እንደብዙዎቹ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ዩኒቨርሲቲው በየጊዜው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር እንዲከፍቱ ለመረጣቸው ታላላቅ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡ እ.ኤ.አ. 2009 ላይ ግን የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር ለከፈቱት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የክብር ዶክትሬት ላለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ልምድና የሥራ ውጤት ለክብር ዶክትሬት ጣሪያ አልደረሰም የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ጉዳዩ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የመክፈቻ ንግግር አድራጊዎችንና የክብር ዶክትሬት የሚሰጣቸውን ግለሰቦች የሚመርጥበት የራሱ ነፃ የሆነ ሒደት እንዳለው፤ የክብር ዶክትሬቱ የሚሰጠውም ለትልቅ ስኬት መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ በወቅቱ ዲግሪው የክብር ከመሆኑ አንፃር ዩኒቨርሲቲው አሠራሩን መሠረት በማድረግ በውሳኔው … [Read more...] about ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት
Right Column - Primary Sidebar
ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንደሌሎች "እኔ ምን አገባኝ? አርፌ ልቀመጥ" ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና፣ በዘረኝንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። የወያኔ ቡችላው ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አልተንቦቀቦቀችም። እንደ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሕሊናዋን አልሸጠችም። የወላይታ ጀግና የሆነውን የንጉስ ጦናን ወኔ ተላብሳ፣ ለእዉነት፣ ለፍትህ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመች። የወላይታ ሕዝብ በባህሉ፣ በቋንቋም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ፣ መብቱ ሲደፈር የማይወድ፣ ታታሪ ሕዝብ ነው። ይች ሴት … [Read more...] about ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና
“የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”
ስለ ሳሙኤል ግድያ ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ብዙዎች ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለእኔ ከሳሙኤል አወቀ ግድያ ምን እንማራለን? የሚለው ነው ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ንግግር ተናግረው የተገደሉ ሰዎች ጋር የሚመደብ ሰው ነው፡፡ የሳሙኤል ትውልድ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ እንደገሚገሉት እያወቀ፣ ነገር ግን ያ ሞቱ ከንቱ እንዳይሆን አስፈላጊውን መረጃ አስቀምጦልናል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስተምረው ህዝቡ ለጣሊያን እንዳይገዛ ሰብከው ተገድለዋል፡፡ ለዚህም ሀውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ይህ መታሰቢያ ለኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ልዕልና እና የአልበገሬነት ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡ የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ተማሪዎችም ይማሩበታል፡፡ የሳሙኤልን ንግግርም ወደፊት እድሜ ከሰጠን እኛ እናየዋለን፡፡ እኛ ባንደርስበት እንኳ መጪው ትውልድ … [Read more...] about “የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”
“የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
ሰሞኑን ኦባማ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው በሚል፤ ከባህር ማዶ ጫጫታ፤ ከወደ አገር ቤት ደግሞ የጆሮ ብራና የሚጠልዝ ከበሮ ድለቃው ተጧጡፏል:: ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !
አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ
"የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል" አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡ በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ … [Read more...] about አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ
“የአማራ ክልል ዳኞች አቤቱታ”
ከአዘጋጆቹ፡- ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፌስቡክ ወዳጃችን “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን” በማለት በውስጥ መስመራችን የላኩልንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ ጋዜጠኝነት “ወንጀል” በሆነባት ኢህአዴግ በሚገዛት አገራችን በስም የተጠቀሱትን ሹመኛ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ ሆኖም ግን መረጃው ስህተት ነው የሚል የኢህአዴግ አካል ምላሽ ከሰጠን ለሕዝብ እናቀርባለን፡፡ “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን”!!!!! ደመወዝና ጥቅማጥቅም ስላነሰን ከእነ ልጆቻችን ተራብን፣ ተጠማን፣ ብለን ሀሳብ እንዳንሰጥ “ችግር አለባቸው” እየተባልን ከነአካቴው ከስራ ልንወገድ ሆነ፡፡ ጎን ለጎን ሌላ ስራ ፈጥረን እንዳንሰራ ዳኛ በንግድ ስራ መሰማራት አይችልም ተባልን፡፡ ኧረ የት እንድረስ!!! ደመወዝና ጥቅማጥቅም ይስተካከልላቸው ተብሎ ከክልሉ ዳኞች አስተዳደር … [Read more...] about “የአማራ ክልል ዳኞች አቤቱታ”
“ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው የምትሄዱት” ፖሊስ
• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አወቀ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ከሳሙኤል አወቀ ጋር የነበራቸውን … [Read more...] about “ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው የምትሄዱት” ፖሊስ
በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ
አቶ ፈቃደ ሸዋቀና የስደትን ነገር መነሻ አድርገው ስለ ብሔራዊ እርቅ የሰነዘሩት ሀሳብ ካለፈው የባሰ ጨለማ የሆነው የሀገራችን መጻኢ እድል አሳስቦ አስጨንቆአቸው ያቀረቡት በጎ ሀሳብ እንደመሆኑ አንብበን የምንተወው ወይንም ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ብለን ልናናንቀው የሚገባ አይደለም፡፡ ርሳቸውም አንዳሉት ሁሉም የየበኩሉን ይበጃል የሚለውን ሀሳብ በመሰንዘር በመተላለቅ ሳይሆን በመታረቅ የምናተርፈበትንና ሀገራችንንም አድነን ለመጪው ትውልድ ልጆቿ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማቆየት ወደሚያስችለን እቅጣጫ ብናመራ ነው የሚበጀው፡፡ በዚህ መንፈስ እኔም እንዲህ ቢሆን እላለሁ፡፡ ወያኔ ስልጣኑን ለብቻው ካደረገ ግዜ ጀምሮ በተለያየ መንገድ የብሔራዊ እርቅ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የሀሳቡ አቀንቃኞች በሁለት ወገን መወገዛቸውን እናስታወሳለን፡፡ ወያኔ የደርግ ሥርዓት ወንጀለኞችን … [Read more...] about በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
ከአዘጋጆቹ፤ ወዳጃችን ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ ... በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ ቆይተው ባለፈው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት እናንተ አንባቢያን ታሪካቸው መነሳት አለበት የምትሉትን ከፎቶ ጋር እንድታቀርቡ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡ የአገራችን ታሪክ በሚያስደነገጥ ፍጥነት እየወደመ ባለበት በአሁኑ ወቅት በህይወት ያሉትንም ሆነ የሌሉትን አንስተን ማወደስ ተገቢ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ አገራዊ ጥሪ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ትኩረታችን እና ኃይላችንን የሚወስደው ነገር አንድ ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም እየደረሰብን ያለው ጥቃት ከበርካታ አአቅጣጫ ነውና፡፡ ስለዚህ አሁንም ይህንን ዓምድ በከፈትንበት መልኩ ሥራቸውና ታሪካቸው እንዲነሳ የምትፈልጉት ሰው ካለ ፎቶውንና … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፰
ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ
የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን … [Read more...] about ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ










