• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

tplf

ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ

November 20, 2019 02:05 pm by Editor 2 Comments

ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ

"ሳይወሰንልኝ" አልሳተፍም አለ  የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ/ህወሓት በቀጥታ መቃወሚያ ሳያቀርብ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች እንዲዋሃዱ በሚወሰንበት የግንባሩ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ፈቃድ አለማግኘቱን አስታወቀ። ይህንኑ የሚጠበቅ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ በተዘዋዋሪ ቀን እንዲሰጠው መጠየቁንና አሁንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ማብራሪያ ያላቀረበበትን የህግና የፖለቲካ ጉዳይ አስታኳል።  በህዳር 6 ቀን 2012 የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ በውህደቱ አጀንዳ በድምጽ ተሸንፎ የወጣው ህወሃት የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ከስብሰባው ማግስት በኋላ ሲያስተባብል የቆየው ትህነግ፣ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ “የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ በጥናቱ ላይ እንዲወያይ ተወስኖ እያለ ምንም ዓይነት ውይይት ሳይደረግ በጥድፊያ የምክር ቤት ስብሰባ ማድረግ ተገቢ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ

Filed Under: News, Politics Tagged With: eprdf, Full Width Top, Middle Column, tplf

በአማራና ትግራይ ህዝብ መካካል አብሮነቱ እንዲጠናከር የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ

November 17, 2019 07:53 pm by Editor Leave a Comment

በአማራና ትግራይ ህዝብ መካካል አብሮነቱ እንዲጠናከር የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ

በአማራና በትግራይ ክልል ህዝቦች መካካል ለዘመናት የዘለቀው የአብሮነት እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁለቱ ክልሎች መንግሥታትና ፖለቲከኞች ልብ ለልብ ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ተናገሩ። የጎንደር ከተማ አስተዳደር በከተማው ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ፣ ክልላዊና ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንደተናገሩት መንግስትና የፖለቲካ ስርአት አላፊ ሲሆኑ፤ ህዝብና አገር ግን የሚቀጥሉና የታሪክ ባለቤት ናቸው። “ጎንደር ያደኩባት፣ የሸመገልኩባት፣ ልጅ ወልጄና አሳድጌ ለወግ ማዕረግ የበቃሁባት ህዝቡም በፍቅር ያኖረኝ ከተማ ነች” ያሉት አቶ ወልደገብርኤል ተክኤ የተባሉ ነዋሪ ናቸው። “በኖርኩባቸው 40 ዓመታት በከተማው አማራ እና ትግሬ … [Read more...] about በአማራና ትግራይ ህዝብ መካካል አብሮነቱ እንዲጠናከር የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar, tplf

ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!

November 17, 2019 07:48 am by Editor 1 Comment

ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!

ሦስቱ ፓርቲዎችና አጋር ድርጅቶች አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል ህወሃት “በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢህአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገርን የሚበትን ተግባር ነው” ሲል ጉዳዩ የሞት ሽረት መሆኑንን አስታውቋል። አሁን ግጭት እየተባባሰ የሄደውም በዚሁ ምክንያት ነው ሲል አክሏል። እስከ ዛሬ ከውህደት ተገለው የነበሩ አጋር ድርጅቶች በኢህአዴግ ሥር ተጠቃለው እንዲቀጥሉ ምኞቱን ያኖረው ህወሃት፤ አጋር ፓርቲዎች ስለምን ተገለው እንደቆዩ ቁጭቱንም ሆነ ምክንያቱን በመግለጫው አላካተተም። ሰሞኑንን አጋር ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ፣ ሶስቱ እህት ድርጅቶች ውህደቱን እንደሚደግፉና እንደሚቀላቀሉ ይፋ ማድረጋቸውን በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ ያላስቀመጠው የህወሃት መግለጫ “ውህደቱ አገር ያፈራርሳል፣ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ” ከማለት … [Read more...] about ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!

Filed Under: News, Politics Tagged With: EPP, eprdf, Left Column, tplf

የዶ/ር አሚር የ“በቃኝ” ጥያቄ፤ የ“ዘይት አስገባልኝ” ጥያቄ!!

November 16, 2019 03:14 am by Editor 9 Comments

የዶ/ር አሚር የ“በቃኝ” ጥያቄ፤ የ“ዘይት አስገባልኝ” ጥያቄ!!

አማራ ክልል የሚሸጥ የምግ ዘይት አነጋጋሪ እየሆነ ነው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትም ሆነ የሚመሩት ተቋም፣ እንዲሁም ራሳቸው በግልጽ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጡም። ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ባደረገው ማጣራት የዶ/ር አሚር መልቀቂያ ማቅረብ ትክክል መሆኑንን ለማወቅ ችሏል። በዚሁ መሠረት ሚኒስትሩ “በቃኝ” ማለታቸው በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሲባል እንደከረመው ከአዴፓ ጋር በተያያዘ ሳይሆን የመገልገያ ጊዜው (expiry date) ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩት የምግብ ዘይት አገር ቤት ለማስገባት ከአንድ ባለሃብት የቀረበላቸውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረጋቸው ነው። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዜና አቀባይ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑትን የመረጃ አጋሮቹን ጠይቆ ሪፖርት እንዳደረገው ከውጭ … [Read more...] about የዶ/ር አሚር የ“በቃኝ” ጥያቄ፤ የ“ዘይት አስገባልኝ” ጥያቄ!!

Filed Under: News Tagged With: amir aman, cooking oil, Full Width Top, Middle Column, tplf

ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!

November 14, 2019 09:37 pm by Editor Leave a Comment

ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!

በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) “እንደቀልድ፣ ሳናውቀው አገራችን ወደ ፍርስራሽነት ተቀየረች” አለ፣ አንድ ታዋቂ የየመን ጋዜጠኛ፤ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ። ነገሮች የረዥም፣ ተከታታይ ሂደት ውጤት ወይም መጨረሻ ናቸው፤ የድንገቴ ክስተት አይደሉም። ጦርነት ያለመግባባትና የቅራኔ ሂደት ውጤት ነው። ሞት ከጤንነት ጀምሮ፣ እየጠነከረ የሚሄድ ህመም ሒደት ውጤት ነው። በሥርዓትና ደንብ የቆመ ሀገር መፍረስም እንዲሁ የረዥም ጊዜ፣ ተከታታይ ከሥርዓትና ደንብ ማፈንገጥ ሒደት ውጤት ነው። የሀገር መሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች . . . ሁላችንም፣ “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያልን እንጮሀለን። ከጩኸቱ ጀርባ የቻሉትን እያደረጉ ያሉት ግን የሀይማኖት አባቶች ብቻ ናቸው፤ ዕንባቸውን ሽቅብ ወደ ፈጣሪ መንበር እየረጩ የመንፈስ ልጆቻቸውን ይለምናሉ፤ ምእመኑን በጸሎትና በጾም ያተጋሉ። ፖለቲከኞች … [Read more...] about ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar massacre, Right Column - Primary Sidebar, sanaa, tplf, yemen

ሐሜትን በዜናነት ሲዘግብ የኖረው የሐሰት ዜና በመፈብረክ ተጠምዷል

November 14, 2019 09:21 am by Editor 4 Comments

ሐሜትን በዜናነት ሲዘግብ የኖረው የሐሰት ዜና በመፈብረክ ተጠምዷል

“የሚዲያው” ባለቤት በሼራተን የቪአይፒ ተስተናጋጅ ሆኗል የ“ሹክሹክታ” (ጎሲፕ ወይም ሐሜት) አምራች በመሆኑ ትልቅ ዋጋ የተሰጠውና በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓመቱን ሽልማት የለገሰው ዘ-ሐበሻ ትላንት “በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ” ሲል ያሰራጨው ዜና ፍጹም ሃሰት መሆኑንን ዩኒቨርሲቲው ባሰራጨው የማስተባበያ ዜና ይፋ አደረገ። የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት የዚሁ “ሚዲያ” ባለቤት ነው የሚባለው ሔኖክ ዓለማየሁ በሸራተን አዲስ በልዩ የዕንግዳ መስተናገጃ /ቪአይፒ/ ሲስተናገድ እንደሰነበተ አስታውቀዋል። “ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በተነሳ ብጥብጥ ምክንያት ሁለት ተማሪዎች በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል” በማለት ዘ-ሐበሻ የሐሰሰት ዜናውን ሲረጭ በስምንት ሰዓታት ውስጥ 556 ሰዎች ስሜታቸውን የገለጹ፣ … [Read more...] about ሐሜትን በዜናነት ሲዘግብ የኖረው የሐሰት ዜና በመፈብረክ ተጠምዷል

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, jawar massacre, Middle Column, tplf, ze habesha

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ

November 9, 2019 03:45 am by Editor 2 Comments

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ

የኢትዮጵያ መንግሥት ባፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ተብሏል ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትሕነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ። መረጃው የአፍሪኮም አዛዥ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተመካከሩ በኋላ መውጣቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው ተብሏል። “ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ፡- ጄ/ል ሳሞራ ዬኑስ በሱዳን 8ሺህ ወታደር እያሰለጠኑ ነው!” በማለት Ethiopian Think Thank Group የተሰኘው ድረገጽ ዛሬ ባስነበበው መሠረት መረጃው የተገኘው ከደኅንነት ሠራተኛ መሆኑን ተናግሯል። … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ

Filed Under: News, Politics Tagged With: abiy ahmed, africom, Full Width Top, Middle Column, terrorism, tplf

ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

November 6, 2019 09:21 am by Editor Leave a Comment

ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው። ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት … [Read more...] about ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre, Left Column, tplf

የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

November 5, 2019 07:01 pm by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት 30 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች! ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ መሸሸቱንና ገንዘቡንም ለማስመለስ መንግሥት ከባድ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀገር የሸሸውን ገንዘብ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ቢጠይቅም መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለው አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዳልታዬ ምሁራኑ ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ እንደገለጹት በኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት በሙስና እና ማጭበርበር የሸሸው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጧል፤ ገንዘቡም በወቅቱ የኢትዮጵያን የስድስት ዓመት ተኩል በጀት መሸፈን የሚችል … [Read more...] about የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: 30 billion, Right Column - Primary Sidebar, tplf

መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!

November 1, 2019 04:09 pm by Editor 3 Comments

መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!

የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!

Filed Under: News, Uncategorized Tagged With: Full Width Top, jawar, jawar massacre, meles, meles zenawi, Middle Column, oromo, tplf

  • « Previous Page
  • Page 1
  • Page 2
  • Page 3
  • Page 4
  • Page 5
  • …
  • Page 16
  • Next Page »

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule