• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ለመተማመን እንነጋገር”

May 14, 2015 11:27 pm by Editor Leave a Comment

በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ሜይ 2 ቀን 2015 ዓመተ-ምህረት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በአካሄደ እለት እውቁ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና እውቁ የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት መጽሀፍ ደራሲ አቶ የሱፍ ሃሰን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ስብሰባው በቅርብ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ባሰቃቂ ሁኔታ ለተሰዉት ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፣ የትብብር መድረኩ ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን አሰፋ በመክፈቻ ንግራቸው እዳስረዱት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበትን የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የጎሳና የሃይማኖት ቀውስ፣ እጅ የከፋ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የዜጎችና የሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል። አያይዘውም፣ የዜጎች ሰብዓዊም ሆነ ብሄራዊ መብት ያላግባብ እየተጣሰ በመሆኑ፣ ዜጎች በሀገራቸውም ውስጥ ሆነ በተሰደዱባቸው ሀገራት ለስቃይ፣ ለመከራ እንግልትና ብሎም ሞት እየተዳረጉ ነው ብለዋል። መንግስት ሀዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ በወጡት ዜጎች ላይ በማናለብኝ የወሰደው የሃይል germany3እርምጃ ድርጅታቸው በጥብቅ የሚያወግዘው መሆኑን የገለጹት አቶ ጌታሁን፣ ህዝባችን አንድ ቢሆንም ድርጅቶች በሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ባንድ ተማክረው ካልሰሩ ለውጥ ማስመዝገብ አንደማይቻል አስገንዝበዋል። በማያያዝም ይህንን ህልውናችንና ብሄራዊ ማንነታችንም የሚፈታተን ችግር ለማስቆምና ዘለቄታ መፍትሄ ለማበጀት ድርጅቶችም ሆኑ ህዝቡ ልዩነትን አጥቦ በጋራ በአንድነትንና በመቻቻል በመስራት ኢትዮጵያን ማዳን ተገቢ አእንደሆነ ጠቁመው፣ በጀርመን የኢትዮጵውያን የትብብር መድረክ መቋቋም አስፈላጊነትም ይህንኑ ሀገራዊ ተልእኮ ለመወጣት ነው ያሉት ሰብሳቢው፣ የጋራ መድረኩና ዓላማና ተግባር አስርድተዋል። በማያያዝ እንደገለጹት፦ ይህንን አስከፊ ሁኔታ ለመቋቋም እኛ በጀርመን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም ከሚገኙ ከሌሎች አቻ ወገኖቻችን ጋር በመሆን፣ ለሀገራችን የሚበጅ ዘለቂታ ያለው መፍትሄ ለማፈላለግና ጸረ-ወያኔ ትግሉን ለማገዝ የተቋቋመ፣ የፖለቲካ፣ የሲቭክ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ሀገር ወዳድ ግለሰቦችን ያቀፈ የሲቪክ እንቅስቃሴ እንደ መሆኑ መጠን፣ ማንኛውም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚል ዜጋ ሁሉ ብሄራዊና ሀገራዊ (ኢትዮጵያ ነክ) በሆኑ አጀንዳዎች ዙሪያ ከጋራ መድረኩ ጋር አብሮ እንዲሠራ ለተሰብሳቢው ህዝብና ባካባቢው ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች፣ የሓይማኖት ተቋማትና ሀገር ወዳድ ግለሰቦች ጥሪ አስተላልፈዋል።

የዕለቱ የክብር እንዳ አቶ የሱፍ ያሲንም በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ቀደምትነት እንዳላቸውና በኢትዮጵያዊነት ጥላ ማእቀፍ ስር ለዥም ዘመናት በሉዓላዊነት ስለመኖራቸው፣ እንዲሁም፣ ስለ ምሥራቅ አፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ ህብረተሰብ ታሪካዊ የዘር አመሠራረት፣ ስለ ኢትዮጵያ ቀደምትነትነትና yusufማንነት ለዘመናት ወደኋላ ተጉዘው ታሪክ እየጠቀሱ በሰፊው ካስረዱ በሁዋላ፣ በዛሬይቱ የኢትዮጵያ፣ የጎሳ ፖለቲካና ማህበረ-ሰባዊ ችግሮች ላይ በዝርዝር ተችተዋል። ጉዳዩን ሲያብራሩ እንዳሉት፣ የወያኔ መንግስት ከሚከተለው የተሳሳተ የፊዴራል አወቃቀርና አስተዳደር አንጻር ያሉትና ሊከሰቱ ይችላሉ ያሏቸውን ስጋቶችና ማህበረ-ሰባዊ ቀውሶች በመጠቆም፣ “ሳንጣላ ተራርቀን፣ ሳንቀራረብ ተራርቀን እንድንኖር እየተደረግን ነው” በማለት ለጉባኤው አስረድተዋል። በማያያዝም፣ ልዩነቶቻችን ለጥንካሬያችን መሠረት ናቸው ያሉት አቶ የሱፍ ያሲን፣ ድክመቱን የሚያሻሽል ክፍተትን መሙላት ይችላል፡፡ በሰለጠነ መንገድና በነፃነት መወያየት ለሃገራችን የሚበጅ መፍትሄ ለማግኘት ዓይነተኛ መንገድ ነው ብለዋል።

አቶ የሱፍ ያሲን አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት የሚለውን ፍኖት በተመለከተ ሲያስረዱ፣ በማንነት ላይ ከመራኮት ይልቅ አሰባሳቢ አንድነት ላይ ትኩረት በመስጠት መወያየትና ለዚህም እውን መሆን አበክሮ መሠራት እንዳለበት አስገንዝበው፣ በየስብሰባውና ውይይት መድረኩ ያለውን አወዛጋቢነት በተመለከተ፣ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረዳ ዘንድ ሀሳባቸውን “አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት” በሚል መድብል ማቅረባቸውን አስረዱ። አስቀድሞ ተስማምቶ እኛ እንዲህ እንሁን ብሎ ወስኖ የተመሠረተ ሃገር የለም፣ ነገር ግን እንዲህ መሆን አለበት ብሎ መወያይት ይቻላላል ብለዋል። “ማንነት መለያ ነው” ፣ የሚሉት አቶ የሱፍ፣ የሰው ልጆች ተሰባስበው በየ’ሚኖሩበት አካባቢያቸው ባሻቸው ፊና ተደራጅተው እራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደራቸው በየትኛውም ሃገር ያለና የተለመደ ተግባር ነው፣ ካሉ በሁዋላ፣ ነገር ግን ችግሮች በመሃከላቸው ሲከሰቱ በውይይት እርምትና ማሻሻያ እየተደረገበት ዘለቄታ ያለው መፍታት ማበጀት እንደሚቻል የጀርመንን ተመክሮ በማንሳት አስረድተዋል። “የፌደራል አወቃቀር ለኢትዮጵያ አስፈላጊ ነው” የሚሉት አቶ ያሲን፣ የብዙሃን ይሁንታ የታከለበት ሲሆን ብቻ ነው የብርሃን አቅጣጫ የሚኖረው ብለዋል። በማያያዝም፣ ችግሩ በየአካባቢው እራስ በራስ ማስተዳደር መቻሉ ሳይሆን፣ አብሬ መኖር አልፈልግም የሚልgermany4 አካል ሲመጣ ነው ብለዋል። በማያያዝም ለእንዲህ አይነቱ ጥያቄ አግባብ ያለው ምላሽ በወቅቱ ሳይሰጥ ሲቀር፣ የሁዋላ የሁዋላ ችግሩ የከፋ ሊሆን ይችላ በማለት በሀገር ውስጥ ቀደም ብለው የተከሰቱትን በሰሜን- ኦሞ የቀጫ ብሄረሰብ ከጋሞ ለመነጠል ያደረገውን፣ ከከጉራጌ ዞን የስልጤ ብሄረሰብ የወሰደውን እርምጃ እንደማሳያ በማንሳት አንስተዋል። በመጨረሻም ከቤቱ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች አግባብ ያለው መልስ የሰጡ ሲሆን ፣ ችግሩን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት ይላ ተብሎ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ፦ የተሠሩ ግድፈቶችን ማስተካከል፣ ስልጣን እንድ ቦታ ላይ እንዳይከማች ማድረግና ሁሉም እራሱን በራሱ በእኩልነትና በነፃነት እንዲያስተዳድር መፍቀድ፣ ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት ማየት፣ መሰባሰባችን በዜግነት ላይ እንጅ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በዘር መሆን እንደሌለበት፣ ነባርና በአባቶች የተገነባው የጋራ አሰባሳቢ “ኢትዮጵያዊነት” ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ በዚሁ የማንነት ጥላ ስር ተሰባስበን ለሀገራችን የሚበጀውን ለመምከርና ለመስራት ስንችል ብቻ ነው ችግሮቻችን ተጋፍጠን ዘላቂ መፍትሄ ልናበጅለት የምንችለው። ያለውንና የነበረውን ስናከብርና ስንቀበል ወደፊት መራመድ እንችላለን በማለት አስገንዝበዋል።

ከአቶ ያሲን የሱፍ በመቀጠል ሰፊ ንግግር ያደረጉት፣ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ(አኢጋን) ጅርጅት መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ፣ በንግግራቸው መግቢያ እንደገለጹት ይኸ መንግስት ከወደቀ ሀገር ውስጥ ገብቼ የምሠራው ሥራ አለኝ እሱም ጎንደር ሄጄ የአማርኛ መምህር መሆን ነው፣ በማለት ቋንቋ መግባቢያችን እንጅ የዘር መለያችን ሊሆን እንደማይገባ በቀልድ መልክ ያስገነዘቡት አቶ ኦባንግ፣ ንግግራቸውን በመቀጠል፣ በደቡብ አፍሪካ የመጨረሻው የሞት ሞት የሞቱት የእኛ ልጆች ናቸው ብለዋል። በመቀጠልም፣ ከዚህ የበለጠ ብሄራዊ ውርደት የለም። በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቁሮችን ጨምሮ ዓለም ፊቷን ያዞረችበት ወቅት ነው ብለዋል። በተጨባጭ በሊቢያ የተከሰተውን የዜጎች አረመኒያዊ ጭፍጨፋ ባስረጅነት አንስተው፣ የዓለም መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ገዳዮቹ እራሳቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን በይፋ እየገለጹ የኢትያጵያ መንግስት ገና እናጣራለን ማለቱ ዜጎቻችን በሀገራቸው እንኳ ምን ያህል ክብራቸው እየተደፈረ፣ ስብዕናቸው እየተጣሰ መሆኑን ያሳያል በማለት የመረረ ሀዘናቸውን germany oየሲቃ እንባ እየተናነቃቸው ለተሰበሰበው ጉባኤ ልብ በሚነካ አገላለጽ አስረድተዋል። ተሰብሳቢዎችም በበኩላቸው በንግግራቸው እጅግ ከመመሰጣቸውም በላይ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂና እልቂትና በደረሰብን ብሔራዊ ውርደት ሳቢያ በእንባ ሲራጩ ውለዋል።

በንጉሱ ዘመን ለትምህርት ወደ አውሮፓ ተልኮ በታሪክ አንድም የቀረ ሰው አልነበረም ዛሬ ግን ይኸ ሁሉ ስደት ለምን…? የሚሉት አቶ ኦባንግ፣ ላስረጅነት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ከ200.000 በላይ ስደተኞች ከየመን መመለሳቸውን ይጠቁማሉ። በማስከተልም፣ በሜዲትራንያን ባሀር ከተጣሉት መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል፣ በየመን የወገን አስከሬን በጎዳና ላይ ወድቆ ለ6 ቀናት ያህል አልተነሳም እበሰበሰ ይገኛል። ወገኖቻችን በገዛ ሀገራቸው ሀዘናቸውን እንኳ ለመግለጽ ሰልፍ ተከልክለዋል ካሉ በሁዋላ፣ እኛ ዛሬ የምናለቅሰው ወገኖቻችንን ስለምንወድ ነው፣ ከሞቱት መካከል ክርስቲያን አለበት፣ እስላም አለበት፣ ኦሮሞ አለበት፣ አማራ አለበት፣ ትግሬ አለበት። አንተም አንችም የህን ጊዜ እዛ ኖራችሁ ቢሆን ኖሮ፣ የናንተ እጣ ሊሆን ይችል ነበር በማለት በምሬት የተናገሩት አቶ ኦባንግ፣ ተበታትነን በየቦታው ከምናልቅ አሁን በቁም ኑ’ እንዋደድ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደጋገፍ፣ የጋራ ችግራችንን በጋራ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ተሰባስበን እንፍታ በማለት፣ ልብ በሚመስጥ አገላለፅ ለሁሉም ዜጎችና ድርጅቶች በአንድነት ሆነን በጋራ ሀገርን ከጥፋት የመታደግ ሥራ ለመሥራት ተባብረን እንቁም የሚል ጥሪ አስተላልፋዋል።

አቶ ኦባንግ ንግግራቸውን በማስረዘም፣ ስለችግሮቹ መፍትሄ ሲያስረዱ እንደገለጹት፦ ለሀገራችን ችግር መንስኤው እኛው ነን። ችግራችን በእኛው ተፈጠሮ እኛኑ ሰለባ አድርጎናል ብለዋል። እናም እራሳችንን ካላስከብርን ሌላ ማንም ሊያስከብርልንም ሆነ ሊያከብርልን አይችልም ካሉ በሁዋላ፣ ያለፈውን መለወጥ አንችልም ነገር ግን የመወደፊቱን መለወጥ መቻል አለብን በማለት ለውጥ ከእኛው ከራሳችም መጀመር እንዳለበትና ይኸውም ቀዳሚ እርምጃ ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት በመስተት አስገንዝበዋል። “እኛ ስንወለድ ጉሳ ወይም ሃይማኖት አልነበረንም” የሚሉት አቶ ኦባንግ፣ ዛሬ በጎሳና ሓይማኖት ሰበብ መለያየታችን ለምን ..? ሲሉም ይጠይቃሉ። በማስከተልም፣ የእኛ መለያየት ለወያኔ መንግስት መንሰራፋት ትልቅ እድል ሰጥቶታል። በዚህም ሳቢያ ነው ለዜጎች መብትና ክብር ግድ የሌለው በማለት ከገለጹ በሁዋላ፣ መንግስት የሌለው እኛ ሃገር ብቻ ነው፣ እኛ የምንጠይቀው ስልጣን ሳይሆንgermany6 የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል። ለዚህም ማሳያ በቅርቡ በፈረንሳይ ሀገር 11 የፈረንሳይ ዜጎች በተገደሉበት ወቅት መላው የአውሮፓ መንግስታት መሪዎች በስፍራው ተገኝተው ሃዘናቸውን ገልፀው እንደነበር አስታውሰው፣ ዛሬ በዓለም ላይ የሚታየው የሰው ልጅ እኩልነት አንፃራዊና ከወረቀት ያላለፈ እንዳልሆነ በማሳያነት ተጠቅመዋል። በማያያዝም ለራሳችን ነፃነት፣ መብትና ክብር እኛው እራሳችን ኢትዮጵያውያን ቆርጠን ካልተነሳንና ካልታገልን ከማንም እጅ፣ (የአውሮፓውያን መንግስታትንም ጨምሮ) መብት በነፃ እንደማይታደለን ልናውቅ ይገባል በማለት ካስረዱ በሁዋላ፣ ምንም እንኳ በርካታ ድርጅቶች ቢኖሩም ተገቢውን ሥራ ግን መሥራት አልቻሉም ብለዋል። ሆኖም ግን ያጣነው የፖለቲካ መሪ ሳይሆን የፍቅር መሪ፣ የጥበብ መሪ ነው። ስለሆነም አንድነትና ጠንካራ ተቋም (ድርጅት) ሊኖረን ይገባል፣ እንዲኖርም ድርጅቶችንና ተቋማትን በውል መርዳት ያስፈልጋል ካሉ በሁዋላ፣ ከቤቱ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች በሰፋት በማብራራት ተገቢ መልስ ስጥተዋል።

በመጨረሻም ተሰብሳቢዎቹ፣ የዜግነት መብትን ለማስከበርና የችግሩ ምንጭ የሆነውን አስከፊ የወያኔ ስርዓት ለመለወጥ በሚደረገው ትግል በጋራ አብሮ ለመቆምና ለመስራት ያሰችላሉ ያሏቸውን ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ ተነቦ የእለቱ ስብሰባ በምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule