በቅርቡ ፋና ብሮድካስት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ “ኢሕአዴግን” የወከሉት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ጥቂት ለመወያየት ነው የዛሬው አሳቤ። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እኚህ ሰው የተናገሩት ብዙው ነገር ከተለመደው የተለየ ባይሆንም በተለይ የኢትዮጵያን ፍላጎት በተመለከተ የፓርቲያቸው አመለካከትና ጥናትና ምርምር ምን መሰረታዊ ችግር እንዳለበት መመርመር የዚህን መንግስት መሰረታዊ ችግሮች እንደገና ለማሳየት ይጠቅማል። በመጀመሪያ ይህ ውይይት ለምን ተዘጋጀ? ካልን ምን አልባትም በሃገሪቱ የተነሳውን ግዙፍ ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የተለያዩ ሃይሎች መንግስት ዲያሎግ እንዲያደርግ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ የተዘጋጀ ይመስላል። ታዲያ የግብር ይውጣ ነገር ብቻ መሆኑን የሚያሳየው የህዝብ ልብ ያረፈባቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች … [Read more...] about የኢትዮጵያን ፍላጎት ያልተረዳ መንግስት ኢትዮጵያን ሊመራ አይችልም
Right Column - Primary Sidebar
የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር
መግቢያ ያለፉትን 40 ዓመታት ፖለቲካችንን ለመረመረ አገርን በሚመለከት የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ወይም የሚሰጡት ትንተናዎች ሁሉ ሳንይሳዊ ይዘት ይኑራቸው አይኑራቸው የሚጠይቅ የለም። በተለይም ፖለቲካ ፍልስፍናዊ መሰረት ያለው ታላቅ ፅንሰ-ሃሳብ መሆኑ ግንዛቤ በሌለበት አገርና፣ ማንኛውም ህብረተሰብንና የአገርን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የግዴታ ሳይንሳዊ ትንተና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ስሜት ዋናው መመሪያ በሆነበት አገር የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ቁጭ ብሎ በሰከነ መንፈስ ለመመርመር የሚቃጣ ሰው በፍጹም የለም። እንደሚታወቀው በተለይም በአብዮቱ ወቅት ሳይንስና ፍልስፍና መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ ስሜት የፖለቲካውን መድረክ በመያዙ እንደተከታተልነው ለብዙ መቶ ሺህ ህዝብ መሞትና ለአገር ውድመት የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቶ አልፏል። ዛሬ … [Read more...] about የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር
የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ማንነት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በፓልቶክ ክፍል ቀርቦ የኦሮሞ ተወላጅ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነገር። አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ከዚህ ዘር ነኝ የማለት የተጠበቀ ነው። የዘር ቆጠራን ያመጡት ራሳቸው ስልጣን ላይ ያሉት ዘረኞች ናቸው እንጂ እኛ አይደለንም። ዛሬ የራሳቸው ቃል እስረኛ የሆኑ ይመስላል። ጥያቄው ዘሩን በገዛ ፈቃዱ የመቀየር ጉዳይ አይደለም። ተቃውሞው ሹመቱ ላይም አይደለም። በዘር ያመጡት የስልጣን ኮታ ዘሩ ባልሆነ ግለሰብ ሲደለደል - ጉዳዩን ለሚያውቁት ንቀት እና ስድብ ይሆናል። ወርቅነህ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት በሚፈቅደው "ጉዲፈቻ" እና "ሞጋሳ" ባህል መሰረት ወደ ኦሮሞነት ተቀይሮ ከሆነ ግልጽ ይሁን። ካልሆነ ግን የእሱን ማንነት የሚገልጸው ዶክመንት ተመልክቶ ፍርድ መስጠቱ ይበጃል። ለስድስት ዓመታት በድህንነት ሲሰራ በርካታ ንጹሃን … [Read more...] about የወርቅነህ ገበየሁ ወልደኪዳን “ነገዎ” ማንነት
የአሜሪካ ምርጫ:- ዶናልድ ትረምፕ ወይስ ሂለሪ ክሊንተን?
መግቢያ የዛሬ ስምንት ዐመት ባራካ ኦባማ ለፕሬዚደንትነት ምርጫ ለውድድር ሲቀርቡ፣ ከፕሪመሪው ጀምሮ የነበረውን የምርጫው ሂደት እዚህ አውሮፓ ሆነን በየሰዓቱ ሁኔታውን በጥብቅ እንከታተል ነበር። በማያጠራጥር መልኩ የብዝዎቻችን ፍላጎትና አድልዎ ለባራክ ኦባማ ቢሆንም፣ ባራክ ኦባማ ያንን አስቸጋሪ የፕሪመሪ ውድድር አልፈውና ተፎካካሪዎቻቸውን አሸንፈው የዲሞክራቲክ ፓርቲውን በመወከል ለፕሬዚደትነት ምርጫ ይቀርባሉ ብሎ የገመተ አልነበረም። የመጨረሻ መጨረሻ ወይዘሮ ሂለሪ ክሊንተን በአሸናፊነት በመውጣት ፓርቲያቸውን በመወከል የሪፓብሊካን ፓርቲን ከሚወክለው ጋር ለውድድር ይቀርባሉ የሚል ግምት ነበረን። አሁንም ቢሆን የኢንስቲቱሽናል ሬሲዝምነትና አጠቃላይ ሬሲዝምነት በነገሰበት በአሜሪካን ህብረተሰብ ውስጥ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለፕሬዜደንትነት ምርጫ በመወዳደር በአሸናፊነት ይወጣል ብሎ … [Read more...] about የአሜሪካ ምርጫ:- ዶናልድ ትረምፕ ወይስ ሂለሪ ክሊንተን?
The changing face of Ethiopia
The US elections are over and I have not met anyone happy with the outcome. All the dirty linen was washed in public and the winner was the one with the most stain. The opinion polls malfunctioned spectacularly. I followed the election process as told by what is called the ‘liberal’ media. Huffington Post, Slate, The New Yorker among many convinced me it was going to be a ride in the park for Secretary Clinton. HP even gave the Democrats a 91.5% percent of winning the Presidency. In case you … [Read more...] about The changing face of Ethiopia
ይድረስ ለጀዋር መሃመድ
Brotherly advice to Ethiopian Friends በሚል ርእስ በፌስቡክ ገጽህ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞችህ የሰጠህውን ምክር አነበብኩት። ጽሁፍህን ሳነብ የመጀመሪያ ባለመሆኑና በፌስቡክ አስተያየቶችህ ላይ ስለምከታተልህም ሃሳብህን ለመረዳት ብዙም አልቸገረኝም። በተለይ ወጣት ኢትዮጵያውያን ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ አስተሳሰብ መድረክ መምጣት ለሃገራችን የሚኖረውን ዘላቂ ጠቀሜታ የምገነዘብ በመሆኑ ጀዋር የፖለቲካ ተንታኙ ወጣት እየተባለ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ቀርበህ ሃሳብ ስትሰጥ ከአምስትና ስድስት አመት በላይ አውቅሃለሁ። ወጣቱ ጀዋር በዚሁ ከቀጠለ በሃገራችን ኢትዮጵያ ጥሩ ፖለቲከኞችን ልናፈራ እንችላለን የሚል ጽኑ እምነት ነበረኝ። በተለይም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ችግር የሚፈታው በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፍትህ እና እኩልነት የሚያመጣ ስርአት በመገንባት ነው። የኦሮሞም … [Read more...] about ይድረስ ለጀዋር መሃመድ
“ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”
“ወያኔ አንድ ታንክ ከመግዛት፣ በ10 ሚሊዩን ዶላር አንድ ከፋፋይ አክቲቪስት መግዛት ትመርጣለች” መስፍን ፈይሳ ሮቢ ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው በ“አፈርሳታ” ዝግጅቱ ጃዋርን አቅርቦ አነጋግሮት ነበር። ለጃዋር የቀረበለት አንዱ ጥይቄ “. . . የግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ደሞክራሲያዊ ግንባርን ጥምረት እንዴት አየኸው?” የሚል ነበር። ጃዋር “. . . ቅን አመለካከት ነው ያላቸው. . .ጥሩ ሙከራ እያደረጉ ነው. . . ኢንቴንሽናቸው ቅን ነው. . .” ብሎ በተናገረው ውስጥ “. . . በትክክል የተሰራ ግን አይደለም፣ የፖለቲካ ብስለት ያለበት ግን አይደለም” የሚል እና ያልተናገረውንም ነገር (between the lines) ትሰማለህ። ነገሩ “ከኛ ወዲያ ፉጭት አፍ ሟሞጥሞጥ ነው. . .” ወይም “. . . ፖለቲካ ከኔ ወዲያ ላሳር ነው” የሚል ድምጸት አለው። ጃዋር ሌላም ጥይቄ … [Read more...] about “ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”
ለትብብር እንቆቅልሽ መላ
በዚህ ፅሁፍ ስለ አማራጭ ሃይሎች ትብብር አስፈላጊነት የታወቀ ነገር ስለሆነ መናገር አልፈልግም። ማተኮር የምፈልገው እንዴት ትብብሩ እንደሚመጣ መላ ፍለጋ ላይ ነው። ይህም ሲባል ነገሮች ተድበስብሰው አንድ ላይ ተጨፍልቀው ማየት ሳይሆን፥ በየደረጀው ከመነሻው እስከ መድረሻው ጥርት ባለ መልኩ ለማስቀመጥ ነው። ከውጭ ለሚያይ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች ተባብለው በሁለት ትልቅ ጎራ ተከፋፍለው በጥርጣሬ መተያየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ባብዛኛው ግን ልባቸው የሚፈልገው ለሁሉም አንድ ነው። ያም ሆኖ አንዳንድ ተስፋ ሰጭ ፍንጭ ከመታየቱ በቀር በሁለቱ ጎራ ዙሪያ ፈቀቅ ያለ ነገር እየተደረገ አይደለም። ስለዚህ አድበስብሰን ለመግባባት እስካሁን የሞከርነው ጠብ ስላላለ አዲስ መንገድ እንከተል። እስቲ ይህንን መንገድ በሶስት ደረጃ ከፍለን እንየው። 1ኛ/ ቅድመ መግባባት … [Read more...] about ለትብብር እንቆቅልሽ መላ
የዞምቢዎች አገዛዝ ሊታደስ አይችልም!
የወያኔ አገዛዝ የትግራይ ዞምቢዎች ጥርቅም ነው። ዞምቢ ማለት ህሊናው የበሰበሰ፤ስብዕናው የቆሸሽ፤ በአስተሳሰብ የነቀዘ፤ ጭንቅላቱ የተመረዘ፤ አእምሮው የደነዘዘ፤መንፈሱ የታመመ፤ በመከነ ርዕዮተ አለም እውር ድንብሩን የሚጓዝ ነፍስ የሌለው፤ በሞተ ልብ የሚገለጥ የሚንቀሳቀስ አካል ነው። ወያኔ «በጥልት እየታደስሁ ነው» የሚለን በጥልቀት መበስበሱን ሲነግረን ነው። ይህ በጥልቅ የበሰበሰው የትግራይ ሽፍቶች ስብስብ በነቀዘ አስተሳሰብ፣ በተመረዘ ጭንቅላት፣ በደነዘዘ አእምሮ፣ በሙት መንፈስና በመከነ ርዕዮተ አለም እውር ድንብሩን የሚጓዝ የዞምቢዎች አገዛዝ ነው። ወያኔዎች ሰው ለማጥቃት የተደራጁ የትግራይ ዞምቢዎች ናቸው። ዞምቢ አይታደስም። ዞምቢ እንኳን በምድራዊ ኃይልና በሰብዓዊ አስተሳሰብ ሊታደስ የፈጠራቸው እግዚያብሔር ራሱ እነዚህን ሰው ለማጥቃት የሰለጠሱ የትግራይ ዞምቢዎች ሲያይ … [Read more...] about የዞምቢዎች አገዛዝ ሊታደስ አይችልም!
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በሚል ስም የሚጠራ የፖለቲካ ድርጅት ዕሁድ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ በተፈረመ ስምምነት መቋቋሙ ተገለፀ፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲና የሲዳማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሆናቸውን አደራዳሪና አፈራራሚ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት በኢሊኖይ ቺካጎ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡ የንቅናቄው ዓላማ የግዛት አንድነቷ የተጠበቀ፣ ዴሞክራሲያዊ የሕዝብ መብቶች የተከበሩባት፣ የፖለቲካ ሥልጣን ከላይ እስከታች በተዋረድ ያሉትና በምርጫ የሚጨበጥ ሥልጣን የሚኖራትን ፌደላዊት ኢትዮጵያን መመሥረት መሆኑን ዶ/ር ጌታቸው ገልፀዋል፡፡ የትግላቸው ግብ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም፤ አዲስ ሕገመንግሥት እንዲቀረፅና ሁሉም ዜጋ እኩል የሆነባት … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ተመሠረተ










