በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
corruption
“የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአስፈጻሚውን አካል የሥራ ክንውን በተመለከተ ያቀረቡት ሪፖርትና ለጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። ሙሉውን ለመመልከት የቪዲዮው ምስል ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about “የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?
በሙስና ወንጀል በሚል በርካታ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ዘብጥያ የጣሉት የዙፋን ተስፈኛው የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በሳዑዲ ሚዲያ ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል። በአንዳንዶች ግምት በቤተመንግሥት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ይባላል። አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ አላሙዲንን “አስፈትተው” የመጡት ማንን አነጋግረው ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ በሥራቸው ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፤ ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት … [Read more...] about የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?



