ሥልጣን የያዙ ሰሞን ሞት የቀደማቸው መለስ ሲጠየቁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እመግባለሁ ወይም ሲመገብ አያለሁ የሚል የውሸት ተስፋ ሰጥተው ነበር፡፡ “የቀማኛ ኢኮኖሚ አቀንቃኝ” የነበሩት መለስ ለሥልጣናቸው ማራዘሚያ ጥቂቶችን በሃብት እንዲወጠሩ ሲያደርጉ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ቀርቶ በሶስት ቀን አንዴ የማይመገብ አድርገውት ተሰናብተዋል፡፡ “ሌጋሲያቸውን እንጠብቃለን፤ እናስጠብቃለን” የሚሉት ያሁኖቹ ዘራፊዎችና ተላላኪዎች አገር በሁለት አኃዝ አድጋለች፤ ኢኮኖሚው ዓለምን እያስደነቀ ነው፤ ህዳሴ ነው፤ ውዳሴ ነው፤ … በማለት በቁማቸው ይዋሻሉ፤ የጥቅም ተካፋዮቻቸውም ይህንኑ ይዘው በየቀኑ ሲያናፉ ይውላሉ፡፡ ህወሃት ስለዘረጋው የዘራፊ፤ የቀማኛ፤ የሌባ፤ ኢኮኖሚ ብዙ ሊባልበት ይቻላል፡፡ ሌብነቱን ደግሞ መለስ ራሳቸው መስክረው ነው የሞቱት፡፡ “ያስቸገረን የመንግሥት … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
“ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
"መንግሥት ስህተቱን ካመነ ኦሮምያ ውስጥ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ አጥፊዎች በገለልተኛ አካል ተለይተው ይቀጡ” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጠይቀዋል። “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” ሲሉም ተችተዋል። “ቀደም ሲል የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በኦሮምያ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋናው መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው” ማለታቸው ይታወቃል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ መለስካቸው አምሃ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር አለው፡፡ እዚህ ላይ ያዳምጡ። (ምንጭ: VOA) … [Read more...] about “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
አንቺን አስታዋሼ
መቼ ትመጫለሽ መቼ ልጠብቅሽ ወይ መቼ ላምጣልሽ መቼ ላቀብልሽ ሽሮና . . . ምናምን ስለተላከልሽ ሽሮውን ውሰጂው በርበሬውን ውሰጅ ቅቤውንም ውሰጅ . . . ሚጥሚጣ ተይልኝ እሱ ስለሆነ - አንቺን ሚያስታውሰኝ ............................. ምን ይሰራልሀል ብቻውን ሚጥሚጣ ትደፋው የለም ወይ እንጀራ ስታጣ … [Read more...] about አንቺን አስታዋሼ
“ናቡቴ” የኢትዮጵያ ሕዝብና “አክዓብ” ገዢዎቹ – ፩
በኢትዮጵያ የግማሽ ምዕተዓመት የፖለቲካዊ ለውጥ ንቅናቄ ታሪክ የመሬት ጥያቄ ዋነኛውና አብዮትን ማሳካት የሚችል ጉልበት ያለው የህዝብ ብሶት መገለጫ መሆኑ የማያሻማ ነው፡፡ ፍውዳላዊውን የሰለሞናዊ ስርወ መንግሰት ንጉሳዊ ስርዓት ግብዓተ መሬት ካፈጠኑት አብይ የሕዝባዊ ብሶትና ምሬት መገለጫ የለውጥ ንቅናቄ መርሆች መኸል “መሬት ለአራሹ” የተሰኘው የተማሪዎች ንቅናቄ መርህ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በንጉሳዊው የፊውዳል ስርዓት የንጉሱ ጋሻ ዣግሬዎች ማለትም መኳንንቱ እና መሳፍንቱ መላውን የሀገሪቱ ሰፊ የገጠር እርሻ መሬት በባለቤትነት (በባላባትነት) ተቀራምተው፤ ባለርስት በመባል ድኸውን ገበሬ ጭሰኛ በማድረግ ጉልበቱንና ምርቱን እየበዘበዙ ለዘመናት ህልውናውን እየፈተኑ፣ ኑሮውን ከድጥ ወደ ማጥ እየገፉ ጭቆናንና በደልን አንሰራፈተው ቢቆዩም የጭሰኛው ገበሬ ልጆች የሆኑት የለውጥ ፋኖ … [Read more...] about “ናቡቴ” የኢትዮጵያ ሕዝብና “አክዓብ” ገዢዎቹ – ፩
የወንድሞቻችን ቅኝ ተገዥዎች አንሁን
ዛሬ ታላላቅ አፍሪካውያን ከተናገሩት መነሳትን መረጥሁ። አንጋፋው ደቡብ አፍሪካዊ ታጋይ ዴዝሞን ቱቱ “When the missionaries came to Africa, they had the Bible and we had the land. They said ‘Let us pray’. We closed our eyes. When we opened them we had the Bible and they had the land”. ተቀራራቢ ትርጉሙ “ሚሲዮናውያን ወደ አፍሪካ ሲመጡ መጽሃፍ ቅዱስ ይዘው ነው። እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ‘እንጸልይ’ አሉን። ለጸሎት ዐይናችንን ጨፈንን። ጸሎቱን ጨርሰን ዐይናችንን ስንከፍት ግን እኛ መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ታቅፈን ስንቀር እነሱ ግን መሪታችንን ይዘውት አገኘን” የሚል ነው። አዎ! ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ዚምባዌ ወዘተ… በቅኝ ግዛትነት ለመውረር የመጡት ነጭ ሚስዮናውያን … [Read more...] about የወንድሞቻችን ቅኝ ተገዥዎች አንሁን
Conference on the Future of Ethiopia: Transition, Democracy, and National Unity
Vision Ethiopia, an independent network of Ethiopian academics and professionals, in collaboration with Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT), has previously announced to convene a conference on a theme of “Ethiopia’s National Unity and Federalism.” But, a number of disturbing events have occurred since the first call for papers was issued. Peaceful protests around the Addis Ababa Master Plan and land dispossessions have descended into open conflicts and, in practical terms, naked … [Read more...] about Conference on the Future of Ethiopia: Transition, Democracy, and National Unity
አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት
አቶ ዠ ከጸሃፌ-መፈክር ወደ ጸሃፌ-ተውኔት እሸጋግራለሁ ብለው መፈከራቸው እንዳለ ሆኖ፣ ይንን አስመልክቶም ለኢሃዴግ ፍቅር ቴአትር ቤት ሥራ አስቀማጭ ደብዳቤ መላካቸው እንዳለ ሆኖ፣ ... ከወራት በኋላ የአቶ ዠ ባለቤት ወይዘሮ ዘ ቡና አፍልተው ከአቦል እስከ በረካ ተጠጥቶ እንዳለቀና ሥኒ እያጠቡ እያለ... ወይዘሮ ዘ ገረሙህ?“ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል” ሲባል አልሰማህም?ባላቸው ዠ ከሆኑ እሳቸው ከ ዘ ሌላ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?ዠ እኮ ባርኔጣ የደፋ ዘ ነው።ከምሬ ነው። ካላመንከኝ ሥለ ቃላትና ፊደላት የሚፈላሰፉ “ዲባቶ”ዎች ፈልግና ጠይቅ። ሥምህ ጨ ከሆነ የምታጫትና የምታገባት ኮረዳ ጠ ነው የምትባለው። እና ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ፣ አቶ ዠ ከባለቤታቸ ጋር “ጨዋታ” ጀመሩ። “ጨዋታ“ው ሲያልቅ ጻፉት፣ አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት። ገጸ-ባህርያት ዠ እና ዘ ብለው ጀመሩ። ዘ … [Read more...] about አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት
ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ
ጉዳዩ፦ መነሻ የመግባቢያ ኃሣብ ስለማቅረብ፦ እስከ አንድነት ለመድረስ የሚያስችል ውጤታማ ትብብር ለማድረግ መከተል ስለሚገባን አካሄድ፤ ማናችንም እንደምንገነዘበው፣ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ስንደራጅ የኖርነው በልዩነቶቻችን ላይ ባተኮሩ ዓላማዎች ዙሪያ ነው። ልዩነቶቻችን ደግሞ ከርዕዮተ-ዓለም ባሻገር፣ በነገድ፣ በጎጥ እና በኃይማኖት ጭምር ያጠነጠኑ በመሆናቸው፣ አንድነታችንን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ከሁሉም በላይ፣ የትግሬ-ወያኔ በባዕዳን ድጋፍ ተበረታትቶ፣ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ሲጨብጥ፣ ያስተጋባው የዲሞክራሲ ቀቢፀ-ተስፋ እውነት መስሏቸው የተከተሉት ወገኖች አይጠፉም። ሆኖም ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን በተግባር ሲያከናውን የሚታየው፥ የቋንቋ ፣ የነገድ ፣ የጎሣ ፣ የዘር ፣ የኃይማኖት ፣ ወዘተርፈ ልዩነቶችን መሠረት አድርጎ ሕዝቡ … [Read more...] about ፀረ-ወያኔ አቋም ለአላቸው የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት በሙሉ
“አፋኝ ህጎችና ፖሊሲዎች ለማሻሻል የተደረገ መሠረታዊ ለውጥ የለም”
እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ እና ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎች ላይ እያደረገ ያለውን ጫና ቀጥሏል፤ አብዛኞቹ እንግልት፣ ዘፈቀዳዊ እስር እና በፖለቲካ የተቀናበረ ክስ ገጥመዋቿል፡፡ ገዢው ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ግንቦት ወር በተካሄደው ምርጫ 547 የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፏል፤ ይሄውም የሆነበት አንዱ ምክንያት ጠንካራ ተጻራሪ ሃሳብ የላቸው ወይንም ተቃዋሚዎች በመታፈናቸው ነው፡፡ በሰኔ ወር የዩናይትድ ስቴትስ (አሜሪካ) ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው አስቀድሞ የተወሰኑ ታዋቂ እስረኞች ከመፈታታቸው ባሻገር በኢትዮጵያን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃኑን አስረው የያዙትን እጅግ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎች ለማሻሻል የተደረገ መሰረታዊ … [Read more...] about “አፋኝ ህጎችና ፖሊሲዎች ለማሻሻል የተደረገ መሠረታዊ ለውጥ የለም”
እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!
ቀኑ፡ እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓም/February 14, 2016 ሰዓቱ፡ 1:00 - 5:00 PM ቦታ፡ Sheraton Silver Spring Hotel 8777 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20910 ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) እሁድ የካቲት 6፤ 2008ዓ.ም./ February 14, 2016 ከ1:00 - 5:00 PM በሚያደርገው የእኛ ለእኛ ሕዝባዊ ውይይት ላይ እንዲገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ዋናው የትኩረት ሃሳብ በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ግፍ፣ እስር፣ ግድያ፣ እንዲሁም የአየር መዛባትና አስተዳደራዊ ብልሹነትን ተከትሎ የተከሰተው ችጋር፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየጨመረ የመጣውን ሕዝባዊ ዓመጽ ወዴት አቅጣጫ ሊወስደን ይችላል? የሚል ሲሆን ከዚህ አንጻር በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ ወራት፣ … የሚከሰተው ነገር የኢትዮጵያን … [Read more...] about እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!










