* የከተማዋ መብራት መቋረጥ ችግር የከተማዋ ዕድገት ነው * የችግሩ ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ነው * የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡና ግድቦች አለመሙላታቸው ነው ችግሩ * ለጥናቱ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል * ዕቅዱ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ተግባራዊ ይሆናል በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ 12 የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ከተሞች በየጊዜው የሚገጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል … [Read more...] about በአዲስ አበባ መብራት እንዳይቋረጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
Right Column - Primary Sidebar
በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
* የእናት 9 ዓመት ሰሚ ያጣ ጩኸት የ4 ዓመት ደልዳላ እያለ ድክ ድክ እያለ ሮጦ ለቀላል ህክምና ከጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አፍንጫ ስር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ገባ። ብዙም ሳይቆይ ከሰመመን መንቃት አልችል አለ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከሰመመን አልነቃም፣ በሃኪሞች ስህተት ብላቴናው መሀመድ ህይዎቱ ተሰናክሎ ላለፉት 9 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነል። ትናንትም ሆነ ከትናንት በስቲያም መሀመድና ቤተሰቦቹ ፍትህ ርትዕ ያገኙ ዘንድ ደጋግሜ ጠይቄያለሁ፣ ዛሬም እጠይቃለሁ! ላለፉት በዘጠኝ አመታት ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጀምሮ ሳይኖር "አለሁ" እስከሚለን የሴቶች ማህበር ተወካዮች ፍትህን ለመሀመድ ያስገኙ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ ፍትህ ማስገኘት ገዷቸዋል፣ ተበዳዮች ፍትህ ርቋቸዋል. . .! ክልትሙ ተንከባሎ ዛሬ ላይ ሲደርስ . . . ታሪኩን ከመሀመድ እናት ቃል በቃል ስሙት፣ ከዚህ ሁሉ … [Read more...] about በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
ሰሞኑን በታጋዩ ወገን ስለ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ እየተወራ ነው። ገና ብዙ እንደሚወራም አጠያያቂ አይደለም። ለምን ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ በኛ ትግል ሂደት፤ ይሄን የመሰለ ቦታ ይዘው እንደተገኙ፤ ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው። ነገር ግን፤ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው ስለኢትዮጵያና ስለሚደረገው ትግል ያላቸው ሃሳብ ተዘግቧል። በአንጻሩ ደግሞ ስላሳቸው የኢትዮጵያ ጠላትነትና የትግሉ እንቅፋትነት ምስክርነት የሠጡ አሉ። በዚህ ሂሳብ፤ እስኪ እኔም በውል የማውቀውን ላቅርብ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለመጀመሪያ ጊዜ ተከዜን ተሻግሮ ወልቃይት በገባ ጊዜ፤ ሸረላ ላይ ጦርነት ገጥመን ክፉኛ ቆስዬ ነበር። በዚህም ምክንያት፤ የነበርኩበት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት በጣም ተመናምኖ፤ ሕልውናው አስጊ በሆነበት ሰዓት፤ ለመሰባሰብ፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር - ጀብሃ - … [Read more...] about ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
The truth may not be black or white. It may be gray. And embracing this fact is good for Ethiopia. Here is my take as an independent voice. My heart is for Ethiopia to find a bridge in reconciliation and mutual understanding. The Story of White The government is joyful that it had secured 100% of the known seats yet (442). This story states that the people had given a green card to the government and thus empowers the government to continue with the status quo. The story dictates that the … [Read more...] about Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
የኢሕአዴግ ቁልቁለት
“ፋክት” መፅሔት ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆን በየሳምንቱ በወቅታዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን ወደ አንባቢ ሲያደርስ የነበረው ሙሉዓለም ገ/መድኅን አዲስ መጽሐፍ ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመፅሃፉ ርዕስ፡- የኢሕአዴግ ቁልቁለት ደራሲ ፡- ሙሉዓለም ገ/መድህን የገፅ ብዛት፡- 235 ዋጋ ለአገር ውስጥ፡- 52 ብር ለውጪ አገር፡- 20 ዶላር አጠቃላይ ይዘት መፅሃፉ በአራት ክፍሎች እና በአስራ አራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፣ ክፍል አንድ ላይ “ቁልቁለቱን በኢሕአዴግ ጎዳና” በሚል አምስት ምዕራፎች ተካተዋል፡፡ በዚህ ክፍል ብሶት ወለደኝ የሚለው ህወሓት ተነሳሁለት የሚለውን የትግል ዓላማ እንዴት እየቀለበሰው እንደመጣ በዝርዝር ያስቃኛል፣ በመስመር መሀል ከጫካ ጀምሮ የህወሓት የፖለቲካ አሽከር ስለሆነው ኢህዴን/ብአዴን ፖለቲካዊ ክሽፈት ያነሳል፣ ለቁጥር ብቻ … [Read more...] about የኢሕአዴግ ቁልቁለት
የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር
ደርግ 17 ዓመታት ሙሉ በህወሓት እና ሻብያ የተከፈተውን ጦርነት ሲዋጋ እንደነበር እና ጦርነቱ በቀን ብቻ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ያስወጣ ነበር። በመቶሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት መግቦ፣ ታንክ እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ነዳጅ እና ግዥ ፈፅሞ ማደር በራሱ ከፍተኛ ወጪ ነበር። ይህ ገንዘብ እንዳሁኑ የእርዳታ እና የብድር ገንዘብ ሳይሆን ህዝቡ ለእናት ሀገር እያለ ከሚያዋጣው እንደነበር ይታወቃል። በእርግጥ የሩስያ እርዳታ እና ብድር እንዳለ ሆኖ። በአንድ ወቅት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርይም የሰሜኑ ጦርነት ባይኖር በጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በባቡር ማገናኘት በተቻለ ነበር። ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል። በተለይ ህወሓት በዋነኛነት ድልድዮች እና መንገዶችን ማፍረስ ስራዬ ብሎ ይዞ ስለነበር እነርሱን ተከታትሎ መጠገን ሌላው ሥራ ነበር። የመከላከያ … [Read more...] about የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር
የምርጫና ነጻነት ቁልቁለት
* ከ45 ዓመት በፊት የፓርላማ ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች ሰማንያ አራት ዓመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ የመጀመርያው ሕዝብ በቀጥታ የተሳተፈበትና እንደራሴዎቹን የመረጠበት ምርጫ የተካሄደው በ1948 ዓ.ም. ነበር፡፡ በቀዳሚው ምርጫ ካሸነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዷ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ናቸው፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ወ/ሮ ስንዱ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት ዓመት አገልግለዋል፡፡ ከወ/ሮ ስንዱ በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሴቶች እስከ 1965 ዓ.ም. ድረስ በተካሄዱት አምስት ምርጫዎች ተፎካክረዋል፡፡ በ1961 ዓ.ም. በተካሄደው አራተኛው የሕዝበ እንደራሴዎች ጠቅላላ ምርጫ ከመላው ኢትዮጵያ ከተመረጡት 250 እንደራሴዎች መካከል አሸናፊ የነበሩት አራት ሴቶች ሲሆኑ፣ ከተወዳደሩት መካከል 24ቱ ሴቶች … [Read more...] about የምርጫና ነጻነት ቁልቁለት
ኢትዮጵያና አሜሪካ
ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ እንደሆነች ጥጋበኛ የአሜሪካ ቅምጥል ሆናለች። የፋርሱ ጉዳይ ከፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ጋር እንደተያያዘው ሁሉ የኢትዮጵያም ጉዳይ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር የተያያዘ ነበር፤ የእውቀት ጥበብ (ቴክኖሎጂ) እያደገ ሲሄድ የቃኘው ጣቢያ ለአሜሪካ አማራጭ የሌለው መሆኑ ቀረ፤ አሜሪካ ኮተቱን ይዞ ወደህንድ ውቅያኖስ ሲሄድ ኢትዮጵያን ችላ ማለት … [Read more...] about ኢትዮጵያና አሜሪካ
“ለመተማመን እንነጋገር”
በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ሜይ 2 ቀን 2015 ዓመተ-ምህረት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በአካሄደ እለት እውቁ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና እውቁ የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት መጽሀፍ ደራሲ አቶ የሱፍ ሃሰን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ስብሰባው በቅርብ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ባሰቃቂ ሁኔታ ለተሰዉት ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፣ የትብብር መድረኩ ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን አሰፋ በመክፈቻ ንግራቸው እዳስረዱት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበትን የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የጎሳና የሃይማኖት ቀውስ፣ እጅ የከፋ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የዜጎችና የሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል። አያይዘውም፣ … [Read more...] about “ለመተማመን እንነጋገር”
በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?
በተለያዩ ሀገሮች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ያለፉባቸውን ጥምዝምዞች፣ የገጠማቸውን ደጋፊና አደናቃፊ ሂደቶች መመርመር ባንድ ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል ታላቅ ጠቀሜታ አለው። በዚህ አንጻር በ2011 የአረብ ስፕሪንግ ካምባገነናዊ ስርአት ወደ ዴሞክርሲ ልትሸጋገር ነው ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመን፣ እነሆ ዛሬ በእርስ በርስ ጦርነት ተናውጣ እንኳንስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ልትሸጋገር ከራሷም አልፋ አካባቢውን ለማመስ የቻለ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ መመርመር ለሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ትግልም ሆነ ባካባቢው መረጋጋት ላይ ሊኖረው ለሚችለው እንደምታ ታላቅ ትምህርት ይሰጣል። በዚህ አኳያ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የየመንን ተመክሮ በመመርመር ለኢትዮጵያ ሁኔታ የሚኖረውን ትምህርት አመለክታለሁ። በርግጥ ይህ ጽሁፍ ሰፊ የሆነውን የሁለቱን ሀገሮች ውስብስብ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ … [Read more...] about በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?










