ለሐጅ ጉብኝት የተጓዙ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ምዕመናን ትናንት ሚና-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ድንገት በመሞታቸዉ የሐገራት መሪዎችና የድርጅት ተጠሪዎች የሚያስተላልፉት የሐዘን መግለጫ፤ የሐይማኖት መሪዎች ፀሎት ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። በአደጋዉ 717 ሰዎች ሞተዋል፤ ከ800 በላይ ቆስለዋል። የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች የአደጋዉ ትክክለኛ መንሥኤ እንዲጣራ አዘዋል።ኢራን ግን ለአደጋዉ የሪያድ ነገሥታት ሐላፊነቱን እንዲወስዱ አሳስባለች።በሐጂ ጉብኝት ወቅት ተደጋጋሚ አደጋዎች ቢደርሱም በርካታ ሠዉ የሞተበት አደጋ ሲደርስ በሃያ-አምስት ዓመት ዉስጥ የትናንቱ የመጀመሪያዉ ነዉ። ከመካዉ ዓል-ሐራም እስከ ሞስኮዉ ካቴድራል፤ ከምሥራቅ ለንደኑ እስከ ካይሮዉ አል-አዝሐር፤ ከካምፓላዉ ቃዛፊ፤ እስከ እየሩሳሌሙ ዓል-አቅሳ፤ ከዓለም መሳጂዶች የሚንቆረቆረዉ ዱዓ፤ምልጃ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ከዋይት ሐዉስ እስከ … [Read more...] about የሐጃጆች ሞት
በትግራይ ድርቅ ህይወት እየቀጠፈ ነው!
* “ከብቶቻችሁን ሸጣችሁ ተገላገሉ” ህወሃት ለነዋሪዎች የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ትግራይ ድርቅ በአስከፊ ሁኔታ ህይወት እየቀጠፈ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለእንስሳትም ሆነ ለሰው ዕርዳታ መስጠት ገና ባይጀመርም በሚደረገው ዕርዳታ የመስጠት ዕቅድ ውስጥ የዓረና-መድረክ አባላት የሆኑ ነዋሪዎች “ዓረና ይርዳህ” በመባል ከዕርዳታው አሠጣጥ ዕቅድ ውጪ ተደርገዋል፡፡ የህወሃት ካድሬዎች ነዋሪ ገበሬዎችን “ከብቶቻችሁን ሸጣችሁ ተገላገሉ” በማለት መመሪያ እየሰጡ ነው፡፡ አምዶም ገብረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ እንዲህ ይነበባል፡- ድርቅ በትግራይ አስከፊ ሁኔታ ላይ በመድረሱ የቤት እንስሳ ህይወት እየቀጠፈ ነው። በትግራይ አብዛኛው ወረዳዎች የድርቅ አደጋ የተጠቁ ሲሆኑ እጅግ አስከፊ የሚባል ጉዳት ያደረሰባቸው ወረዳዎች ግን አፅቢ ወንበርታ 12 ቀበሌዎች፣ የክልተ … [Read more...] about በትግራይ ድርቅ ህይወት እየቀጠፈ ነው!
ስለ ክህደት ምንነት ልምዴን ላካፍላችሁ
ከአመታት በፊት በምርጫ ዘጠና ሰባት አካባቢ አዋሳ ከተማ ውስጥ የገጠመኝ ነገር ትዝ ይለኛል። በአዋሳ ከተማ ቆይታየ ጊዜ ከአንድ ታዋቂ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እሳተፍ ነበር። በዚህ ድርጅት መሳተፍ እንደጀመርኩ ብዙም ሳልቆይ የወጣቶች ጉዳይና የድርጅት ጉዳይ ሆኘ ተመደብኩ።ታዲያ በዚያ አጭር ጊዜ ቆይታየ የመንግስትን የስለላ ስራና ተፈጥሮ እንድረዳ እድል ስለሰጠኝ ያ ጊዜ አስተማሪየ ሆኖ ይሰማኛል። በውነት ለመናገር ያ የአዋሳ ቆይታየ ስለ ወያኔ ያለኝን መረዳት አራምዶት ነበር። ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (TPDM) መሪ የነበረው ሞላ የተወሰኑ ታጋዮችን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚለው ዜና ከተሰማ በሁዋላ ያ የአዋሳው ትዝታየ የኋሊት በምናብ ታወሰኝ። በተለይም የሞላ አስገዶምን ኢንተርቪው ሳይ “እኛ ከመንግስት ጋር ስንሰራ ቆይተናል። ግንኙነት ነበረን” ሲሉ … [Read more...] about ስለ ክህደት ምንነት ልምዴን ላካፍላችሁ
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ በደል እየፈጸመ ነው” ተጓዦች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚጓዙ መንገደኞችን በአሮጌው ተርሚናል በኩል በማስተናገድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው እየተዋከቡ መሆኑን መንገደኞቹ የደረሰባቸውን በደል ዋቢ በማድረግ ምንጮች ገልጸዋል። በተለይ ከሳውዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ተጓዦችን በአየር መንገዱ የሚገኙ የደኅንነት ሰዎች ግልጽ ጉቦ እየጠየቁ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በተለይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚጓዘው ኢትዮጵያውያዊ አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ እንደመሆኑ መጠን ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚደረግባቸው የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች ዜጎች በገዛ አገራቸውና አየር መንገዳቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታችው የመንግስት እጅ እንዳለበት አመላካች መሆኑን ይጠቁማሉ። በአሮጌው ተርሚናል የሚስተናገድ እነዚህ የአየር መንገዱ ተገልገላይ ኢትዮጵያውያን ደምበኞች ይዘውት በሚወጡትና … [Read more...] about “የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ በደል እየፈጸመ ነው” ተጓዦች
በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል የሕወሃት/ብአዴን ታጣቂዎች 2 ነዋሪዎችን ገደሉ፣ ከ50 በላይ አቆሰሉ
የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ሕወሃት) የፈጠረው የብአዴን ታጣቂዎች በመተማ ከተማ "በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች" በሚል ሁለት ነዋሪዎችን መግደላቸው፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው እንዲሁም ከሃምሳ በላይ ማቁሰላቸው ተሰማ። የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም። ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን። እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ … [Read more...] about በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል የሕወሃት/ብአዴን ታጣቂዎች 2 ነዋሪዎችን ገደሉ፣ ከ50 በላይ አቆሰሉ
OPEN LETTER OF APPEAL TO POPE FRANCIS I REGARDING JUSTICE FOR ETHIOPIA
Your Holiness, The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause presents its compliments, in our most humble and respectful manner, to Your Holiness and submits this petition for a formal Vatican apology to the Ethiopian people for its complicity with Fascist Italy in the war crimes perpetrated in Ethiopia by the Italian regime then led by Benito Mussolini during 1935-41. We take this opportunity to express our joy and sincere appreciation of Your Holiness’ formal apology to the people of … [Read more...] about OPEN LETTER OF APPEAL TO POPE FRANCIS I REGARDING JUSTICE FOR ETHIOPIA
ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል
በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር። የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም። አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ … [Read more...] about ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል
ሌቦ ነይ …
ማስታወሻ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የህወሃት አባል ወይም ተላላኪ እንደሆነ የታሰበ ግለሰብ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት (በፎቶው እንደሚታየው) ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን እንግሊዝ ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ለመጀመሪያ የፍርድ ምርመራ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኛው “ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ግለሰቡ “ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጾዋል። ይሁን እንጂ ዳኛው “ይህን ያህል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ ለጊዜው በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሚ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የወለላዬ ግጥም በዚህ ዘረፋ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ (ቅርብ የሆናችሁ … [Read more...] about ሌቦ ነይ …
ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም!!
መግቢያ በየጊዜው ለመጻፍ ብዕሬን በመቃጣት ላይ እያለሁ እመለሳለሁ። ይህንን የማደርግበት ምክንያት በእንግሊዘኛም ሆነ በአማርኛ በየድህረ-ገጾች ላይ ተጽፈው ለንባብ የሚቀርቡ ጽሁፎች ስለማያረኩኝ ነው። ይህንን የምልበት ምክንያት እኔ ብቻ በትክክል የምጽፍ ሆኖ ስለሚሰማኝ ሳይሆን የጽሁፎቹን ዓላማ ለማወቅም ሆነ ለመረዳት ስለሚያስቸግረኝ ነው። ሁለተኛ፣ አብዛኛዎች ጽሁፎች በተወሰነ ሃሳብ ላይ ያተኮሩና በዚያው ላይ የሚሽከረከሩ አይደሉም። በሌላ አነጋገር እንድንወያይበትና እንድንከራከርበት በር የሚከፍቱ አይደሉም። ሁሉም እንደፈለገውና እንደመሰለው የሚጽፍ እንጂ ከተጨባጭ ሁኔታዎችና ከህሊና ሁኔታ በመነሳት ችግራችንን የሚተነትን አይደለም። በሶስተኛ ደረጃ፣ በአንዳንድ ድህረ-ገጾች ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በአንድ ግለሰብ ሃሳብና ርዕይ ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ፣ የግለሰብን ስም የሚያጎድፉ ወይም ሞራሉ … [Read more...] about ችግሩ ወያኔን በማስወገድ ብቻ የሚፈታ አይደለም!!
ክላሽንኮቭ ያነገበ የህወሃት ታጣቂ የወጣቷን ህይወት አጠፋ
አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡ ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡ ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም … [Read more...] about ክላሽንኮቭ ያነገበ የህወሃት ታጣቂ የወጣቷን ህይወት አጠፋ










