• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት “ተቃዋሚዎችን” በዓመት ሦስቴ ደጄን ከረገጣችሁ ይበቃችኋል አላቸው

December 12, 2016 06:58 pm by Editor 1 Comment

በጥልቅ እየታደስኩ ነው የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በየቀኑ በጥልቅ መበስበሱን እና ለመታደስ ፈጽሞ የማይችል መሆኑን የሚመለክቱ ተግባራትን ሲፈጽም እየታየ ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆችን ወደኋላ በማድረግ ከመድረኩ በማውጣት የፊት ገጾች እንዲሆኑ ከትግራ ውጭ ያሉ ግለሰቦችን በማስቀመጥ ሥራውን በምክትሎቻቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲሠራ እደረገ ነው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ፣ አሳታፊ እሆናለሁ፣ … እያለ የፖለቲካ አመራሮችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ኃይላትን ያስራል፤ ሕዝቡን ያሰቃያል፣ ይገድላል፡፡

አዲስ አድማስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው በውይይት እንዲሳተፉ ለማድረግ ማኑዋል እየተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ “ተቃዋሚዎች፤ ሳንመረጥ ፓርላማ አንገባም አሉ” በሚል ርዕስ የዘገበው እንዲህ ይነበባል፤

tigistu-so-called-oppositionመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዓመት ሦስት ጊዜ ፓርላማ ገብተው በውይይት እንዲሳተፉ ለማድረግ ማኑዋል እየተዘጋጀ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፣ ሳይወከሉ በፓርላማ ውይይት ህገ መንግስታዊ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

ተቃዋሚዎች ለምን አላማ ከመንግስት ጋር በዚህ መንገድ እንዲወያዩ እንደተፈለገ አይገባንም ያሉት የአረና ም/ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ፤ ውይይቱ በፓርላማ መደረጉ ምናልባት ኢህአዴግ ብቻውን ተቆጣጥሮታል የሚለውን ሃሜት ለማስቀረት ካልሆነ በቀር ሌላ ፋይዳ አይኖረውም ብለዋል። “የተቃዋሚዎች የመወሰን ሚና ጨርሶ በሌለበት ሁኔታ የሚደረጉ ውይይቶች ጥቅማቸው እምብዛም ነው” ይላሉ አቶ ጎይቶም፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው፤ ተቃዋሚዎች የህዝብ ውክልና ሳይኖራቸው በፓርላማ መገኘታቸው በምን አግባብ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ “ፓርላማው ላይ መገኘት የሚቻለው በህዝብ ሲወከሉ ብቻ ነው” ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ተቃዋሚዎች የመወሰን ሚና ሳይኖራቸው የሚያደርጉት ውይይት ምንም ፋይዳ አይኖረውም ብለዋል፡፡

“መንግስት ከተቃዋሚዎች ምክር የሚፈልግ ከሆነ፣ በፓርላማው መሆን የለበትም” ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ሌሎች ልዩ መድረኮች መዘጋጀት አለባቸው ይላሉ፡፡ ተግባራዊ ይደረጋል ብለው እንደማያምኑ የተናገሩት ም/ሊቀመንበሩ፤ ከዚህ በፊት መሰል የውይይት መድረኮች ይዘጋጃሉ ተብሎ መቅረቱን ያስታውሳሉ፡፡ አሁን መንግስት ማድረግ ያለበት ለህዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው ብለዋል – አቶ ሙላቱ፡፡

የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆነው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ በበኩላቸው፤ “መንግስት ከተቃዋሚዎች ጋር ይወያያል የተባለው ከ2002 ምርጫ ማግስት ጀምሮ ነው፤ ሆኖም ተፈፅሞ አያውቅም፤ የአሁኑም የፓርላማው ውይይት የተስፋ ቃል ነው” ይላሉ፡፡

የመንግስትና የተቃዋሚዎች ውይይት እስካሁን ተግባራዊ ሲሆን አለማየታቸውን የገለፁት አቶ ተሻለ፤ “በእውን የሚደረግ ከሆነም፣ “በምን አግባብ ይከናወናል? መቼ ነው የሚጀምረው? እንዴት ነው ተቃዋሚዎች የሚሳተፉት? የሚሉትን ጥያቄዎችን መመለስ አለበት” ብለዋል፡፡ “የውይይት መድረኩ እውን ይሆናል ብለን እንድናምንና ምልክቶች መታየት አለባቸው ብለዋል” – ሲሉ አክለዋል፡፡

“የተቃዋሚዎች በፓርላማ መሳተፍ ምንን መርህ አድርጎ ነው? ህገ መንግስታዊ ነው? በአዋጅ የሚያሳትፍ ነው? የፖሊሲ አቅጣጫ አለው?” ሲሉ የጠየቁት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤ “ተቃዋሚዎች በምን መንገድ፣ የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ወክለው  ነው በፓርላማ ሊሣተፉ የሚችሉት” ብለዋል፡፡

“መንግስት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ለህዝቡ ቀጥተኛ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ላይ ነው” ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ “በአሁኑ ሰዓት ህዝብ ለተቃዋሚዎችም ለመንግስትም ፍላጎት ባላሳየበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች በምን አግባብ ነው ፓርላማ ገብተው ሊነጋገሩ የሚችሉት” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡  ኢዴፓ ተቃዋሚዎችን ፓርላማ አስገብቶ በመወያየት ብቻ ችግሮች ይቀረፋሉ የሚል እምነት እንደሌለው የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ፓርቲያቸው የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲሻሻሉና ህግ ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

አቶ ናሁሠናይ በላይ
አቶ ናሁሠናይ በላይ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና የፌደራሊዝም መምህር አቶ ናሁሠናይ በላይ የፓርላማውን ውይይት በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ በፓርላማው ለየት ያለ ሃሳብ እንዲንፀባረቅ መፈለጉ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው፤ የተቃዋሚዎች ሚና የሚለካው ከገዥው ፓርቲ ጋር በመገናኘታቸው ብቻ አይደለም፤ ገዥው ፓርቲ በተቃዋሚዎች ሚና የሚያምን ከሆነ፣ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ የሚንቀሣቀሱበትን የመጫወቻ ሜዳ ምቹ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

“ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገንቢ ሚና አላቸው ብሎ ማመን መጀመሩን ለማሳየት ከፈለገ፣ በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ላይ እንቅፋት ከመሆን መቆጠብ ይኖርበታል፤ በአመት ሶስት ጊዜ ተቃዋሚዎችን በፓርላማ አሳትፋለሁ ማለት ብቻውን በቂ አይደለም፤ የተለያዩ መድረኮች መዘጋጀት አለባቸው” ያሉት ምሁሩ፤ “አሁን የሃገሪቱ ሁኔታ እንደ ቀድሞ የኔ ሃሳብ ብቻ  ይሰማ የሚባልበት ባለመሆኑ፣ ኢህአዴግ ከልቡ ተምሮ ከሆነ፣ ይህን ውጥኑን ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል” ሲሉ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡ (አዲስ አድማስ) (ፎቶ: DW እና Dassenech Tsemai)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    December 13, 2016 11:08 pm at 11:08 pm

    I guess the ruling party lacks sophistication. Who, in his right mind suggest such outright child’s game. Is that what Machivlae suggests when he said ” make you adversaries closer, so that you look benevolent and caring”. Has that been the intention, the ruling party need to understand it does not belong to the current century time frame. Safe exit the right strategy — durable peace and less costly.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule