ለዚህ ሃሳብ ማብራሪያ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል መንግሥት ምክትል ርዕስ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ውይይቱ የተናጠል ሳይሆን ሁሉንም አካላት ማካተት እንዳለበት መናገራቸውን ጠቅሷል። "የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ፌደራሊስት ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ትግራይ መንግሥት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም" ማለታቸውን ቢሮው ገልጿል። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ "ውይይቱ በመጨረሻ ሰዓት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው" ያሉ ሲሆን ጨምረውም "የአገሪቱን ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀስ አካል ችግሩ የተፈጠረው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምባገናናዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው … [Read more...] about አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም
Uncategorized
በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
በትግራይ የሚገኘውና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑን ስደተኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በመጠለያው የሚኖሩ በአስር ቀናት ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ መጠለያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ከሰባት ዓመት በፊት ተቋቁሞ 18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች እያስተናገደ የሚገኝ ማእከል ነው። በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ሕንፃፅ የሚኖሩ ኤርትራውያን እንደሚሉት ባለፈው ዕለተ ሐሙስ ነበር የሚኖሩበት መጠልያ እንደሚዘጋና በአስር ቀናት ውስጥ ቦታ እንዲቀይሩ የተነገራቸው። … [Read more...] about በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የሜቴኩ ክንፈ እና የኢንሳው ተክለብርሃን በቁጥጥር ሥር ውለዋል
የቀድሞው የሜቴክ ዋና ኃላፊ የነበረው ክንፈ ዳኜው እና የኢንሳ (የህወሃት የኢንፎርሜሽን ስለላ) ኃላፊ የነበረው ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት (አብመድ) በፌስቡክ ገጹ ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ዋልታ እንደዘገበው ደግሞ “ሱዳን ድንበር አካባቢ የተያዙት ሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ዛሬ (ማክሰኞ) ከሰአት ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የደረሰን መረጃ ያመለክታል”። አብመድ ግለሰቦቹን በስም ባይጠቅስም በዜናው ላይ ግን “የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እና የኢንሳ የቀድሞ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል” በማለት ነበር የዘገበው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ትላንት በሰጠው መግለጫ ሜቴክ ያለምንም ጨረታ የ37 ቢሊዮን ብር ግዢ የፈጸመ መሆኑን የተናገረ ሲሆን በሽብር፣ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ … [Read more...] about የሜቴኩ ክንፈ እና የኢንሳው ተክለብርሃን በቁጥጥር ሥር ውለዋል
“ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም! ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም! አይኖረውም!” ዐቢይ አሕመድ
ህወሓት የሰየመለትን ስም፣ ዓርማና መዝሙር በማስወገድ ራሱን ነጻ ያወጣው የቀድሞው ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የሚል ስያሜ በመውሰድ አዲስ ፓርቲ ሆኗል፤ የሚከተሉትን የኦዴፓ/ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በማድረግ መርጧል 1. ዶክተር አብይ አህመድ፤ 2. አቶ ለማ መገርሳ፤ 3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፤ 4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ 5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፤ 6. አቶ አዲሱ አረጋ፤ 7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ 8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ፤ 9. ዶክተር ዓለሙ ስሜ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከተሉትን 55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፤ እስካሁን ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት መሰረትም፦ ዶክተር አብይ አህመድ አቶ ለማ መገርሳ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አቶ ሽመልስ … [Read more...] about “ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም! ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም! አይኖረውም!” ዐቢይ አሕመድ
ኢሳያስ ከ“ጎረቤት” ትግራይ በፊት የአማራን ክልል ሊጎበኙ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሰላም ስምምነት ከፈፀሙና ሁለቱ መሪዎች በየአገራቱ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት ከመንግሥት አልፎ በሕዝብ ደረጃ በርካታ ለውጦችን አምጥቶዋል። ይህንን ተከትሎ ኢሳያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ የአማራን ብሔራዊ ክልልን እንደሚጎበኙ ተገልጾዋል። ኤርትራን ከትግራ ጋር እንድታብር ለሚመኛትና በኢሳያስ አጠራር የህወሓት “ጥምብ አንሣዎች” ይህ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራና ውርደት ነው ተብሏል። ፋና ባሰራጨው ዜና ላይ እንደተገለጸው “የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሚመሩት ልኡክ በአስመራ ይገኛል። በቆይታቸውም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ልዩ አማካሪ ከአቶ የማነ ገብረአብ ጋር የኤርትራውያንንና የኢትዮጵያውያንን የሕዝብ … [Read more...] about ኢሳያስ ከ“ጎረቤት” ትግራይ በፊት የአማራን ክልል ሊጎበኙ ነው
የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!
ከ27 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ የተገኙት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ ዶ/ር ዐቢይ የዕለቱን የመወያያ አጀንዳ ከገለጹ በኋላ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች አሳባቸው እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው፤ የኔታ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የገቡት። ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ በአዳራሽ ውስጥ የነበሩ ተሰብሳቢዎች የኔታ የመቀመጫ ወንበራቸውን እስኪይዙ ድረስ የተሰብሳቢው ዓይን በፍቅርና በአክብሮት እሳቸው ላይ ነበር ያረፈው። የተጀመረው ውይይት በተሰብሳቢዎች በሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት ቀጥሎ ለሻይ ዕረፍት ስብሰባው ተቋረጠ። ሁላችንም ሻይ እና ቡና ወደተዘጋጀበት ቦታ አመራን፤ ዶ/ር ዐቢይ ለሻይ በወጣንበት ወቅት የቱ ጋር እንዳሉ እኔ ልብ አላልኩም፤ ይልቁንም ለየኔታ ትኩስ ነገር ምን ላምጣሎት ብዬ ስጠይቃቸው፤ “አንድ ሲኒ ቡና ትንሽ ስኳር ጨምረ አመጣልኝ፣ ከዚያ … [Read more...] about የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!
ሁለቱ ጄኔራሎች
ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና ሜ/ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ከመከላከያ ሰራዊቱ በተለያየ ጊዜ “የመከላከያ ሪፎርም አደናቃፊ” በሚል ማዕረጋቸው ተገፍፎ የተሰናበቱ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸው። ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የቀድሞ የጦር ሠራዊት አባል የነበረና በ1978 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ጀግና አዋጊ እንደሆነ የኢህዴን ጓዶቹ ሳይቀር ይመሰክሩለታል። ድህረ-ደርግ በሲቪል አስተዳዳሪነት የላስታ ወረዳ አስተዳደር ቀጥሎም የሰሜን ወሎ ዞን አመራር ሆኖ ሰርቷል። የባድመ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ወደ ወታደራዊ አመራርነት የተመለሰው አሳምነው ጽጌ፣ የቀደመ የትግል ልምዱን መነሻ በማድረግ ያለአንዳች ማዕረግ በጦርነቱ ውስጥ በባድመ የጦር ግንባር 22ኛ ክፍለ ጦርን እየመራ ተዋግቷል። ባድመ ላይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከነበሩት ጥቂት አመራሮች አንዱ አሳምነው ጽጌ ይገኝበት … [Read more...] about ሁለቱ ጄኔራሎች
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተስፋን-በጥንቃቄ (cautious optimism) ካነገቡት ሰዎች አንዱ ነኝ። የተስፋዬ መሠረቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ፣ የገቧቸው ቃልኪዳኖች እና አሁን የታየው መረጋጋት ናቸው። አሁን የታየው መረጋጋት ስል የቄሮዎች የአደባባይ ተቃውሞ መቆሙን ማለቴ አይደለም። ተቃዋሚዎችን እያሳደዱ መከታተል፣ ማዋከብ እና ማሰር ርቀን ሳንሔድ አምና ከነበረው አንፃር እንኳ ልዩነቱ የትየለሌ ነው። ለዚህ የራሴን ስሜት እና ተሞክሮ ነው በምሳሌነት የማቀርበው። በፊትም አሁንም ሐሳቤን በነጻነት እገልጻለሁ። ነገር ግን አምና እና ካቻምና ከያንዳንዱ ጽሑፎቼ/ንግግሮቼ ቀጥሎ እስር ይመጣል እያልኩ እየሰጋሁ ነበር የማደርገው። አሁን ምን ያክል ይዘልቃል የሚለው ቢያሰጋኝም እታሰራለሁ እያልኩ በየደቂቃው አልባትትም። በፊት ሲያስሩ፣ ሲያዋክቡ እና ሲከስሱ ከነበሩት … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!
ይድረስ የፈጣሪን ስም ለጠሩ ዶ/ር አብይ አህመድ
በ 44 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መሪ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ “ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” እያሉ ንግግርዎን ሲያሳርጉ አይቶ ሕዝበ ኢትዮጵያ በደስታ ተሞልቷል። እኔ ግን እያሉ ያሉት ይህ የማሳረጊያ ቃል በሕዝብ ፊት ብቻ ሳይሆን በአምላክ ፊት ምንና ምንን በሃላፊነት ሊያስጠይቅዎ እንደሚችል የነገሩ ክብደት እጅግ አሳስቦኛል። የፈጣሪ ስም ከተነሳ ዘንዳ፥ ይህ ፈጣሪ የሚሰጠን በረከት ምንነት ይታወቅ ዘንድ ያስፈልጋል። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” ሲባል ዝንተ አለም አሳልፈን ዛሬን ደረስን። እስከ ዛሬ “ትዘረጋለች” ከማለት አልፈን “ዘረጋች” ወደማለት ሳንሸጋገር ሦስት ሽህ ዓመታት ጠበቅን። በዚህ ፅሁፌ ይህ 3000 ዓመታት ያስቆጠረው ትንቢት ተፈፀመ የሚያስብለው ሁኔታ ምን እንደሆነና፤ የፈጣሪን በረከት የጠየቁት እርስዎ ስለዚህ በረከት ሊኖርዎት … [Read more...] about ይድረስ የፈጣሪን ስም ለጠሩ ዶ/ር አብይ አህመድ










