ሰዎች መልካም ሢሠሩና ሲናገሩ ማመስገን፣ መጥፎ ሢሠሩና ሲናገሩ ደግሞ መምከርና መገሰጥ ተገቢ ነው። ምንጊዜም ሁሉም ሰው ሕይዎቱን ሙሉ ስሕተት ብቻ እየሠራ አይኖርም። መልካም ነገሮችም ይሠራል። ልዩነት የሚኖረው የትኛው ሥራው ነው የሚያመዝነው? መልካሙ ወይስ መጥፎ የሚለውን መመዘኑ ላይ ነው። በዚህ ረገድ የሻለቃ ዳዊትን ሥራዎች መዝኖ፤ የማሞገሱም ሆነ የመውቀሱ ተግባር፣ እርሳቸውን የሚያውቁ፣ አብረዋቸው የሠሩ፣ የትaምህርትና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተግባር ይሆናል። ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ለዐማራ ነገድ ድምፅ ለመሆን የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ያለ ድርጅት ነው። ስለዚህ ሻለቃውን በዚህ ንግግራቸው፣ ላለፉት 5 ዓመታት ሲጮኽባቸው የነበሩ አንኳር ጉዳዮችን እያነሱ፣ ዐማራውን ሲያወግዙ፣ በጠላትነት ፈርጀው የዘር ፍጅት በፈጸሙ ግለሰቦችና ስብስቦች ፊት በኩራት ቆመው በመናገራቸው ከልብ … [Read more...] about የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!
Right Column - Primary Sidebar
የአቶ አሰፋ ጫቦ ሞት ጉዳይ ምን ደረሰ?
አቶ አሰፋ ጫቦ ከአርባ ዓመታት በላይ ከዘለለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ጎልተው የታዩ ሰው ነበሩ። እንዲሁም ሊጽፏቸው የፈለጓቸውን ነገሮች የራሳቸው በሆነ የአፃፃፍ ስልት የሚያቀርቡ፣ ስለነበሩ በዚሁ ሥራቸው በብዙዎች ዘንድ ሞገስና ውዳሴ አትርፈዋል። በቅርቡም የትዝታ ፈለግ የሚባል መጽሐፍ አሳትመው ሕዝብ እንዲያነበው አድርገዋል። የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በአቶ አሰፋ የፖለቲካ ሕይወት ወይም ስነጽሁፋቸውን ለመቃኘት ሳይሆን የአሟታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ቬሮኒካ መላኩ ባቀረቡት ጽሑፍ ላይ ተመርኩዞ የተነሳ ነው። ቬሮኒካ መላኩ በጽሑፋቸው አቶ አሰፋ ከመሞታቸው በፊት በነበሩ ቀናት ውስጥ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኙ እንደነበር በመገልጽ ለቦርከና ድረገጽ ባለቤት ወደ ደረሰው መልዕክት ይንደረደራሉ። በመልዕክቱም ግሪጎሪ ማኬንዚ የተባሉ ሰው አቶ አሰፋን እንደሚያውቁ ሁለቱም ዓለም በቃኝ እስር … [Read more...] about የአቶ አሰፋ ጫቦ ሞት ጉዳይ ምን ደረሰ?
ሁለት የኢትዮጵያ ሴት ሯጭ ስፖርተኞች በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያሳዩት ጋጠወጥ ባሕሪና ፖለቲካዊ ምርጫ!
ይህ ትችት የኔን ጽሑፍ በሚያስተናግዱ እንደሚለጠፍ ባውቅም፤ ለሌሎቹ ተቃዋሚ ድረገፆች በሙሉ ተልኳል። ቢያወጡት አስተማሪ ነው። ብዙዎቹ ግን እንደማያውጡት ጥርጣሬ አለኝ። ምክንያቱም የፖለቲካ መሪዎቻቸውና ድርጅቶቻቸውን ጨምሮ በዚህ ትችት ስለተካተቱ ወገንተኛነታቸው ከሉጓም በበለጠ ይስባቸዋል። ለማንኛወም ለታሪክ ልኬአለሁ። አሁን ወደ ርዕሱ ልግባ። በትግርኛ በምንመስለው ምሳሌ ልጀምር፡ {ዝፀገባ ደራሁስ ምስ ፀኻድም ማሕበር ይኣትዋ} “የጠገቡ ዶሮዎች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር ይገባሉ” ይባላል። ሁለቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች እውቅ ሯጮች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር መግባቱ ምርጫቸው አድርገው ይሆናል። የጭልፊቶቹ እና የዶሮዎቹ ማሕበር የሚቆየው ዕድሜ አብረን የምናየው ይሆናል። ሰሞኑን በአጋጣሚ “ዩቱብ” ድረገጽ ላይ አንድ ማሕደር ለመፈተሽ ጎራ ስል ድንገት ያላሰብኩበትን እና አስደንጋጭ … [Read more...] about ሁለት የኢትዮጵያ ሴት ሯጭ ስፖርተኞች በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያሳዩት ጋጠወጥ ባሕሪና ፖለቲካዊ ምርጫ!
A Call To Boycott Ginbot 20 Celebration in New York
Subject: Occasion at the Church of Holy Family at 315 East 47 St on June 3, 2017 Dear Sir/Madame We respectfully ask you NOT to celebrate Ginbot 20. Unless you are protesting, your presence at the Church of Holy Family on June 3, will mean you are celebrating ethnocentrism, the torture and killings of innocent Ethiopians.Instead we ask you to spend your precious time praying for thousands of Ethiopians who have been killed and tortured, millions that are starving and millions that are denied … [Read more...] about A Call To Boycott Ginbot 20 Celebration in New York
የትግሬ-ቤጃዎች ማንነት
ይህ ጽሁፍ እንዲታተምላቸው የላኩት (Bill Teferedegn: bill.teferedegn@yahoo.co.uk) ናቸው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡ … [Read more...] about የትግሬ-ቤጃዎች ማንነት
“ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]
አንጀት አርስና አንገት አስደፊ አስተያየት አንጀታቸው ካረረ ሽማግሌ። በመስሪያ ቤታችን የግንቦት 20 በዓልን እያከበርን ነው። ክቡር ሰብሳቢው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ብዙ የበዙና የተባዙ የለውጥ ማሳያዎችን ሲናገሩ ቆይተው በመጨረሻ እንዲህ አሉ፡- "...ባጭሩ ከግንቦት 20 ድል በኋላ ተቆጥሮ የማያልቅ ብዙ ለውጥ አምጥተናል። በተለይም ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል ረገድ ሙስና በማኅበረሰቡ ዘንድ ነውር ሆኖ እንዲታይ አድርገናል። ሁላችሁም እንደምታውቁት ድሮ ድሮ... "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል"... እየተባለ በድፍረት ይነገር ነበር። ይህ ማለት ሲሾሙ መብላት ሲሻሩ ላላመቆጨት ወሳኝ መሆኑን ኅብረተሰቡ አምኖበት ነበር። አሁን ግን ይህ አባባል እየቀረና እየተረሳ ነው። ይህም የትግል ውጤት ነው።" ሰብሳቢው ይህንን በክብር እየተናገሩ እያለ ጋሽ ደፋሩ እጃቸው ላጥ! አድርገው አወጡ። … [Read more...] about “ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]
በግንቦት 20 ያተረፍኩትና የጎደለብኝ
ግንቦት 20 ከመደዴ ቀንነት ተመንጥቆ፣ ቅድስና ተቀብቶ መዘከር ከጀመረ ይኽው ሀያ ስድስት አመት ሆነ፡፡ በየካቲት 1983 አ.ም. ጎንደር በኢህአዴግ ሲያዝ፣ እኔና ጓደኞቼ እናስተምርበት ከነበረው ከጎርጎራ መንደር፣ በውጫሌ በኩል በኢህአዴግ ተሸኝተን፣ ደሴ ላይ አንድ ኩንታል ስንዴ ተመጽውተን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ውጫሌ ላይ የሸኙን የኢህአዴግ ታጋዮች ቀድመውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ ነግረውን ነበር፤ እንዳሉት ቀድመውን ባይገቡም፣ ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ከኢህአዴግ የመጨረሻ ግዛት ከውጫሌ የደርግ ግዛት እስከነበረው የሀይቅ ከተማ የነበረውን የፈሪ ምድር ያቋረጥነው በእግር ነበር፡፡ ያንን ረባዳ ለምለም ስፍራ በእግር ስጓዝ አስበው የነበረው (አሁን ምኞት ብለው ይሻላል) ልብን የሚያሞቅ፣ ብርታት የሚሰጥ ነገር እስካሁን ከህሊናዬ አልጠፋም፡፡ " . . . . ከሁሉም በላይ የደርግ … [Read more...] about በግንቦት 20 ያተረፍኩትና የጎደለብኝ
በትዕቢት አይሆንም….
ባልና ሚስት ሆነን መስርተን ትዳር ልጆችም አፍርተን አንዳችም ሳይቀር ተመሥገን ፈጣሪ ምኞቴ ተሟላ አልቀይርም ሕይወት ይሄንን በሌላ ተሥፋ ለወደፊት ምሥጋና ሣሰማ ነገሩ ሌላ ነው ለካሥ ያንቺ ዓላማ የወለድናቸውን ልጆች በየተራ መንፈሥ እየቀየርሽ በተንኮል በሤራ እየመከርሻቸው የመለየት ሥራ ቤታችን ነገሠ ኩርፊያ አተካራ የገነባነውን ሐብትና ትዳር መጠበቅ ሲገባን በጋራ በምክር አንቺ ትብሽ እኔ በለን እንደአዋቂ ቀጣይ ትዳር ሆኖ ወደፊት ዘላቂ እንዲሠፍን ሰላም እንዲከተል ተድላ ሁሌም እንደመትጋት በጋራ በመላ አንቺ ግን ጥላቻ ልጆቹን አስተምረሽ በጎሪጥ ተመልካች ከሁሉም አናክሰሽ አጥሩ እንዲላላ ከውስጥ እንደመዥገር እየቦረቦርሽው እንዳይኖረው ማገር ይጠቅሰው የነበር ሁሉም በምሣሌ ቤታችን አመራ ወደ አልባሌ ለልጆቼ ባዳ ባይተዋር ላገሩ የሌለ … [Read more...] about በትዕቢት አይሆንም….
HRC35: Addressing the pervasive human rights crisis in Ethiopia
Your Excellency, To Permanent Representatives of Members and Observer States of the UN Human Rights Council Geneva, 25 May 2017 RE: Addressing the pervasive human rights crisis in Ethiopia Your Excellency, The undersigned civil society organisations write to draw your attention to persistent and grave violations of human rights in Ethiopia and the pressing need to support the establishment of an independent, impartial and international investigation into atrocities committed by security … [Read more...] about HRC35: Addressing the pervasive human rights crisis in Ethiopia
ይድረስ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት
ከሸዋ ሕዝብ ድርጅት (Shoa People Organisation (SPO) የተሰጠውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ይድረስ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት





![“ሲሾም ያልበላ… ድሮ ቀረ” — [የግንቦት 20 ወግ]](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2015/01/eprdfs-economic-policy-233x300.jpg)


