የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው – ኦሞት ኦባንግ !! ኦሞት የዛሬ 14ዓመት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኙዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን … [Read more...] about አሁንም ይፈለጋል!
tplf
ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው
አባቶች “ሥራ ለሠሪው እሾህ ለአጣሪው” እንዲሉ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት ዘረኝነትን ፖሊሲው ያደረገው ህወሃት ለሃያሰባት ዓመት ኮትኩቶና ውሃ እያጠታ ያሳደገው ዘረኝነት ወይም የጎሰኝነት ገመድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ መተንፈሻ እያሳጣው ነው። ሰው በሰውነቱ ከዚያም ዝቅ ሲል በዜግነቱ ወይም በኢትዮጵያዊነቱ መከበር ሲኖርበት፣ ህዝቡን በጎጥ አጥር ከትቶ እርስ በርሱ እንዲጋደል ወያኔ ሌት ተቀን ሠርቷል። ለዘመናት የቆየው ኢትዮጵያዊ ትስስርና ባህሉ ህዝቡን በአንድነት ቢያቆየውም ብዙ ዜጎች በማንነታቸው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተሰደዋል፣ ተንገላትተዋል። ጊዜ ይውሰድ እንጂ ኢትዮጵያውያን የወያኔ ተንኮል ከመረዳት አልፈው በቃህ በሚል ፍጻሜውን ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዓለምን ያስደነገጠው የሩዋንዳ እልቂት ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸውን ሩዋንዳውያን ቅኝ … [Read more...] about ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው


