በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው። ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ … [Read more...] about የህወሓት ተስፋፊነት በኢትዮጵያ
የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በተለይ በምዕራብ ጎጃም አካባቢ የደነገገው አዲስ የበርበሬ አዋጅ ችግር እያስከተለ መሆኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ አስታውቀዋል፡፡ እንደ እማኝ ዘጋቢው ከሆነ አዋጁ የወጣው በ2002ዓም ሲሆን በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በዚህ ዓመት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ በበርበሬ ላይ ብቻ የተደነገገው አዋጅ ዋና ምክንያቱን በውል ለማወቅ የሚያዳግት ቢሆንም እንደ እማኝ ዘጋቢው አስተያየት በርበሬው ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚላክ በመሆኑ በተለይ የትግራይ ነጋዴዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጥቀም ታስቦ እንደሆነ ከሚሰጡት ግምቶች የላቀው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እማኝ ዘጋቢያችን የላኩልን መረጃ እንዲህ ይነበባል፡- “በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ በፍኖተ ሰላም በሺንዲ … [Read more...] about የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል እና ውጤቱ
ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግፍና የፍትህ መጥፋት ስለበዛ ህዝባዊ አመጽ በሁለት መንገድ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ቆይተዋል አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች። አንደኛው ህዝብ ራሱ ድንገት የሚያነሳውና የሚመራው (spontaneous አመጽ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካ ወይም በሲቪክ በተደራጁ ሃይላት ታቅዶ የሚመራ በቅስቀሳና በጥሪ የሚነሳ ሊሆን ነው። ከወር በላይ የሆነውና በኦሮሞ ክልል ውስጥ በሰፊው የተነሳው ተቃውሞ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተፈጸመውን ማፈናቀል እንደ ማቀጣጠያ አድርጎ የተነሳ በህዝብ የተመራ ህዝባዊ አመጽ ሆኖ ብዙ ሰው በሚገባ እንደተረዳው የህዝቡ ጥያቄ የመንግስት ለውጥ ጥያቄ ነው። ለብዙ ዓመታት ታምቆ የቆየ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ የመሬት ነጠቃው ጉዳይ ናቸው ዛሬ ይህን ህዝብ አስመርረው- አስመርረው ጎዳና ላይ ያወጡት። ህዝቡ በየቦታው … [Read more...] about ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት
ድንበር
መግቢያ “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ … [Read more...] about ድንበር
አዲስ አበባ ስለምን ታወዛግባለች?
ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ ሲባል ተወውና መፅሃፍ ነጋዴ ሆነ፡፡ ማርክሲስት ነጋዴ! ‹ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣኦት› እንዲሉ የትናንት ቀዳሹ ሕሩይ ዛሬ ማርክስዚምን ወደደ፡፡ የሕሩይ ማርክሲዝም ከትናንት ማንነቱ እጅግ በተለየ መንገድ ወሰደው፣ የመፅሃፍ አርታኢነት፡፡ መፅሃፍ ሲያነብ፣ ሲተረጉም፣ ሲፅፍና የአርትኦ ስራ ሲሰራ ውሎ ጫት ይቅማል፤ በዛ ላይ አረቄም ይሞካክራል፡፡ በመጨረሻ አበደ፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ብዙ … [Read more...] about አዲስ አበባ ስለምን ታወዛግባለች?
በአደባባይ የተነገረው እውነት ውሸት ሆኖ ይከስማል ወይም እውነት ሆኖ ይጠበድላል
ትግርኛ ቋንቋም ያደናብር ጀመረ እንዴ! ዛሬ (ጥር 6) በፌስቡክ ላይ እንዳየሁት አንዲት ሴት ወገብዋን በነጠላዋ አስራ ትግርኛ የማያውቀውንም የሚቀሰቅስ ንግግር ስታደርግ ነበረ፤ የተናገረችው ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ነው፤ የሕዝቡን ቀልብ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራው ነበር ለማለት አያስቸግርም፤ አንዳንድ ትግርኛ ተናጋሪዎች "ጀግና" እያሉ በወያኔ ላይ የተቃውሞ ንግግር ማድረጉዋን ሲገልጹ አንዳንዶቹ የቋንቋው ባለቤቶች ደግሞ በጣም እየተናደዱ የሴትዮዋ ንግግር የተቃውሞ ሳይሆን የድጋፍ ንግግር ነበር እያሉ ይሞግታሉ፤ የትግርኛ ተናጋሪዎች ተቃውሞንና ድጋፍን ለመለየት ችግር አለባቸው ከማለቴ በፊት ከዚህ በፊት እኔ በትግራይ ሕዝብ ምክንያት የታማሁበትን እንደሚያስታውሰኝ መግለጹ ተገቢ ይመስለኛል፤ የወያኔ ግልጽ ተጽእኖ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ በሀሳብ እንዳይለያይ ነው፤ ወያኔ በትግራይ ችጋር የለም … [Read more...] about በአደባባይ የተነገረው እውነት ውሸት ሆኖ ይከስማል ወይም እውነት ሆኖ ይጠበድላል
በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረውና ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በጭካኔ ለመገደላቸው መረጃ የሚቀርብበት ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎዋል። ኢህአዴግ በአፈቀላጤዎቹ አማካኝነት "ሰልፍ የወጣ የለም፣ ከተማችን ሰላም ነው፣ የተገደለ የለም፣ . . ." በማለት የማስተባበያ ሙከራው በራሱ ሹሞች ሲጨናገፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። በሌላ በኩል በፌዴራልና በአግአዚ መራር ሰቆቃ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ "ባርነት በቃን፣ ግድያው ይቁም፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ . . ." የሚሉ መፈክሮችን እያነገበ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባለፉት ሦስት ቀናት የተከሰተውን ያቀረበው ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል። ባለፈው ሐምሌ ወር ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ታስሮ እንደነበርና ታሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው ተማሪ አብደታ … [Read more...] about በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ተቃዋሚው ሕብረት የኢትዮጵያ ፌድራላዊ አንድነት መድረክ፤ በአገሪቱ እየታየ ያለውን ቀውስና ሌሎች ነባር ችግሮች አስመልክቶ አሳስበውኛል፤ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል። “የሕዝቦቻችንን ጥቅሞች ማዕከል ያላደረጉና ሕዝብን ያላሳተፉ በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ እንጠይቃለን።” መድረክ። መድረክ መፍትሔ ያላቸውን ባለ አምስት ነጥብ ደብዳቤ መነሻነት የድርጅቱ ሊቀ መንበር ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ። … [Read more...] about በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰውን ጥቃት ከፎቶ ጋር አያይዘው ልከውልናል፡፡ ዘጋቢው እንዳሉት ከሆነ እዚያው ተማሪ ሲሆኑ የደረሰውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ይገልጹታል፡- “ከትላንት ወዲያ (ማክሰኞ) ማታ ካፌ ተማሪዎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ሲሞክሩ ፌዴራሎች በዱላ ጀመሩ፤ ከዚያም ዶርም ገባን፤ ሁላችንንም ዶርም እየገቡ በሩን እየሰበሩ እያወጡን አዳሩን ሲደበድቡን አደሩ፤ እስካሁን የሆነ ብሎክ መግባትም አይቻልም፤ የሞተ ሰው አለ እየተባለ ነው፤ እዚያም መግባት አይቻልም፤ ሌላ ብሎክ ደግሞ እሣት ተያይዞ ነበር፤ ማታ እሣት አደጋ መጥቶ አጠፋው … ወዴት እንሂድ? ወደ አገራችን እንዳንሄድ መንገድ ተዘግቷል፤ ኬላ በሙሉ (ተዘግቷል)፤ ወደ ጊቢም እንዴት እንግባ? ያገኙትን ነው የሚቀጠቅጡት፤ … ” በማለት በዚያ የደረሰውን ጥቃት እንድናሰማላቸው ከፎቶዎች ጋር … [Read more...] about ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት










