ሀገራችን ካሏትና ሐበሻን እንደ ሐበሻ ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ ከሌሎች ተልይታ እንድትታወቅ ካደረጓት ታሪካዊና ባሕላዊ መለያዎቿ ምንጫቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በጉልህ ከሚታወቁት ባሕላዊ ኩነቶቻችን ውስጥ ሃይማኖታዊ አሻራ ያላረፈበት አንድም ባሕላዊና ታሪካዊ ክንውን እሴትና ቅርስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ይህ ሁኔታ በሌላ በኩል ሕዝቡን ሃይማኖቱን ከባሕሉ ጋር ማዋሐድና ማሰላሰል እስከመቻል የደረሰ ቅሩበ እግዚአብሔር ሕዝብ በማሰኘት አድናቆትን ሲያስቸረው ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ሀገራችንንና ሕዝባችንን እንደ ሀገርና ሕዝብ መለያው ወታወቂያው እንዲሆን ካደረጉት ድንቅና ብርቅ እሴቶች ውስጥ አሁን ህልውናቸው አደጋ ላይ ከወደቁት አንዱን አንስተን እናወራለን፡፡ የጥምቀት በዓል አከባበርን ፡፡ ሌሎቹን በሌላ ጊዜ እናያለን ፡፡ የጥምቀት በዓል ከሀገራችን ሌላ … [Read more...] about ጥምቀት ወይስ ካርኒቫል? ለምን?
Right Column - Primary Sidebar
የመረጃ ነፃነት?
‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡ መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡ በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም … [Read more...] about የመረጃ ነፃነት?
ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ … [Read more...] about ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል
የቦይ ስካውት ትዝታዬ
"አስካውት!..." "ምን ጊዜም ዝግጁ!!!" ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ እስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር፡፡ ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ እስካውት ክለብ አባል ነበርኩ፡፡ ፍቼ እያለን፣ የእስካውት ክለባችን ኃላፊ መምህር ወልዴ ይባሉ ነበር፡፡ በእግራችን ወደ ገጠር እየተጓዝን ድንኳንም ተክለን፣ ምግባችንን አብስለን፣ ሻይ አፍልተን እየተደሰትን አድረን እንመለስ ነበር፡፡ ማታ ማታም ደመራ ደምረን (Camp fire) ዙሪያውን ከበን እየጨፈርን፣ ግጥም የመግጠም ተሰጥኦ ያለን እየገጠምን ለጓደቾቻችን እያሰማን፣ አጫጭር የወዲያው ፈጠር ድራማም እያሳየን እንደሰት ነበር፡፡ ቀልዳ ቀልድም የሚያሰሙ ብዙዎች ነበሩ፡፡ በተለይም … [Read more...] about የቦይ ስካውት ትዝታዬ
Who is Seyyid Mohamed Abdillahi Hassan? An Ethiopian hero or a Somalia nationalist who championed for the goal “Greater Somalia”
Recently the Somali Regional government installed a statue in the middle of Jijiga town (the regional capital). This statue is for the 19th century “Somali patriot” who fought with all forces within the Horn of Africa. Historical books and literatures are full of the ideal he had waged battles and wars. In this short article I would like to consider whether he was an Ethiopian and deserve a multi-million dollar statue in the centre of the regional capital. And examine the legacy this man will … [Read more...] about Who is Seyyid Mohamed Abdillahi Hassan? An Ethiopian hero or a Somalia nationalist who championed for the goal “Greater Somalia”
ቴዲ አፍሮና የቢራው ፖለቲካ
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ ሳምንት አሰራጭቷል! ያለ አንዳች መረጃ። "ለነጮች እጄን አልሰጥም!" ብሎ አድዋ ላይ ስላዋረዳቸው ምኒሊክን ለማንቋሸሽ ምንም መረጃ አያስፈልጋቸውም። እልፍነሽ ቀኖ የተባለች የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ በአንድ ወቅት በለቀቀችው ነጠላ ዜማ ምክንያት ማእከላዊ እስር ቤት ታስራ ነበር። ምርመራውን የሚያካሂዱት ሰዎች በመጀመርያ የዘፈኑ ግጥም … [Read more...] about ቴዲ አፍሮና የቢራው ፖለቲካ
ጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን፡፡
የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሥራ ከመስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 9, 2009) ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ዕለታዊ የሱዳን ጋዜጣ ሱዳን ትሪቢውን (Sudan Tribune) በመስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. (September 18, 2009) መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ ያንገበገባቸው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩት ዜጎቻችንም ራሳቸውን በተለያዩ “ኮሚቴዎች” እና “ግብረ ሃይሎች” በማደራጀት ለጉዳዩ ክፈተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ፓርቲያችን (ሰማያዊ)፣ ለነዚህ ሀገር ወዳድ ዜጎች ያለውን ከፍተኛ አክብሮት ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት … [Read more...] about ጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…)
ጥሩ ግንኙነት ከሰዎች ለመፍጠር ማወቅ የሚገባህ የሚስጥሩ ተግባር አመለካከትህ ያለህ አስተያየት ካፍህ የሚወጣው የንግግር ቃላት ከፍላጎትህ ጋር ግጭት እንዳይፈጥር አጢነህ ተመልከት እራስህን መርምር እራስህ እራስህን ማርካት ከተሳነህ ለሰው የምትሰጠው ምንም ነገር የለህ አክብሮት ስትሰጥ እራስህን ስትወድ ሌላው እንዲያከብርህ ትፈጥራለህ መንገድ ስለራስህ መጥፎ ነገሮች ስታስብ ለሰዎች ያለህን ፍቅር በመገደብ ለነገር ጫሪዎች ስሜት ለሚያስቆጡ መንገድ ትከፍታለህ ወዳንተ እንዲመጡ የሰዎችን ድክመት አጋነህ ከመውቀስ ጥንካሬአቸውን ጠቅሰህ ስታሞግስ አንተ በምትሻው በፈለከው መንገድ ይተባበራሉ አብረውህ ለመሄድ እንግዲህ ወዳጄ ይሄ ነው ሚስጥሩ ትልቁ ብልሀት አብሮ ለመኖሩ። ****************************** The Secret (ሚስጢሩ…) … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ማንነት (identity)
አዲሱ ዓመት መጣና ፤ ጎረቤቴን የሰፈሬን ልጅ እንኳን አደረሽ ብላት ፤ መልካም ምኞቴን ሳውጅ እኛን አያገባንi ብትለኝ ፤ እንዴት? ለምን? ብየ ጠየኳት አታውቅም ? በእኛ ሃይማኖት ፤ ጃንዋሪ ላይ ነው አዲስ ዓመት ብላ ብትለኝ ደንግጨ ፤ ሆኘ ቅርት የጨው ሀውልት አየ አዲስ ዓመት እንቁጣጣሽ ፤ በምድሪቱ ሳይቀር ተበሳሪ ተፈጥሮ አጅቦ የሚያመጣት ፤ በአበባ ልምላሜው ከባሪ የእኛ አይደለሽም ተባልሽ ? እዚሁ በምድርሽ በቅሎ ማዛሽ ማዛው ላይ እየናኘ ፤ ከአፈር አየርሽ ኮብልሎ ምን ሳይሰማ እንዲሉ ፤ እንዲህም መቷላ ጉድ ፈጦ መለያን ከስሩ ነቃቅሎ ፤ ልብን ከልብ ላይ ቆርጦ አሁን ይህችን ልጅ እኅቴን ፤ ማን ናት ምን ብየስ ልጥራት እነሱስ ሰባኪዎቿ ፤ ሰላዮቹ የቅኝ ግዛት ማን ብለው ይሆን ትውልዷን ፤ የሷን ዜግነት … [Read more...] about ማንነት (identity)
ባለቤቱን ከአልናቁ . . .
መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ያወጣውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ባለቤቱን ከአልናቁ . . .










