ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ። ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: አለማየሁ መሰለ ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ) ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ በዚህ ጉዳየ ላይ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ካወጡት ዘገባ ጋር በማያያዝ ተስፋዬ ገ/አብ እንደ … [Read more...] about ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?
Right Column - Primary Sidebar
ኳሱ በማን እጅ ነው?
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤ በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሻለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም … [Read more...] about ኳሱ በማን እጅ ነው?
ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
(ይህንን ጽሁፍ በከፊል ከሁለት ዓመት በፊት በ16-08-2011. "ሁለቱም መስመሮች ይጎዱናል" በሚል አርዕስት አውጥቼው በተለያዩ የኢንተርኔት ድኅረ ገጾች ተነቦ የነበረ ቢሆንም፣ አብዛኛው ጽንሰ ሃሳብ፣ ሰሞኑ እየተካሄደ ካለው ጽንፈኛ የጎጥ ፖለቲካ ጋር፣ ብዙ ተያያዥነት ያለው ስለሆነ፣ አንዳንድ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይሄዱትን አስተካክዬ፣ ካሁኑ ሁኔታ ጋር አያይዤ ነው ያቀረብኩት፡፡ ፒዲኤፉ ብቻ ስለሆነ በእጄ የቀረውና ከፊሉን ማረም ስላልቻልኩኝ፣ ስለጥራቱ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡) ሰሞኑን በዲያስፖራ የፓልቶክ የውይይት መድረኮች፣ የአጼ ሚኒሊክንና እና ቴዲ አፍሮን በሚደግፉና በሚቃወሙ፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ ታዳሚዎች መሃከል ይካሄድ የነበረውን ውንጀላና፣ መከላከልን እኔም ለጥቂት ቀናት እያዳመጥኩኝ ስከታተል፣ ሁኔታው እንዳሳዘነኝ የገባት ባለቤቴ፣ ወንበሯን ስባ ተጠግታኝ፣ እሷም … [Read more...] about ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
“ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኘው የኩዩ ቀበሌ ግማሽ ያህል ነዋሪዎቿ አይነ ስውር የመሆን አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ በዚሁ መንደር በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆኑ ህጻናት በቤተሰባቸው ውስጥ የዓይን ችግር ያለበት ሰው እንዳለ ሲጠየቁ 20 ያህል ህጻናት እጃቸውን ያወጣሉ ይላል ዘገባው፡፡ የዚህ ሁሉ መነሾው ደግሞ ትራኮማ ነው፡፡ ቢበዛ በ10 ደቂቃ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊፈወስ የሚችለው ትራኮማ አንዳንዶች የድህነት በሽታ ይሉታል፡፡ በዓለማችን 2.2 ሚሊየን ህዝብ በትራኮማ ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣ ሲሆን በኢትዮጵያ ትራኮማ እጅጉን የተስፋፋው በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ 10 ደቂቃ የማይሞላውን ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ካላገኙ 200 000 ያህል የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ የሚለው … [Read more...] about “ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ
“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣልፍቅር ያሸንፋል-- የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነውእዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡ መነሻው ምንድነው? “አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤ የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣ ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣ አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…” እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት - ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን … [Read more...] about “ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
ህ.ወ.ሓ.ት. የኢ.ሕ.አ.ፓ. አመራርና ሌሎች ታጋዮች የጦር ምርከኞች በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር መልሶባቸው እንደቀበራቸው
ይህንን አሳዛኝና ዘግናኝ ዜና "ኢትዮሚዱያ" በመባል የሚታወቀው ድህረ ገጽ ላይ በጀነዋሪ 2014 ዓ.ም. ወጥቶ አንብቤአለሁ:: ህወሓት በኢ.ሕ.አ.ፓ አመራርና ላልች ታጋዮች የጦር ምርከኞችን በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር ተመልሶባቸው እንዲቀበሩ ማድረጉን ኢትዮሚዲያ አስነብቦናል:: ህወሓት ከዚህ የበለጠ ብዙ ዘግናኝና አሰቃቂ ድርጊቶችን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈፀመ እንንሆነ አስተርጓሚ የሚያሻው አይደለም:: (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ህ.ወ.ሓ.ት. የኢ.ሕ.አ.ፓ. አመራርና ሌሎች ታጋዮች የጦር ምርከኞች በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር መልሶባቸው እንደቀበራቸው
ግራና ቀኝ ጠፋን!
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡ በአደባባይ … [Read more...] about ግራና ቀኝ ጠፋን!
የጥምቀት በዓል
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ይሰብከዋል። በተለይ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት የጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አበው በሰሩልን ስርአት ከዓለም ልዩ በሆነ መንገድ እናንጸባርቀዋለን። በውስጡ ያዘለው ለወዳጅ ለጠላት የተሸከመው የመልእክቱ ይዘት እና ጥልቀት ምን ያህል እንደገባን እራሳችንን እንጠይቅ። ምክንያቱም ይህች ጦማር የተሸከመችውን ያባቶቻችንን ስሜት ለመናገር ለመመስከርና ትውልዱን ለማስተምር የሚጠይቅና የሚፈትን ከዚህ ዘመን የከፋ የለም። ስለ ጥምቀት በዓል ሁሉም የሚሰብከውን ሁሉም የሚያውቀውን በዚህች ጦማር ገልብጨና መልሸ በመናገር አንባቢን ማድከም አልፈልግም። ሲነገር ብሰማ ኖሮ ሰአቴን ባላጠፋሁ እኔም ባልደከምኩ ነበር። ይህ … [Read more...] about የጥምቀት በዓል
አዲስ ዓመት?
ከሁለት ሳምንታት በፊት የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንደገባ እናስታውሳለን፡፡ ይሄን ተከትሎ የአንዳንድ ድርጅቶች ሲገርመን ባልተለመደ መልኩ ጭራሽ ከሀገርና ከሕዝብ እሴትና ጥቅም አንጻር ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበትና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅበት የብዙኃን መገናኛውም (ሚዲያው) ይህንን የባዕዳኑን አዲስ ዓመት እድምተኞቻቸውም ማለትም አድማጭ ተመልካቾቻቸውም በዓሉን በማክበሩ እንዲቀላቀሏቸው በሚጋብዝ መልኩ በድምቀት አከበሩ፡፡ ይህ ስሕተት ጎልቶ ከታየበት የብዙኃን መገናኛዎች አንዱ ኢ.ቢ.ኤስ. በሚል አሕጽሮተ ቃል የሚጠራው የኬብል ቴሌቪዥን ነበር፡፡ በዚህ ቴሌቪዥን (ምርዓዬ-ኩነት) ከሚተላለፉ ዝግጅቶችና ይህን ስሕተት ከፈጸሙት ምስናዶች (ፕሮግራሞች) አንዱ “መቅዲ ሾው” (መቅዲ ትዕይንተ-ወግ) የተሰኘው ምስናድ ነበር፡፡ ጉዳዩ ትንሽ የሚያበሳጭ ስለነበር ለአዘጋጇ በፌስ ቡክ … [Read more...] about አዲስ ዓመት?
የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል
በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ - የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል? የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው? የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም? እና ሌሎችም... መግቢያ ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል:- ''ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል










