የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር፣ ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መሥራቱ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሠራው፣ በአካባቢው የሚተላለፈው የሕዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ሕይወት (ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም) ለመታደግ በሚል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ሦስተኛ መሸጋገሪያ ድልድይ የሠራው ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወደ ራስ መኰንን፣ ወደ አዲሱ ገበያና ወደ አፍንጮ በር (ውቤ በረሃ) በሚወስደው አደባባይ ላይ ነው፡፡ ይህ መሰላል አቀማመጡ ወይም የተሠራበት አቅጣጫ ለተጠቃሚው አመች ባለመሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቀሙበት የሚስተዋሉት … [Read more...] about ‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የፈረሰው መሸጋገሪያ
Right Column - Primary Sidebar
የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
1. መግቢያ ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው:: በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው:: አንደኛው አስተሳሰብ የሚያጠነጥነው የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄው የሚካትተው ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትንና በደሎችን እንዲሁም በያ ትውልድ ውስጥ የተፈፀሙ መጠፋፋትን አካቶ ሁሉን-አካታች መድረክ በማዘጋጀት ያለፈውን በደሎች ዕውቅና በመስጠት በፖለቲካ ሊህቃን መካከል መግባባትን ማስፈንን ነው:: ሁለተኛው አስተሳሰብ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በአዲስ መሰረት … [Read more...] about የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
እጅ-ለጅ!
የፊት ጉዱን ረስቶ፣ ከረሀብ መትረፉን፣ የሙሴን ውለታ የእናት ጡት ነካሽ ልጅ፣ ፈርዖን በእስራኤል፣ ክንዱን አበረታ! መሄጃ ያጣህ ዕለት፣ ኢትዮጵያ አትርፋልህ፣ ዕምነትህ እንዳትጠፋ! ስማን እንጂ ሳውዲ፣ አንተም እንደፈርዖን፣ ታዋርዳት ገባህ፣ አገሬን በይፋ? ደግ እናት ነበረች፣ አንጀቷ የሚራራ፣ እግዚአብሔርን ፈሪ ኢትዮጵያ አገሬ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ የሰው ልጅ አፍቅሪ አቅፋ የምትደብቅ፣ የተሰደደውን፣ ላትሰጥ ላባራሪ “ዕድሜ” ለወያኔ፣ ዛሬ ግን ቀን ጥሏት፣ ለጆቿ ተርበው፣ ሆኑ ጦም አዳሪ። አይ ስምንተኛው ሺ፣ የዘመን ጎዶሎ፣ ያመጣብን ጣጣ አንተም ቀን አልፎልህ፣ አሽከርና ገረድ፣ ከኢትዮጵያ ታስመጣ? እሱስ እሺ ይሁን፣ ምነዋ መርሳትህ፣ ያቺን ክፉ ዘመን ጌዜው ተለዋውጦ፣ እኛም ለአንድ እንጀራ፣ በእጅህ ላይ ሲጥለን። ዕምነትክን ረስተኸው፣ ትዕዛዙን ጥሰህ፣ … [Read more...] about እጅ-ለጅ!
ሞት፣ ወያኔና “እኛ”
የግፍ ጽዋው ሞልቶ፣ …… ሞልቶ፣….. ሞልቶ ፈሶ ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ ከ'ጥናፍ- እስከ-አጥናፍ፣ ደማችን “'ረክሶ’’፤ ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ እዩት ይ'ጣለላል፣ አስፋልቱን አልብሶ። ግን እኮ፣ …….. እንኳ’ ደም ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም:: '' ዓለም የም'ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።" /አልበርት አነስታየን/ እናም የምድርን የሰቆቃና የሞት አይነት ሁሉ እያስከፈሉን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን እያጠፉ ያሉት፣ ወያኔ/ሻአቢያ፣ ሳውዲ አረቢያ/ አረቦች፣ ምእራቡ ዓለም፣ ወይም ሌላ ሳይሆን፣ እኛ እራሳችን ቁጭ ብለን የምንመለከተው ወይም ለታይታ የምንታይው፣ ኢትዮጵያዊያኖች ነን። እኛ ነን….. በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን … [Read more...] about ሞት፣ ወያኔና “እኛ”
“አቤቱ እንዳንጠፋ አድነን”
የርዕሰ አድባረት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ በሳውዲ አረቢያ ባለው በኢትዮጵያውያ ወገኖቻችን ላይ በሚደርሠው ኢሰብዓዊ አሣዛኝና ዓሠቃቂ መከራና ሞት እንቃወማለን:: (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “አቤቱ እንዳንጠፋ አድነን”
በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀጥሏል
ሪያድ አሚራ ኑራ ዩኒቨርስቲ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ሜዳ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ። ሪያድ መንፉሃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ሰሞኑንን በሳውዲ ፖሊሶች ታፍሰው ከከተማይቱ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኝ፡ በተለምዶ ሚንዛህሚያ እየተባለ የሚጠራ እስርቤት ተወስደው ከነበሩ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን መሃከል ግማሽ ያህሉ በ17 አውቶብስ ተጭነው ማምሻውን ሪያድ ከተማ አሚራ ኑራ እየተባለ የሚጠራ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተከትሎ ከባድ ሁከት መቀስቀሱን ከሪያድ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህን ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል ከባድ ግጭት መከሰቱን የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች አዲት ነፍሰጡር ሴት ከድንጋይ ውርወራው … [Read more...] about በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ቀጥሏል
ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ። በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል። አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ … [Read more...] about ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ
Open Letter to Ethiopian Foreign Minister
Re: Abuse of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) is concerned about the recent abuse of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia, especially the reported torture, abuse and rape of Ethiopian women. CREW is a non-government, non-profit, non-partisan, human rights and peace organization established to promote the social, economic and legal rights of Ethiopian women in Ethiopia and worldwide. One of the objectives of the organization is to … [Read more...] about Open Letter to Ethiopian Foreign Minister
እንደማያልፍ የለም
አዎ፤ የኔም እምባ ፈሷል እምነቴ ደፍርሷል ሰበዕናየ አንሷል ምክንያት ፍለጋ - መፍትሄ ፍለጋ ቀኑ እስከሚጨልም - ሌሊቱ እስቲነጋ ብቆርጥ ብቀጥል - ባነሳ ብጥለው ዘላለም ሆነብኝ - ማለቂያ የሌለው ሕመምሽ አሞኛል ድካምሽ ደክሞኛል እምባሽን ለመጥረግ - አቅም በማጣቴ ሕሊናየ ቆስሏል - ተቃጥሏል አንጀቴ እና….ጠንክሪ እህት ዓለም ይሄም ቀን ይረሳል - እንደማያልፍ የለም … [Read more...] about እንደማያልፍ የለም
በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን
ዘግናኙ የስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ግፍ በሳዑዲ አረቢያዊያን እጅ፤ ከፊታችን ተደቅኗል። ሁላችን በያለንበት፤ “ለምን? ምን አደረግን? መጨረሻው ምንድን ነው? መቼ ነው ይኼ ሁሉ የሚያበቃው?” እያልን እርስ በርሳችን እየተጠያየቅን ነው። እኛ ወደ የምንፈልገው መንገድ ካልገባን፤ ሌላ ሊይስገባን የሚችል ኃይል የትም የለም። በሳዑዲ አረቢያ የተደረገውን ኢሰብዓዊ ድርጊት፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያን በግል በራሷና በራሱ እንደተደረገ በደል አድርገን ወሰደነዋል። ተገቢም ነው። ኢትዮጵያዊያን እንደ ትቢያ ተረገጥን፣ ተዋረድን፣ ተገደልን። እናም አንድ ነገር ማድረግ አለብን። ሀገራዊ መልስ ሠጪ መንግሥት የለንም፤ ሀገራችንን የሚወክል መንግሥት የለንምና። እኛ ግን በኢትዮጵያዊነታችን ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት አለብን። ኃላፊነታችን እስከምን ደረስ ነው? የሚለውን በዚህ ጽሑፍ እቃኛለሁ። በሳዑዲ አረቢያ … [Read more...] about በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን










