሬ አሥር አመት ኢትዮጵያውያን ይሆናሉ፣ በቁጥርም ከ 80 ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ” ብዬ አዳመጥኩ። ያገሬ ህዝብ ደግሞ የቀን ሥራ እንኳን ሳይቀር እየተቀማ ለቻይና ሲሰጥበት፣ ተግቶ ይጸልያል። “የባሰ አታምጣ” እያለ። እኔ ደግሞ አዳምጣለሁ፣ “የባሰ አታምጣ”ን መሥማት ደከመኝ “የተሻለ አምጣ” የሚል ናፈቀኝ” ብዬ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላው ቁጥር … [Read more...] about እኔ እንዳዳመጥኩት
Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause (GAJEC)
DECLARATION BY THE INTERNATIONAL CONFERENCE ON JUSTICE FOR THE FASCIST ITALIAN WAR CRIMES COMMITTED AGAINST ETHIOPIA IN 1936-41 PREAMBLE 1.1 Taking into consideration the presentations and deliberations at the international conference which was held at the hall of the College of Medicine at Howard University on September 26, 2015; 1.2 Expressing the conference’s warmest appreciation to Howard University for having provided its hall free of charge and for its excellent hospitality as … [Read more...] about Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause (GAJEC)
Regarding heroes and Villains
If only I could have charged a penny for the many times my friends ask me 'what is new in Ethiopia' I would be a rich person by now. That is a very common question when Ethiopians meet. I always try to answer in a positive manner. It is not a simple matter trying to put a positive spin on a situation that by any stretch of the imagination does not give one a chance to embellish the truth no matter how hard one tries. I am not saying nothing good comes out of Woyane land. Stuff happen no matter … [Read more...] about Regarding heroes and Villains
ሸንጎ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግለውን አመራር መረጠ
በኦታዋ ካናዳ በተካሄደው ጉባኤ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2012 የተመሠረተውና የኢትዮጵያ የአንድነት ኃይሎች ትልቁ ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ (ሸንጎ) በዛሬው ዕለት ባካሄደው የምክር ቤት ስብሰባ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ድርጅቱን የሚመሩ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላትን መርጧል። በዚህም መሰረት ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴው አባላት ውስጥ ዶክተር ታዬ ዘገዬን፣ ሊቀመንበር ወይዘሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግደይ ዘርአጽዮንን ዋና ጸሀፊ እና አቶ መሐመድ ጀሚልን ምክትል ዋና ጸሀፊ አድርጎ መርጧል፡፡ የተቀሩት የኮሚቴው አባላት ደግሞ የተለያዩ የተግባር ኮሚቴወችን በኃላፊነት ይመራሉ። ሸንጎው በቅርቡ አጠቃላይ ጉባዔ በማካሄድ ኢትዮጵያችንና ሕዝቧ የሚገኙበትን ሁኔታ በጥልቅ ከመረመረ በኋላ ሀገራችን ከምትገኝበት አስከፊና አደገኛ የግፍ ሥርዓት ተላቃ … [Read more...] about ሸንጎ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግለውን አመራር መረጠ
“ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስም የኧርነስትና ያንግ የተሰኘውን የንግድ ሒሳብና ኦዲት ሥራ የሚያከናውን ኩባንያ ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ዘመድነህ ንጋቱ በኦባንግ ሜቶ ለዓምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አቤቱታ ቀረበባቸው፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለዓለምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ዋና የሥራ ኃላፊዎች ማርክ ዋይንበርገር እና ሮጀር ደንባር ጥቅምት 9፤2008 ዓም (October 20, 2015) በጻፉት ደብዳቤ የኩባንያው ሸሪክ አስተዳዳሪ አቶ ዘመድነህ ንጋቱ ኩባንያው ከቆመለት ዓላማ ውጪ በመንቀሳቀስ ከህወሃት ጋር በማበር ከሙያው ሥነምግባር ያፈነገጠ አካሄድ በመሄድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየበደሉ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ “ላለፉት 14 ዓመታት” ይላል ደብዳቤው … [Read more...] about “ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”
“ባቡር ይሄድበታል”
አቶ ማሞ፣ የዘመናይና የእስከዳር አባት፣ የወ/ሮ ከልካይ ባለቤት፣ አንድ ወፍጮ ቤት አላቸው። እህልም ይነግዳሉ። ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ እዚያው ገዝተው እዚያው የሚያስፈጩ ደምበኞች ሞልተዋል። አቶ ማሞ በሰፈሩ ተወዳጅ ናቸው። ተወዳጅ ያደረጋቸው ደግሞ ምርቃታቸው ነው። ምርቃቶቹ በቄንጥ የተደረደሩ ቃላት ሳይሆኑ 50 ኪሎ ጤፍ ላይ ሁለት ወይም ሶስት ኪሎ መጨመራቸው ነው። “እጅ አጠረኝ ...” ላለ ጎረቤት ደግሞ መልሳቸው፤ “ምን ችግር አለ! ሲያገኙ ይከፍላሉ ...” ነው። የተበጠሰ ቺንጋ እየቀየሩ፤ መፋቂያ የተሰኩባቸውን ጉራማይሌ ጥርሶቻቸውን በፈገግታ ብልጭ እያደረጉ። አቶ ማሞ ሃብታም አይደሉም። ድሃም አይደሉም። የሚያገኙት ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ይበቃቸዋል። ያቶ ማሞ መኖሪያ ቤትና ወፍጮ ቤት የተያያዘ ነው። አጥር ነው የሚለየው። ሌሊት ወፍጮ ቤቱ ሲዘጋ እንዳይላሉ የሚባለው፤ ቀኑን … [Read more...] about “ባቡር ይሄድበታል”
በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
ዘመን ፊትሽ ተከምሮ እየታዬ ስራሽ አምሮ እንቁጣጣሽ አንድ ብለሽ አርባ ድረስ እድሜ ቆጥረሽ እንደ ቤቶች የሳቅ ተውኔት እንደ ጨቤ ስካር ህይወት ሞት ራሱን ያሾፍሽበት ለምንድነው? በይ ንገሪኝ እባክሽን አደብቂኝ ባንቺው ቀዬ የተወለድኩ ፊደል በጄ እዛው የያዝኩ መስፍን ሜዳ የተራገጥኩ በጨበጣ ብይ ያስቆጠርኩ ቲቸር ታዬ ያስተማሩኝ ገብሬ ኩርኩም ያቀመሰኝ የሲሚንቶ ጭስ ያወዛኝ ቅዱስ ያሬድ ተሳልሜ ከሽፋ ቤት ተሰይሜ ያቶ ማሞን ኪኒን ቅሜ እዛው ኖሬ እዛው ያደኩ የቃጠሎው ቀን የተረፍኩ እኔ እማውቅሽ የማታውቂኝ የሰፈርሽ አንድ ስው ነኝ ይሄን ሁሉ ዘርዝሬልሽ ጥያቄዬን ስጠይቅሽ ዝም አትይም መቼም ከፍተሽ ፊት ለፊትሽ ተስፋሽ ሞልቶ እየታየ ዝናሽ ጎልቶ እንደጸደይ ባገር ፈክተሽ በህዝብ ፊት ደምቀሽ ታይተሽ በአዲስ አመት በንቁጣጣሽ በ´ለቱ ለት … [Read more...] about በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!
በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት ሰሞኑን ዕቅድ ብሎ ባወጣው ዘገባ ላይ ለዓመታት ሲወራለት የነበረው የድርብ አኃዝ ዕድገት እንደተደሰኮረለት እንዳልሆነ እንዲያውም ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን የሥራ አጥነት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ በከተማዎች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ችግር እየሆነ መምጣቱን ለራሱ ባመነበት የኢኮኖሚ ፕላን ላይ አትቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- መንግስት ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ • የኢኮኖሚ መዋቅሩ ከሳህራ በታች ከሚገኙ ሀገራትም ያነሰ ነው • የወጪ ንግድ ገቢ እና የገቢ ንግድ ክፍተት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል • ለውጭ ገበያ የቀረበው አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ሰሊጥና … [Read more...] about ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!










![ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2014/06/poor1-300x157.jpg)