እኔም እንደ ዜጋ ለአገር ሰላም አለኝ!! ኢትዮጵያ የምትባል አገር የሁላችንም እንጂ የተወሰኑ ግለሰቦች፣ ብሔሮች፣ ጎሳ፣ ዘር፣ …. አይደለችም፡፡ የተወለድኩት በንጉሡ ዘመን ሲሆን፣ ነፍስ ያወኩትና ፊደል የቆጠርኩት በደርግ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ደርግ እጅግ ክፉና ጨካኝ ወታደራዊ መንግሥት እንደ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ብዙዎች ተገድለዋል፤ ተረሽነዋል፡፡ በአንጻሩ አሁን ያለው መንግሥት ከደርግ በምን ይሻልል? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ደርግ በአርሶ አደሩና በከተሜው ሕዝብ ዘንድ አንጻራዊ በሆነ መልኩም ቢሆን ተቀባይነት ነበረው፡፡ በተለይ አገራዊ አጀንዳን በሚመለከት ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን ቆሞአል፡፡ በ1969 ዓ.ም ትዕቢተኛው የሶማሊያ ወራሪ መንግሥት ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ሕዝቡ አዎንታዊ ምላሽ ሰጥቶአል፡፡ ወረራውን ለመቀልበስ የሕዝቡ ድጋፍ ከደርግ … [Read more...] about ለአገር ሰላም መፍትሔው …
Right Column - Primary Sidebar
Anatomy of a failed leadership
The ¼ Prime Minster of Ethiopia was at it again. Abay and Mesfin have been busy warning us of the consequences of getting rid of Woyane. Debretsion is more concerned about the rift in the military while Tigrai warlord Abay Woldu is swearing Wolkait or death. Aba Dula and Kassu were added to give color to discussion not that any body paid attention. It was quarter PM’s turn and he delivered his colorful speech to Woyane 100% Parliament. As usual it was all theatrics and void of any quotable … [Read more...] about Anatomy of a failed leadership
“የኦህዴዱ መሪ” ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ነው፤ ምስጢሩ እነሆ…
ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ገብረኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከገብረ-ኪዳን ወደ ኩምሳ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር። ጉዳዩን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ፋካልቲ ስንማር ሁለታችንንም በአንድ ክፍል አስተምሮናል። የወርቅነህ ትክክለኛ አያት ስም ያለበት ሰነድም በእጁ አለ። ግን ጉዳዩን አላጋለጠውም። ምናልባት የሙያው ስነ-ምግባር ይህንን ለማድረግ አይፈቅድ ይሆናል። ወርቅነህ ገበየሁ ሻሸመኔ ነው ተወልዶ ያደገው። እዚያ መኖሩ ደግሞ ኦሮምኛን አቀላጥፎ እንዲናገር ረድቶታል። ዘር መቁጠር ጸያፍ ቢሆንም ይህ ግን መታወቅ ያለበት ጉዳይ ነውና የወርቅነህ ገበየሁ ወላጆች ኦሮሞዎች አይደሉም። … [Read more...] about “የኦህዴዱ መሪ” ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ነው፤ ምስጢሩ እነሆ…
ካሚል ሸምሱ እውነት ነጻ ያወጣችው ጀግና
እውነትን መናገር ለራስ ነው የሚያምኑበትን ሳይናገሩ ከመኖር ይሰውረን!!! ከአንድ አመት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የማውቀውን ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እስከ ቂሊንጦ በሚል ርእስ አንዲት ጽሁፍ ጀባ ብዬ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እነ ካሚል ሸምሱ ከቂሊንጦ ቃሊቲ ከዛም ወደ ቤተሰብ ተቀላቅለዋል፤ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው፡፡ በርካታ ጓደኞቼን ስለ ካሚል ሳጫውታቸው በቅድሚያ ግራና ቀኛቸውን ይመለታሉ፣ ይቀጥሉና አንገታቸውን እስቲሰበር ድረስ ወደ ኋላቸው ገልመጥ ይላሉ፣ ይቀጥሉና የአግአዚ ስናይፐር እንዳይመታቸው ይመስል ወይንም ነፍሴን አደራ በሰማይ በሚመስል መልኩ ሽቅብ ያንጋጥጣሉ፣ በመጨረሻም ራሴውኑ በጥርጣሬ አይን ይመለከቱና ስለ ካሚል ሸምሱ ያላቸውን አስተያየት በሹክሹክታ ይነግሩኛል፡፡ ብሽቅ ብዬ ትቻቸው ልሄድ ስልም ምክንያታቸውን ይገልጹልኛል፣ ‹ምን ነካህ አብረውን … [Read more...] about ካሚል ሸምሱ እውነት ነጻ ያወጣችው ጀግና
ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
በአገራችን፣ ህወሓት በመጀመሪያ በትግራይ ከ40 አመት በፊት በመላ ኢትዮጵያ ደግሞ በበላይነት በሚቆጣጠረው ኢህአዴግ ከ25 አመት በፊት የጀመረው የግድያና የአፈና ስርዓት አሁንም በመቀጠል ላይ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ተቋማዊ ባደረገው የዘውግ ፖለቲካ ምክንያት ህዝባችን ተከፋፍሎ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ በተወሰኑ ክልሎች እንደ ባዕድ የሚታዩበት ሁኔታ ከተከሰተ ቆይቷል። ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን ፍፁማዊ ለማድረግ ሃይማኖትን በመሳሪያነት ስለሚጠቀም በክርስቲያኖች ውስጥና በሙስሊሞች ውስጥም ወደ ግጭት የሚያመራ ክፍፍል ፈጥሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስርዓቱን ለማቆየት የተገነባው የዘውግና የሃይማኖት ክፍፍል ስርዓቱን ለማስወገድ ወደሚጠቅም መሳሪያነት እየተቀየረ ነው፡፡ በአገራችን ያሉ ዋናዎቹ ችግሮች፡ 1. ህወሓት/ኢህአዴግ ገዳይ፣አፈኝና ከፋፋይ መሆኑና ህዝባችን በህይወት … [Read more...] about ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴ ዘረኛውን ቡድን ወደ ተከላካይነት አውርዶታል!
ትክክለኛ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ግብ መዳረሻው ጽኑ መሠረቱ እንቅስቃሴው ሕዝቡን ማዕከል ማድረጉና ሁሉንም ወገን አሳታፊ መሆኑ ነው። በዚህ ረገድ በመላው የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶች የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቢተኝነት፣የወያኔን የአንድ ለአምስት የስለላ መዋቅር በጣጥሶ፣ ሞትን ፊት ለፊት በማጋፈጥ፣ ገዳዮቹን እየገደለ ለበርካታ ወራት የዘለቀው፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነት፣ የዘረኛውን ቡድንና አጋሮቹን ከአጥቂነት ወደ ተከላካይነት እንዲወርዱ አስገድዷቸዋል። አንድ ገዳይ ቡድን ከአጥቂነት ወደ ተከላካይነት ወረደ ማለት የውስጥ ጥንካሬው መዳከሙን፣ ሚስጢራዊ ሥራው በወንፊት ውኃ መቅዳት መጀመሩን፣ በቡድኑ መካከል አለመግባባት መንገሡን፣ የማስገደጃ ተቋሞቹ ግዳጃቸውን እንደጥንቱ ለመፈጸም ዝግጁና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አመልካች ነው። በዚህ ረገድ የወያኔ የማስገደጃ ተቋሞች እንደጥንቱ የማስገደድ … [Read more...] about የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴ ዘረኛውን ቡድን ወደ ተከላካይነት አውርዶታል!
ግፍና ጎርፍ
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ) ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር … [Read more...] about ግፍና ጎርፍ
ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
የአፍሪካ ነፃነት አብሪ ኮከብና በጀግና ህዝቧ አኩሪ ተጋድሎ ባለክብር የነበረቺው ኢትዮጵያ ዛሬ በከፋ ፈተና ውስጥ ገብታለች። በብርቱ ትግልና ጥንቃቄ መወገድ ያለባቸው ያገርና የህዝብ ደህንነት ስጋቶች ከፊቷ ተጋርጠዋል። የርስ በርስ ጦርነት ስጋት፣ የአስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እጦት፣ የማእከላዊ መንግስት አቅጣጫ ብዥታና የውጭ ጠላት ስጋት፣ ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህንና መሰል ያገርና ህዝብ ደህንነት ስጋቶች ለማስወገድና ጤናማ የፖለቲካ ድባብ ለመፍጠር ባስቸኳይ መንቀሳቀስና ሀገርና ህዝብን ካሳፋሪ ውድቀት ማዳን ያስፈልጋል። በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ ያንዣበቡትን እነዚህን አደጋዎች ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? በእርግጥስ ይቻላል? እነዚህን ያገርና የህዝብ ህልውና ፈተናዎች በማስወገድ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሰላማዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ የሚችለውስ ማነው? የሁሉም ጥያቄዎች መልስ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
የፍቅር ብልሃቱ
ልዩነትን አድንቅ አንድነትን አድምቅ እንቆቅልሽ ፍታ ጥላቻ ይረታ ሁሉም ብሔረሰብ ነውና ቤተሰብ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ተውክ አማራ ምንም እንኳን በአገር መንፈስህ ቢኮራ “እኔ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ተውክ ኦሮሞ ምንም እንኳን ጥሪህ ሁሎ ቢያድር ከርሞ “ኢትዮጵያዊ አማራ” ሆነህ ስትሄድ “ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ” አገኘህ መንገድ የልብ ትርታ ሲወጣ ገሃድ ብለው ሲጠብቁ እሳትና ጭድ ፍቅር ጣልቃ ገብቶ አደረገ ጉድ የፍቅር ብልሃቱ ግርም ማሰኘቱ አንቺዬ ድንቅ አገር ኢትዮጵያ የሚሉሽ ትግሬና ሶማሌ ደቡብን የያዝሽ ጉራጌ ጋምቤላ አፋርን ያቀፍሽ ስንቱን ልጠራ ነው በዙ ልጆችሽ ነግሩ ሲጠራ እንዲሁም ሲጣራ እኩልነት ሰፍኖ ፍቅርም ልቆ ገኖ ኦሮሞ አማራ ማለቱ ይረሳና ኢትዮጵያዊ ነኝም ማለት ይቀርና ከአሁን ማንነትህ አድገህ … [Read more...] about የፍቅር ብልሃቱ
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው
በትያትር ድርሰት ጽሁፎቹ ፤ በትርጉምና የግጥም ስራዎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ነፍሱን ይማርና) በ1987 ዓ.ም እዚህ በስደተኛነት ነዋሪ የሆንኩበት ሆላንድ ሀገር መጥቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጎልን ነበር። እንደሚታወቀው ጋሽ ጸጋዬ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ እንደወጣ የደረሰው ወይም የጻፈው አንድ “ሀሁ ፐፑ” የተሰኘ የትያትር ስራው ለህዝብ እንዳይታይ ታግዶበት ነበር። አዋሳን በመሰሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ተዋንያን መድረክ ላይ ሆነው ትያትሩን ሲተውኑ በወያኔ ወታደሮች በዱላ እየተደበደቡ ተውኔቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ሌላው ቀርቶ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ለታላቁ ጸረ-ፋሽስት፤ የኢትዮጵያ ሰማእትና አርበኛ ለአቡነ ጴጥሮስ ማስታወሻ የደረሰውን “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተባለውን ትያትር ለህዝብ … [Read more...] about ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው










