እንደ - መግቢያ በኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ ላይ ብዙ ልዩነቶች ይስተዋላሉ፡፡ የልዩነቶቹ ሥረ-ምክንያት እንደ ጸሐፊው ማንነትና የሥርዓታቱን ባህሪ መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የኢትዮጵያን የቀደመ ታሪክ የሚቃኙ የተለያዩ ኃይለ-ሐሳቦች በየጊዜዉ እንዲጸባረቁ ግድ ብሏል፡፡ የታሪክ ትንቅንቁ በአጥቂነትና በተከላካይነት የሚበየን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ፍልሰት፣ መስፋፋት፣ ብሔራዊ ጭቆና፣ ቅኝ ግዛትና መሰል ቃላት ላለፉት አርባ ዓመታት፤ በተለየ መልኩ ደግሞ ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት የታሪክ ሙግት አጀንዳ አስቀማጭ ቃላት ሆነዋል፡፡ ባሳለፍነው የሩብ ክፍለ ዘመን ጉዟችን የታሪክ ጉዳይ እጅግ አብሰልሳይና ውርክብ የበዛበት ሊሆን የቻለው አገዛዙ ለኢትዮጵያ የቀደመ ታሪክ በጎ እይታ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የታሪክ ነክ ሙግቶች ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዱላ ቀረሽ ደረጃ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የታሪክ ውዝግብ የወለደው አዲሱ የሕዝባዊ ታሪክ ፀሐፊና መርማሪ – በዕውቀቱ ሥዩም
እንደገና መሬት ላራሹ!
በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ፣ የመሬት ላራሹ ጉዳይ ሙሉ መልስ ጠፍቶት እነሆ ግምሽ ምዕተ ዓመትን ፈጀብን። ዛሬም ግን ይህ ጥያቄ እንደገና ተቀጣጥሎ እልባት ካላገኘ አገራችን ከችግር ትወጣለች ማለት የማይሆን ነገር ነው። የመሬት ይዞታን ጉዳይ በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወገኖች የተለያየ ኣሳብ ያላቸው ይመስላል። አንዱ ወገን ችግሩ መሬት የመንግስት መሆኑ ሳይሆን የመንግስት የፖለቲካ ቁርጠኝነቱ ዝቅተኛ መሆኑ ነው ይላል። መንግስት ጠንካራና ለሃገር ኣሳቢ ቢሆን መሬት በመንግስት መያዙ ጥሩ ነው አይነት ይከራከራሉ። በሌላ በኩል በተለይም ከመንግስት ኣካባቢ ደግሞ የመሬት ባላቤትነት ጥያቄ እውን ከሆነና ገበሬው እስከ መሸጥና መለወጥ ሃላፊነት ከተሰጠው ምን አልባት መሬቱን እየሸጠ በሰፊው ይፈናቀላል የሚል ነገርም አለ። ይሁን እንጂ ታዲያ መንግስት መሬት እንዲሸጥ … [Read more...] about እንደገና መሬት ላራሹ!
በሃዋሳ በሶስት ጥይት ስለተገደለው
ባፈው ሃሙስ በሃዋሳ ከተማ ከተማ ልዩ ስሙ ታቦር ት/ቤት በሚባል አካባቢ ፖሊስ በሦስት ጥይት አንድ ሰው መግደሉ በዕለቱ ወዲያውኑ ከሥፍራው መረጃ ቢደርሰንም እስካሁን ተጨማሪ መረጃዎችን ስናሰባስብ ቆይተናል፡፡ የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) የላኩልን በምስል የተደገፈ መረጃ እንደሚያመለክተው ድርጊቱ የተከሰተው ግለሰቡ ለቤ/ክ ወደተከራየ ጊቢ ለመግባት በር ላይ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ዘጋቢያችን ጠቁመዋል፡፡ ቤቱ ለቤተክርስቲያንነት ቢከራይም የቤተሰቦቹ የሆነውን ቤት እሱ ሳያውቅ የተከራ በመሆኑ እንዲለቁለት ተከራዮቹን በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበር መረጃ አቀባያችን ያስረዳሉ፡፡ እንደተለመደው በዕለቱም ይህንኑ ጥያቄውን ለማቅረብና ወደ ጊቢው ለመግባት በሚሞክርበት ጊዜ ተከራዮቹና ሌሎች ውስጥ የነበሩ ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ መጥራታቸውን ዘጋቢያችን በላኩልን መረጃ … [Read more...] about በሃዋሳ በሶስት ጥይት ስለተገደለው
በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም
በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታና ደኅንነት ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ አለመሆኑ ተነገረ፡፡ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ወደ መስክ የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ተከለከለ፤ የፕሮጀክት ሥራዎች ሊደናቀፉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ኢህአዴግ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን ወደተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን መረጃው የደረሳቸው ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለይ የአማራ ክልልና በምዕራብ ደግሞ የጋምቤላ ክልል አካባቢ ያለው ውጥረት እጅግ እያየለ በመምጣቱ በቦታዎቹ ላይ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ሊደርስባቸው ስለሚችል ጉዳት ተጠያቂ እንደማይሆን ኢህአዴግ በሰጠው ማሳሰቢያ አስታውቋል፡፡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል የካቶሊክ ዕርዳታ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም
The Danger Of a Single Story and What We Ethiopians Can Do About It
Based on Nigerian novelist Chimamanda Adichie’s Global TED Talk, which was filmed in 2009, I recently wrote a blog. The talk was very powerful- over 9 million people have watched it. In that blog, I complained concerning the unfair treatment of the media at world stage against our country. Notwithstanding of Ethiopia being one of the two countries in Africa that never been colonized, irrespective of our coffee- one of Starbucks’ signature brands, regardless of our long distance runners who hold … [Read more...] about The Danger Of a Single Story and What We Ethiopians Can Do About It
አቅም የተፈጠረላቸው ፈላሾች – ህወሃቶች
ከ1997 ምርጫ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ከፈለሱት የክልል ነዋሪዎች መካከል ከ87 በመቶ በላይ የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑ አንድ የስታትስቲክስ ባለስልጣን ባለሙያ ጠቆሙ። ቁጥሩ የሚያሳየው ባግባቡ ከሃብትና ንብረት፣ ወይም ከመተዳደሪያ ጋር የተመዘገቡትን ብቻ እንደሚያካትት ባለሙያው አመልክተዋል። ከዘጠና በመቶ በላይ ከሌሎች ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚፈልሱት የእለት ጉርስ ፍለጋ ነው። በኢንቨስትመንት ስም በሚፈናቀሉ ዜጎች ኮቴ፣ በኮንደሚኒየም ቤቶች ዝውውር፣ መከላከያ፣ ደህንነትና ሁሉንም ዓይነት የፖሊስ ተቋማት ጨምሮ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ቅጥርና በመሳሰሉት ሰፊ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ ተምመዋል፤ እየተመሙም ናቸው። እንደባለሙያው የሌሎች ክልል ተወላጆች በስፋት ወደ አዲስ አበባ ቢፈልሱም፣ የትግራይ ተወላጆችን ልዩ የሚያደርገው “አቅም እየተፈጠረላቸው … [Read more...] about አቅም የተፈጠረላቸው ፈላሾች – ህወሃቶች
የላላው ጭቃ
አሁንም ቀኑን እንቆጥራለን። ሌሊቱንም እንዲሁ። አሁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን ተግባር እንዘረዝራለን። አሁንም ሰዎች በገዛ ሀገራቸው እንዳውሬ እየታደኑ፣ እየተያዙ፣ ይታሰራሉ፣ ከሀገር ይሰደዳሉ፣ ይገደላሉ፣ እንላለን። አሁንም በየቤተክርስትያኑና በየመስጊዱ እግዚዖ እንላለን። አሁንም የሀገራችን ለም መሬት ከባለቤቱ ኢትዮጵያዊ እየተነጠቀ፤ ለሹማምንትና ለውጪ ሀገር ባለሀብቶች ተሠጠ እያልን እናላዝናለን። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)። … [Read more...] about የላላው ጭቃ
Explaining Ethiopian Soaring Real Estate and Property Prices
Introduction Admittedly, in all countries of the world, Ethiopia included, the reasons behind rising property prices could be many. In the Ethiopian case, these factors include, among others, demand for and supply of real (estate) assets, rising population and urbanization, the existence of a large number of tenants working for donor communities (NGOs) and multinational institutions, huge influx of money that the diaspora community sends back home (remittances) that largely is poured onto the … [Read more...] about Explaining Ethiopian Soaring Real Estate and Property Prices
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳
ከአዘጋጆቹ፤ በጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ ጀማሪነትና አቀናባሪነት ሲስተናገድ የነበረው “እኚህ ሰው ማናቸው?” የተሰኘው ዝግጅታችን እንደገና ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ይቅርታ እየጠየቅን አሁን ግን በወዳጃችን ወለላዬ ብርቱ ትጋት ለመጀመር በመቻላችን ለወለላዬ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በዝግጅቱ ስትካፈሉ ለነበራችሁና መልሳችሁን ስትሰጡ ለነበራችሁ ሁሉ አሁንም ይህንኑ ማድረግ እንድትጀምሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በአገራችን ስማቸውን ተክለው ያለፉ በፎቶ አስደግፎ የግጥም ጥያቄ ማቅረብ ሲሆን ተሳታፊዎችም ምላሻችሁን በግጥም እንድትመልሱ ትደፋፈራላችሁ፡፡ ታሪክ በሥነቃል ታጅቦ ያዝናናል፤ ዝርዝር ጥናት ለማድረግ ለሚፈልግ ደግሞ ብርሃን ይፈነጥቃል፡፡ ለአሁኑ የእኚህን ሰው ፎቶ በግጥማዊ ጥያቄ አጅበን አቅርበናል፡፡ ከላይ እንዳልነው ቢቻል በግጥም ምላሻችሁን ከሥር … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳
መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
* “የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሊደርስ ይችላል” ነዋሪዎች * “የሞቱት 14 ሰዎች ናቸው” ኢህአዴግ ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በበኩሉ የሞቱት 14 ብቻ ናቸው ይላል፡፡ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያ እንደ “ገጸ በረከት” ያመጡት መለስ በየቦታው የጫሩት እሣት ለፍርድ ሳያቀርባቸው ሾልከዋል፡፡ እሣቱ ግን አሁንም እየነደደ ነው፡፡ ጎልጉል ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ ባገኘው መረጃ መሠረት በግጭቱ የሞቱት እስከ መቶ እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ግጭቱ ከመነሻው በቀላሉ የተነሣ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሥር የሰደደ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንኑ ዜና ኢሳት ሲዘግብ የሟቾቹ ቁጥር ከመቶ እንደሚያልፍ ምንጮቹን ጥቅሶ … [Read more...] about መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ










