የሚዲያ አውታሮች ከውስጥም ከውጭም፣ የመንግሥትም ሆኑ የግል፣ የተገዙም ሆኑ በሊዝ የተያዙ፣ በደመ ነፍስ የሚጓዙትን ጨምሮ ሆን ብለው አስበውበትም ሆነ ሳያውቁት የጃዋር ሰለባና አንደበት ሆነዋል። አንዳንዶቹ በሳል የሚባሉት የሚዲያ አውታሮች ተቆጣጣሪ ኤዲቶር ያላቸውም አይመስሉም። “በድንገት በጃዋር ላይ በለሊት ከበባ መደረጉን ተከትሎ” እያሉ እሳቱ ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋሉ። የዘገቡ መስሏቸው የጃዋር አፈቀላጤ በመሆን በትጋት ያገለግላሉ። ጃዋር “ተከበበ ” የተባለው በማን ነው? ማን ከበበው? እንዴት ተከበበ? ስንት ሠራዊት ከበበው? ለምን ተከበበ? በሚል ማጣራቱ ቢቀር እሱ ያለውን ጠቅሶ መዘገብ እንዴት ለአንድ ሚዲያ ይከብዳል? ከደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ቁሳዊ ጥፋት ለማምለጥ እየዋለ ሲያድር ከሚባለው ውጪ “በሌሊት ጠባቂዎቼ እንዲነሱ ታዘዘ” የሚለውን ጠቅሶ ለመዘገብ ያልተቻለበት … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች በሱ መመሪያ የተጨፈጨፉት ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያውም ጭምር ነው
tplf
ህወሓት – ስዩም ተሾመን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደምትገል ማስጠንቀቂያ ላከች
“ሕዝብ ስዩምን ሊጠብቀው ይገባል” በጃዋር ትዕዛዝ ንጹሃን መጨፍቸፋቸውን፣ መታረዳቸውን፣ የእምነት ተቋማት መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን ተከትሎ ሴራው እንዴትና በነማን ቅንጅት እንደተቀነባበረ ይፋ በማድረግ ላይ ባለው አምደኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስዩም ተሾመ ላይ የግድያ ዛቻ ተሰነዘረ። የግድያው ዛቻ በቀጥታ የተላከው ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል ጌታቸው ነው። ህወሓት ፖሊሱን፣ ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ኢኮኖሚውን ከፍተኛውን የአገሪቱን ሥልጣን በተቆጣጠረበት ወቅት በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ጎን ለጎን ትግል ሲያካሂድ የነበረው ስዩም ተሾመ በተደጋጋሚ ታስሯል፣ ቶርቸር ተደርጓል፣ ተሰቃይቷል፣ እንደዜጋ ለምን ጻፍክ በሚል የከፋ ወንጀል ተፈጽሞበታል። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ቢያልፍም ግንባሩን ሳያጥፍ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን በብዕሩ ተጋፍጧል። ለውጡ እውን … [Read more...] about ህወሓት – ስዩም ተሾመን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደምትገል ማስጠንቀቂያ ላከች
የጃዋር ሰለባዎች ዝርዝር በከፊል!
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው የጫትና የመጠጥ ሱሰኛው ጃዋር መሐመድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሃን ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ ጃዋርን የምትደግፉ እፈሩ! ኅሊና ካላችሁ ወደምታምኑት አምላክ ንሰሐ ግቡና ተመለሱ፤ ከሌላችሁ ከሱ ያላነሰ ፍርድን በራሳችሁ ወይም በልጆቻችሁ እንደምታገኙ አትጠራጠሩ፤ አምቦ በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ከተገደሉት መካከል … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች ዝርዝር በከፊል!
እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
በመጀመሪያ "የለውጡን (ሥሌት) የሰራሁት እኔ ነኝ" አለ - በዝምታ "አዎ ነህ" ተባለ ቀጠለና "እዚህ ሀገር ሁለት መንግሥት ነው ያለው የአብይ እና የቄሮ [የኔ]" አለ አሁንም በዝምታ "አዎ ልክ ነህ" ተባለ መንግሥት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጃዋር መንግሥት በንግግር ብቻ ሳይገታ ውሳኔዎችን መሻር ማሳለፍ ጀመረ - በዝምታ መንግሥትነቱ ተረጋገጠለት እነሆ አሁን ደግሞ ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የመንግሥት ሰዎች፣ አኩራፊዎች እና ጥገኛ ባለሀብቶች በተቀነባበረ ሴራ "ኢመደበኛው መንግሥታችሁ ሊገረሰስ ነው" ተብሎ (“የመግደል ሙከራ” በሚል ፈጠራ) 67 ንፁሃን ምስኪኖች ያልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይፀና፤ ምሽጉም ይጠነክር ዘንድ መስዋዕት ሆነው ቀረቡለት። ይሄን ጊዜ በዝምታ አያልፉም ስንል - ተናገሩ! ምን አሉ "አንተ ዐይን ነህ - እንደ ብሌናችን … [Read more...] about እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች! የኢትዮጵያን ሕዝብ በአፈና፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ ጥሰት ሲገዛ በነበረው ህወሓት እና በሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቡድኖች በገዥነት ዘመናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል አገርን ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ተረድተናል። በተለይም አሁን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ ሌሎች አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ የሚያደርገው ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን የውህደት እንቅስቃሴ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ከማጣጣል ጀምሮ፣ የተለያዩ የትርምስ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን … [Read more...] about “የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
በተለያየ አጋጣሚ ከሚያጋጥሙኝ አስተያየቶች አንዱ ጃዋር መሃመድን መነጋገሪያችን ማድረጉን እንተው፤ግለሰቡ የሚሰጠንን አጀንዳ አንስተን በመተንተን ሰውየው የሚፈልገውን ክብር በመስጠት ተፅኖ ፈጣሪነት እንዲሰማው አናድርግ የሚል ነው። በግሌ ስራየ ብሎ ሰውን ማጉላትንም ሆነ ሆን ብሎ ሰውን ማሳነስን ብቻ አላማ አድርጎ መጓዙ የብልህ መንገድ አይመስለኝም። ጠቃሚው ነገር የሰው ስራ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩ ይመስለኛል። በዚህ ሁኔታ ግባችን ግለሰቦች ሳይሆኑ የግለሰቦች ሃሳብ እና አካሄድ የሚያመጣው በጎ ወይ መጥፎ ተፅዕኖ ነው። በጎ ወይም መጥፎ ተፀዕኖ ያመጣውን የሰዎችን ስራ በተመለከተ ስንነጋገር የሰዎችን ስም ማንሳታችን ደግሞ አይቀርም። በጎውን ስራ ስናወድስ፤ መጥፎው ስራ ወደ ባሰ መጥፎ እንዳያድግ ልንነጋገርበት ስናነሳሳው ከግለሰቦች ጋር የተለየ ፀብ ወይም … [Read more...] about ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
አዴፓ ህወሓትን በልኩ በሚገባው ስም በመጥራት አዋርዶ ቀበረው
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ብቸኛ ጠላት የሆነውን ህወሓት በሚገባው ስም መጠራት አለበት በማለት በተደጋጋሚ ሲወተውት ለመኖሩ ያለፉትን ጽሁፎች መመልከቱ በቂ ግንዛቤ ይሰጣል። በመሆኑም ህወሓት (የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) በሚለው የተገንጣይ ስሙ አገር በግፍ እየገዛ ያለ የወንበዴዎች ስብስብ ነው በማለት በዚሁ ስሙ እንዲጠራ ብዙ ብለናል። ይህ የአሸባሪዎችና በሞራል ዝቅጠት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ባሉ ርካሾች የሚመራ የወሮበሎች ድርጅት በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን ያከለ ታላቅ አገር በንቀት እየገዛ ያለ ነው በማለት አትተናል። በመሆኑም ይህ በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች ቋት ውስጥ እስካሁን ድረስ ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መታደስ ሳይሆን መታገድና መክሰም ያለበት መሆኑንም አበክረን አሳስበናል። ይህ የእኛ ብቻ ሳይሆን የበርካቶች … [Read more...] about አዴፓ ህወሓትን በልኩ በሚገባው ስም በመጥራት አዋርዶ ቀበረው
ህወሓት ወደ ስልጣን ለመመለስ የሎቢ ሥራውን ዳግም ጀምሯል
የተከበራችሁ የጎልጉል አንባቢያን፤ ለወራት ጠፍተን በመቆየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን። አንዱና ዋንኛው ምክንያት ድረገጻችን በማደስና የምናትማቸውን ጽሁፎች ባዲስ መልክ ለማድረስ እየሠራን ስለነበር ነው። ሥራው በፈቃደኝነት የሚሠራ በመሆኑ ካሰብነው ጊዜ በላይ ቢወስድብንም ባሁኑ ጊዜ በመጠናቀቅ ይገኛል። በቅርቡ አዲሱን ድረገጻችንን እናስተዋውቃለን። እስከዚያው ግን እዚሁ ላይ እንደተለመደው መረጃዎችን ማተማችንን እንቀጥላለን። በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁንና መልዕክቶች ለላካችሁልን ምስጋናችን የላቀ ነው። ከልብ እናመሰግናለን። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ። በኢትዮጵያ ከፖለቲካው ቀውስ በማያንስ መጠን የኢኮኖሚው መላሸቅ፣ የሥራአጥነትና ድህነት የሚያስከትሉት አደጋ አሳሳቢና አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ። የለውጡ ኃይሎች ለውጡን በሚያደናቅፉ ላይ ፈጥነው እርምጃ አለመውሰዳቸው … [Read more...] about ህወሓት ወደ ስልጣን ለመመለስ የሎቢ ሥራውን ዳግም ጀምሯል
በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
የአል አሙዲ ሃብት በ9.7 ቢሊዮን ዶላር ወደረ!
የኢትዮጵያን ሃብት ከህወሓት ጋር በጥቅም በመመሳጠር ሲበዘብዝ የነበረው መሐመድ አለ አሙዲ (አላሙዲ) እጅግ በርካታ ገንዘብ ከፍሎ በሌብነት ከታሰረበት ሳዑዲ አረቢያ መለቀቁ ተሰምቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሲታሰር 10.9 ቢሊዮን ዶላር የነበረው ሃብቱ ሲፈታ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በፎርብስ ደረጃ አሠጣጥ መሠረት ከእስር በኋላ የ159ኛ ደረጃ ሰጥቶታል። ሆኖም ፎርብስ የአላሙዲ ሃብት በእርግጥ የእርሱ መሆኑን ማረጋገጥ ስላልቻለ በ2018 ከዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ አውጥቶታል። በርካታዎች እየሞቱና መብታቸው ተገፍፎ በእስር እየማቀቁ በነበሩበት ወቅት የንብ ካኔተራ በመልበስ የህወሓት ደጋፊነቱን በገሃድ ያስመሰከረው አላሙዲንን ከህወሓት ለይቶ “የሕዝብ ሰው” አድርጎ ማቅረብ ለህወሓት ያለን “ጥላቻ” ከአላሙዲ “ትግሬ” አለመሆን ጋር የተገናኘ ይመስላል የሚሉ ጥቂቶች … [Read more...] about የአል አሙዲ ሃብት በ9.7 ቢሊዮን ዶላር ወደረ!










