በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጀመረውን ፍተሻ በማረጋገጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በአስቸኳይ ለጸጥታ አስከባሪዎች እጅ በመስጠት ወደ መጠለያ በመግባት ወደ ሃገር እንዲገቡ ማምሻውን ባወጣው ማስታወቂያ አሳስቧል። ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በሪያድ መንፉሃ በኤምባሲውና በሃገር ሽማግሌዎች የተቋቋሙ የመረጋጋት ኮሚቴ አባላት ወደ መንፉሃና ኢትዮጵያውያን በሚበዙባቸው መንደሮች በመንቀሳቀስ ዜጎች ያለ ምንም ጉዳት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሃገር ለመግባት እንዲዘጋጁ የመከረ ቢሆንም ጥረቱ አልተሳካም ነበር ። የሪያድ ኤምባሲ የሽማግሌዎች ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ቅስቀሳ ወደ ሃገር ለመግባት ባልተጨበጠ ተስፋ የተዘናጉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያልያዙ ወደ ሃገር በመግባቱ ላይ እንዳያቅማሙ መምከራቸው ይጠቀሳል! አሁን በተጀመረው የመንፉሃ ፍተሻ ማዋከብ የለበትም። ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ … [Read more...] about ረቡዕ ምሽት በመንፉሃ ዙሪያ መጠነ ሰፊ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ!
Right Column - Primary Sidebar
የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ
ክፍል አንድ ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ የሚኖረውን ገጽታ እና ትርጓሜ ማስቀመጥ ያስቸግራል። አንዱ ሰው የሚፈራውን ነገር ሌላው ላይፈራው ስለሚችል ፍርሃት እንደ የግለሰቡ ባህሪ እና ጥንካሬ ወይም ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ የተለያየ መልክ ይኖረዋል። ይሁንና በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚጋሩት ባህልና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ እንደመኖሩ ሁሉ የሚጋሩትም ፍርሃት ወይም ደስታ ወይም ሃዘን ወይም ድፍረት ወይም ሌሎች ባህሪያት ይኖራል። በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሰዋዊ ባህሪያት ለአንድ ማህበረሰብ ወይም ለበርካታ ሰዎች የወል መገለጫ ተደርጎ ሲገለጽ ይስተዋላል። ‘የዚህ አካባቢ ሰዎች ጀግኖች ወይም ጸብ ፈሪዎች ወይም እሩህ ሩህዎች ወይም ጨካኞች ወይም ቂመኞች ወይም ገራገሮች ወይም ተንኮለኖች ወይም ጎጠኞች ወይም ሌላ ባህሪ ያላቸው ናቸው’ የሚል አገላለጽ … [Read more...] about የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በመላው UKየምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ሁሉ። በስደት ላይ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ጥረት፤ ድካምና ተጋድሎ አማካኝነት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘረጋው የጎሳ ፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር ሳትወድቅ በአስተዳደር ራሷን ችላ በመመራት ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃችው አንጋፋዋ የለንደን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ለወያኔ ባደሩ ጥቂት ባንዳ ካህናትና ተከታዮቻቸው አማካኝነት ገንዘብና ጉልበታቸውን አስተባብረው፤ ጥረውና ግረው የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለቤት ካደረጓት አባላቷ ተነጥቃ የወያኔ አገዛዝ ሹመኞችና ደጋፊዎች ንብረት እንድትሆን የሚካሄደው ጥረት ቀጥሎ … [Read more...] about ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?
ፖለቲካ የሚለው ቃል የባዕድ ቃል ነው እምነተ-አሥተዳደር ማለት ነው፡፡ ከባዕድ ከመምጣቱም ቃሉንና ተግባሩን በመልካም ጎኑ ቀምሰን ሳናጣጥመው ወዲያውኑ ምሬቱን ስላሳየን ለቃሉና ለተግባሩ መልካም ስሜት የለንም፡፡ አንድ አባባልም ፈጥረንለት ከሥነ-ቃሎቻችን ቀላቅለንለታል ‹‹ፖለቲካንና ኮረንቲን በሩቁ ነው›› የሚል፡፡ በእርግጥ ግን ፖለቲካን ርቆ መራቅ ይቻላል? ለዚህ ቃልና ለተግባሩ ባለን ጥሩ ያልሆነ አመለካከት የተነሣ ፖለቲካ ያለውን የሀገርንና የሕዝብን እጣ ፈንታ የመወሰንን ያህል ግዙፍ አቅምና ሚና ዘንግተን ፖለቲካንና ፖለቲከኛነትን ጭንቅላታችን ውስጥ የጭራቅ ምስል ሥለን በመፍራት በመጥላትና በመሸሽ በዜግነታችን ለሀገራችን ልናበረክተው የሚገባንን ተግባርና አገልግሎት እንዳናበረክትና ሀገሪቱም በፖለቲካ ምክንያት ከሚከሰቱ ትብትብ ችግሮች እንዳትወጣ አድርጓታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ … [Read more...] about ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?
የክፉ ቀን አለኝታዋ ትዝታ
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about የክፉ ቀን አለኝታዋ ትዝታ
ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …
የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ... እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ፣ እግር በጣለኝ የሳውዲ የቀለጡ በርሃዎች ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ። ላፍታም ቢሆን ጊዜ ሰጥቼ እየኖሩት ስላለው ኑሮ፣ እየገፉት ስላለው ክፉም ደግ ተሞክሮ እጠይቃቸዋለሁ አንድም ሳይደብቁ የሆድ የሆዳቸውን ያጫውቱኛል ... እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ መካከል በምትገኝ የዋዲ በርሃ ዙሪያ ነበር ። አየሩ ተቀያይሯል፣ ከዚህ ቀደም ወደዚህ ቦታ ሳመራ እንደ እሳት ነበልባል የሚጋረፈው ሙቀት ዛሬ የለም። ለስራ ወዳቀናሁበት በድቅድቁ በርሃ ላይ በተሰራው የድንጋይ መከስከሻ ፋብሪካ እንደደረስኩ አንድ መልከ መልካም ወንድም የግቢውን በር ከፍቶልኝ ለመግባት ወዴት መሄድ እንደምፈልግ ጠየቀኝ፣ ወጣቱ ሃበሻ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል … [Read more...] about ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …
Time to Bring Eritrea in from the Cold
Eritrean President Isaias Afewerki has stated that ‘Eritrea cannot fulfill its destiny without Ethiopia.’ After being part of Ethiopia for forty years, the people of Eritrea held a referendum in April 1993 and decided to establish an independent state. The referendum took place in the aftermath of a thirty-year insurgency against two successive Ethiopian regimes waged by the Eritrean Peoples Liberation Front (EPLF). At the same time, an allied insurgent group, the Tigrean Peoples Liberation … [Read more...] about Time to Bring Eritrea in from the Cold
ጉቦ በመቀበል እስረኞችን የለቀቁ ታሰሩ!
ከ300 እስከ 500 ሺህ ብር እየተቀበሉ በሀሰተኛ ሰነድ ታራሚዎችን ከማረሚያ እንዲወጡ አስደርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የስራ ሀላፊዎችና አምስት ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ ኦፊሰር ገብረመድህን አረጋ፣ ረዳት ኦፊሰር ኢሳያስ ከበደና ዋርደር ኢብራሂም መሀመድ ሲሆኑ፥ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የእስረኞች አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ የስራ ሃላፊዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የተቀሩት ግለሰቦች ደግሞ ፥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ ሰለሞን ገለታ፣ አቶ ብሩክ ሀይሌ፣ ወይዘሪት ሳባ ገብረሚካኤል፣ አቶ ናታን ዘላለምና አቶ ቴዎድሮስ ግደይ ናቸው። የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት … [Read more...] about ጉቦ በመቀበል እስረኞችን የለቀቁ ታሰሩ!
አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት:: ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ:: በእርግጥም ሳውዲዎች ጨካኞች ናቸው ስራቸውም እጅግ አሳፋሪ ነው:: … [Read more...] about አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !
‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)
አቶ ተማም አባ ቡልጉ ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት ቁጥር 128 ህዳር/2006 ዕትም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ አዲስ ጉዳይ፡ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደ ታህሳስ 3 ሲዛዋወር እንደ ጉዳዩ ዓቃቤነትዎ እንዲያውቁት ተደርገው ነበር? ተማም፡ በፍጹም ለእኔ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራ ጠበቃ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ ‘ጉዳዩ እንዴት ነው?’ ሲለኝ አይ እዚያው ነው ብዬ ሳረጋግጥለት ‘አረ ፍርድ ቤቱ ባዶ ነው’ የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ አንዳንድ ጠበቆች ጋር ስደውልም እከሌ የተባለ ጠበቃ እኮ ፍርድ ቤት በነበረበት ወቅት ከጽ/ቤት ተነግሮት ነበር አሉኝ፡፡ በዚህ ዓይነት መልኩ ነው ቀጠሮው መራዘሙን የሰማሁት፡፡ አዲስ ጉዳይ፡ በይፋ የተነገራችሁ ነገር የለም ማለት ነው? ተማም፡ ለእኛ በይፋ ምንም የተገለፀልን ነገር የለም፡፡ በፍርድ ቤት በይፋ … [Read more...] about ‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)










