መረራ ጉዲና ገና ከለጋ ወጣትነት ህይወቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባልተቋረጠ ወኔና ጥራት ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ ዜጋ ነው፡፡ በዚህ ያልተቋረጠ ተጋድሎው በንገሱ ዘመን አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በተማሪው ንቅናቄ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ በደርጉ ዘመን ደግሞ በመኢሶን ታጋይነቱ ለሰባት አመታት በእስር ተንገላቷል፡፡ ለአለፉት 25 አመታት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግን ግፈኛ አገዛዝ በመቃወም በሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት ተሰማርቶ ከነዚህ የጥፋት ሃይሎች አንጻር እነሱ ከፋፍለህ ግዛን ሲያራመዱ የህዝቦች ወንድማማችነትን እየሰበከ፣ እነሱ ለስልጣናቸው ሲሉ በለየለት የአፋኝና የአመጽ ጎዳና ሲሰማሩ ዴሞክራሲን፣ ሰላምንና ህጋዊነትን እያነገበ ሲሞግታቸውና ሲታገላቸው በህዝባችን ፊት ተአማኒነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈ ብርቅየ … [Read more...] about የዶ/ር መረራ መታሰር ሰላማዊው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተደረገ ጥሪ ነው!!!!
Right Column - Primary Sidebar
ተመስገን “ሰባት ስምንት ፖሊሶች” ከብበውት ወንድሙ አየው
ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ፡፡ ቤተሰቦቹ “ተመስገን ዝዋይ የለንም ተብለናል” ሲሉ አቤቱቻቸውን ለተለያዩ አካላት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬ ለጥቂት ደቂቃዎች ተመስገንን መመልከት እንደቻሉና ጤንነቱ መቃወሱን ተናግረዋል፡፡ በጻፋቸው እና ባሳተማቸው ጽሁፎች ክስ ቀርቦበት እና ተፈርዶበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት እስሩን እየገፋ ይገኝ የነበረው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደብዛ መጥፋት የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ፡፡ ከሰብዓዊ መብት ተቋማት እስከ ጋዜጠኛ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ለጉዳዩ አጽንኦት ሰጥተው መግለጫ እስከ ማውጣት እና በማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ እስከመክፈት ደርሰዋል፡ የተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች በዝዋይ ማረሚያ ቤት “ተመስገን እዚህ የለም” ተብለናል … [Read more...] about ተመስገን “ሰባት ስምንት ፖሊሶች” ከብበውት ወንድሙ አየው
ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ሄኖክ የሺጥላ እና ሌሎች የፌስቡክ ታጋዮች!
አንዷ ያገሬ ሴት ደጋግማ ስታወራኝ ነው አንዱን የፌስ ቡክ ዝነኛ ታጋይ ያወቅሁት። እንዴት እስካሁን እንዳላየሁት ገርሞኝ በስሙ ፈልጌ ገባሁ። ጊዜየን አላጠፋሁም። ዘጋሁት። ካሁን ቀደም እንዴት የፌስ ቡክ ገጼ ላይ እንደመጣ ሳላውቀው ገጭ ብሎ ባገኘው ከፍቼ አይቸው፣ ሰምቼው... ወዲያው ነበር የዘጋሁት። ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳየው፣ ነብያችን ድንገት ተከስተውለት ኖሮ፣ አዲስ ሙስሊም (convert) ሆኖ ነው መሰለኝ፣ ጥቂት የማውቃቸው ሙስሊም የፌስ ቡክ ወዳጆቼ፣ ላይክ አድርገው “ኢንሻላህ! ሱብሃናሁ ወተዓላ...”፣ “... እንኳን ወደ እውነተኛው እምነት መጣህ ወንድማችን...” ... ወዘተ የሚሉ ጽሁፎች ገጹ ስር ተኮልኩለው አይቼ ሳምንት ሳይሞላኝ ነው ያቺው ያገሬ ሴት ስትነግረኝ እንደገና ፈልጌ የገባሁት። ላካንስ ሰውየው (ካሁን በኋላ “ሰውየው” ስል ይኸኑ ሰውየ ነው) ባንድ ሳምንት … [Read more...] about ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ሄኖክ የሺጥላ እና ሌሎች የፌስቡክ ታጋዮች!
“እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም”
ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ከተመሰረተች 9 ዓመት ሆኗታል:: ባለፉት 9 ዓመታት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መረጃ ከሚያቀብሉ የመረጃ መረቦች መካከል አንዷ በመሆን በአማራጭነት ሚድያነት አገልግላለች:: በየዕለቱ ድክመቶቻችን በማረም ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ አሁንም ተመራጭና ተአማኒ ሚዲያ ለመሆን ተግተን እየሰራን ነው:: እንደሚታወቀው የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች የሚዲያን ሥራ የጀመሩት እዚህ ስደት ላይ ከወጡ በኋላ አይደለም:: በሃገር ቤት በኢትዮጵያ ነጻው ፕሬስ ውስጥ መስዋዕትነት የከፈሉ፣ የታሰሩ፣ የተገረፉና ብዙ መስዋዕትነት በከፈሉ ጋዜጠኞች የምትዘጋጅ ድረገጽ ናት:: ዘ-ሐበሻ ድረገጽ በተለይ ዕድሜያቸው ከ18 – 45 ዓመት ክልል ውስጥ በብዛት የምትጎበኝ፣ ወቅታዊ መረጃዎችንም በፍጥነት የምታደርስ መሆኗ የሕወሓትን መንግስት ሁሌም እንዳስደነገጠች ነው:: ባለፉት 9 ዓመታት በተለይ … [Read more...] about “እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም”
ህወሃት “ተቃዋሚዎችን” በዓመት ሦስቴ ደጄን ከረገጣችሁ ይበቃችኋል አላቸው
በጥልቅ እየታደስኩ ነው የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በየቀኑ በጥልቅ መበስበሱን እና ለመታደስ ፈጽሞ የማይችል መሆኑን የሚመለክቱ ተግባራትን ሲፈጽም እየታየ ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆችን ወደኋላ በማድረግ ከመድረኩ በማውጣት የፊት ገጾች እንዲሆኑ ከትግራ ውጭ ያሉ ግለሰቦችን በማስቀመጥ ሥራውን በምክትሎቻቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲሠራ እደረገ ነው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ፣ አሳታፊ እሆናለሁ፣ … እያለ የፖለቲካ አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ኃይላትን ያስራል፤ ሕዝቡን ያሰቃያል፣ ይገድላል፡፡ አዲስ አድማስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው በውይይት እንዲሳተፉ ለማድረግ ማኑዋል እየተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ “ተቃዋሚዎች፤ ሳንመረጥ ፓርላማ አንገባም አሉ” በሚል ርዕስ የዘገበው እንዲህ ይነበባል፤ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው … [Read more...] about ህወሃት “ተቃዋሚዎችን” በዓመት ሦስቴ ደጄን ከረገጣችሁ ይበቃችኋል አላቸው
ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
አምልኮተ መለስ የተጠናወተውና የህወሃት አባል የሆነው ዛዲግ አብርሃ "የጥልቅ ተሃድሶ" ውጤት ተብሎ የተመደበው የነገሪ ሌንጮ ምክትል ሆኖ በሃይለማርያም ደሳለኝ መሾሙን Ethiopia Observer ዘግቦታል። ኦሮሞው ሌንጮ በአፈቀላጤነት በየሚዲያው ፊቱን ሲያስመታ የድርጅት ሥራውን የሚያከናውነው መለስን ማንነቴ ነው መንፈሴን ይቀሰቅሰዋል የሚለው ህወሃቱ ዛዲግ ይሆናል። ከዚህ በፊት ስለ መለስ የተናገረውን እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል። "ጥልቅ ተሃድሶ" በጥልቅ መበስበስ ይቀጥላል! ጎልጉል … [Read more...] about ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
አቻምየለህ ታምሩ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ አዳነች ፍሰሃዬ ወልቃይትን አስመልክቶ ላነሳችው አመክንዮዎች የሰጠው ምላሽ:- ይድረስ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ አዳነች ፍስሀዬ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ ካለሽበት ቦታ ይድረስሽ። በዛሬው እለት (ህዳር 28, 2016) «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት» በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ዶክተር ብርሀኑ መንግስቱን፣ ፕሮፌሰር አለማንተ ገብረሥላሴና ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያን ጋብዘሽ ስለወልቃይት ያቀረብሽውን ዝግጅት በጥሞና ተከታትየዋለሁ። ይህንን ግልጽ አስተያየት እንድጽፍልሽ የገፋፋኝ ምክንያት አንቺ አዘጋጅና አቅራቢ ሆነሽ ባሰናዳሽው በዚህ «የምሁራኖች» የውይይት መድረክ ላይ ይዘሽ የቀረብሽው የግል አቋምና የተሳሳተ ግንዛቤ አመክንዮ የሌለው መሆኑን በመታዘቤ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዳደረገ ሰው ምናልባት … [Read more...] about በወልቃይት ጉዳይ የተሰጥ ምላሽ
የመረራ ምክር ለበረከትና ኢህአዴግ
Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
The Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is deeply concerned with the wide-ranging restrictions the state of emergency decree has enabled, which severely affect freedom of expression, freedom of assembly, association and peaceful protest in Ethiopia. Ethiopia’s close allies and partners in the international community unequivocally condemn the grave violations of human rights in Ethiopia and the misuse of the directive to silence political dissents, to threaten and systematically … [Read more...] about Ethiopia: End State of Emergency restrictions on political dissent and targeting of human rights defenders
ዲያስጶራዎቻችን
ዲያስፖራ (ዲያስጶራ) የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ብትን /የተበተነ›› ወይም በአጪር አነጋገር ከትውልድ አገሩ ውጭ ተበታትኖ ያለ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ ከኢትዮጵያ መቶ ሜትርም ይሁን አንድ ሺሕ ማይል ይራቅ ከድንበር ማዶ ያለ ሁሉ ዲያስፖራ ነው፡፡ የምንገኝበት አገር፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የወጣንበት መንገድ፣ ሃይማኖታችን ወይም ብሔራችን ዲያስፖራ ከመሆን (ከመበትን) አያድነንም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በአውሮፕላንም ይሁን በመርከብ፣ ጥገኝነት ጠይቆም ይሁን አግብቶ፣ ፊደል የቆጠረም ይሁን ፕሮፌሰር የሆነ፣ እስላምም ይሁን ክርስቲያን፣ ዐማራም ይሁን ኦሮሞ ወይም ጉራጌ ወይም ሌላ ከድንበር ወጥተን ወደ ሌላ ሉዓላዊ አገር ከገባን ተበትነናል ማለት ነው፡፡ የምንገኝበት አገርም መመዘኛ አይደለም፡፡ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤዥያ ወይም ኦሽኒያ መሆናችን ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ … [Read more...] about ዲያስጶራዎቻችን









