የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን(ዮሐ 3፡11) ከዚህ በፊት በተከታታይ በወጡት ጦማሮች ተዋጊ ፋኖዎች በእነ በላይ ዘለቀ፣ መንገሻ ጀንበሬ፣ ራስ ሀይሉ በለው፣ በበዛብህ ነጋሽና ሌሎችም የየጦር መሪነት፤ አርበኞች ካህናት በእነ ሊቀጠበብት አድማሱ ጀንበሬ፣ መላከ ሰላም አለማየሁ ሻሾና ሌሎችም ካህናት አስተባባሪነት፤ በእነ ክቡር ሀዲስ አለማየሁ፣ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴና ሎችም አርበኞች ደራስያን አስተማሪነትና ቀስቃሽነት እንደዚሁም በእነ ራስ ሀይሉ ተክለሃይማኖት የጦር አማካሪነትና የጣልያንን ምስጢር አውጪነት የተፈፀመውን የጦር ጀብዱና የተገኘውን ድል ጨልፌ አቅርቤአለሁ፡፡ በቀጣይ ጦማሮቼ ደግሞ ሊቀጠበብት አድማሱ ጀንበሬ ከድህረ ጦርነት በኋላ የፈፀሟቸውን ገድሎች ለማሳሰብ አቀርባለሁ፡፡ (የክፍል አንድ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ክፍል ሁለት ሙሉ ጽሁፍ … [Read more...] about አጽማቸውን የፈለሰው መላከ ብርሃን አድማሱ ከአምስቱ ዘመን ተጋድሎ በኋላ ክፍል አንድና ሁለት
Right Column - Primary Sidebar
AN OPEN LETTER TO THE ETHIOPIAN PEOPLE:
WHAT COURSE OF ACTION NOW WILL GIVE ALL ETHIOPIANS THE BEST SUSTAINABLE ENDING TO TPLF/EPRDF DOMINATION? Dear Ethiopian, We wish you a meaningful Ethiopian New Year, hoping that Ethiopians will join with us in finding an effective and sustainable solution to the crisis as we enter the New Year. We come to you as stakeholders who care about the future of all of us. We believe sustainable peace will not come until we value the humanity of all our people, putting humanity before ethnicity or any … [Read more...] about AN OPEN LETTER TO THE ETHIOPIAN PEOPLE:
መስከረም፣ መስከረም
ኢዮሃ አበባዬ / መስከረም ጠባዬ ኢዮሃ አበባዬ / መስከረም ጠባዬ ... የወራት ሁሉ ቁንጮ መስከረም። ግንቦት እሳት፣ ሰኔ ውኃ ነው። የኢትዮጵያ ምድር በእሳትና በውኃ ሳትጠመቅ እረፍት እና ልምላሜዋን አታጋራም። ከግንቦት ማብቂያ እስከ መስከረም መጀመሪያ ሦስት ወር ብቻ ቢሆንም፣ እስኪጠባ መጠበቁ ሦስት ዓመት ያስመስለዋል። የመከራ አንዱ ቀን እንደ ዘላለም ነው፤ እግሮቹም በብረት ሰንሰለት ከብደዋል። ደስታ ግን ክንፍ እንጂ እግር የለው። ግንቦት ድርቅና ብክነት ነው። መስከረም እረፍትና ልምላሜ። ወራት መኳንንት ቢሆኑ መስከረም ንጉሥ ነው። መስከረም ደጅ ያስጠናል። ደጁን ካልከፈተ፣ ፊት ከነሳ ጥቅምትን ማየት አይቻል። አስራ ሁለቱን ወር እንደ ምን ተንፏቆ የደረሰ፣ አምስት እና ስድስት ቀን ጨምሮ ደጅ ይጠናል፤ ራሱንና ጓዳውን እንዲያዘገጃጅ ይገደዳል። ይህን ያህል ርቀት ተጕዘው … [Read more...] about መስከረም፣ መስከረም
Open Letter to Columbia University Faculty and Students:
Dr Tedros Adhanom: A TPLF central committee member, a criminal who is leading the WHO will be a keynote speaker at the Columbia University World Leaders Forum to be held on September 19, 2017 at Casa Italiana, 1161 Amsterdam Ave., New York. Dr Tedros Adhanom has been and still is a member of a killing, torturous and genocidal regime that has perpetrated crimes against humanity in Ethiopia. For the past twenty-six years, a regime controlled by his party,the Tigrayan People’s Liberation Front … [Read more...] about Open Letter to Columbia University Faculty and Students:
ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል
የህወሃት አገዛዝ 2010 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ለማክበር የጀመረውን ከባህሪው የወጣ ድርጊት ተመልክተው አንዳንዶች ስርዓቱ እውነተኛ የመንግስትነት ባህርይን እየያዘ ነው ሲሉ ይደመጣል። እነዚህ የዋሆች ሰሞኑን ከነሀሴ 26 ቀን ጀምሮ የፍቅር ቀን፣ የእናቶችና ህፃናት ቀን፣ የአረጋውያን ቀን፣ የሰላም ቀን፣ የንባብ ቀን፣ የአረንጓዴ ልማት ቀን፣ የመከባበር ቀን፣ የሀገር ፍቅር ቀን፣ የአንድነት ቀን እና የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ መለያዎች አዲሱን ኣመት ለመቀበል ህወሀት የያዘውን ፕሮግራም እንደ አንድ ማስረጃነት ሲጠቅሱ ይታያል። ታርሟል በሚል። መሬት ላይ የምናያቸው የስርኣቱ ባህርያት በምክንያት ለገመገመ ሰው ግን ስርዓቱ ለመሻሻል ፍላጎት እንደሌለው ይገነዘባል። በእኔ ምልከታ ችግሩ ከድርጅቱ ፍጥረታዊ ባህርይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ ህወሀት ከምስረታው ጀምሮ … [Read more...] about ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል
ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ
በነዚያ የነተቡ ብዕሮች "ተራራውን ያንቀጠቀጠ" እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩ ሁሉ እነሆ በአንድ ብላቴና ሲንቀጠቀጡ ከማየት የበለጠ ምስክር ከየትም ሊመጣ አይችልም። የ"ኢትዮጵያ" ስም ሲጠራ ብርክ እንደያዘው የሚሽመደመዱ፤ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እያልን በጣት የምንቆጥራቸው የጥላቻና የበቀል ጉግማንጉጎች ለመሆናቸውም ትውልድን ደፍሮ ይናገርላቸዋል። የዚህ ቡድን አባላት ከመጠን ያለፉ ጭቃዎች መሆናቸውን እንኳ ለማወቅ ራሳቸውን በመስታወት የሚመለከቱ አይመስልም። መቶ ሚሊዮን ሕዝብ እየመራ ያለው ይህ ቡድን በየትኛውም መመዘኛ ቢለካ አርቆ ማሰብ እና አስተዋይነት ይጎድለዋል። አስተዋይነት ደግሞ የታላላቆች ውድ ስጦታ ስለሆነ ከርካሽ ሰዎች አይጠበቅም። አበው ትተውልን ያለፉት አንድ ቅርስ፣ ያቺ የቀስተደመና ተምሳለት፣ ያቺ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስትነሳ አጋንንት እንደለከፈው እርያ … [Read more...] about ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ
Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
Remembering Peaceful Demonstrators Murdered by TPLF in Bahir Dar One Year Ago The area in which this took place is called Abay Mado“Kobel”, located in Bahir Dar. It was in the August of last year when all over the country, Ethiopians, including the youth were peacefully demonstrating in large numbers, expressing their displeasure towards the ethnocentric, extremely corrupt and suppressive regime of the TPLF. The youth in Bahir Dar was expressing its solidarity with “Welkite” and “Oromo” … [Read more...] about Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
ትልቅ ሰው ትልቅን
ይባላል ... ድሮም ይነገራል ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ሲባል በፊትም ሰምተናል ይኸው ዕውነት ሆኖ ሲፈጸም አየን ቃሉ በነጋሽ ገ/ማርያም፣ በተስፋዬ ሳህሉ የሐምሌ ወርን የሰላሳ ቀናት እቅፍ በነኀሴ ተክተን ሳናልፍ ሁለቱን ታላላቅ የጥበብ ከዋክብት አከታትለን አጣን የአዛውንቶች ክበብን ዘጋን ፀጋዬ ገ/መድህን በጻፈው አባተ መኩሪያ ባዘጋጀው አውላቸው ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ በተጫወቱበት ዓለሙና ሲራክ አብረው በሆኑበት እነ አስናቀች ወርቁ፣ በላይነሽ አመዴ፣ እነ አባተ መኩሪያ መላኩ አሻግሬና ዘነበች ታደሰ እነ ሠይፈ አርኣያ ሙናዬ መንበሩ፣ ኃይማኖት ዓለሙ፣ እነ አስራት አንለይ በኃይሉ መንገሻ፣ ሱራፌል በጋሻው፣ ያ ፍስሀ በላይ በተካፈሉበት ... የላይ ቤት ትዕይንት ተባብረው አብረው አንድ … [Read more...] about ትልቅ ሰው ትልቅን
ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ክምሩን የሀገር ሀብት ስርቆት ፣ ብክነት ሳስበው ... ክምር በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር መዋዕለ ንዋይ ከመቶ ባልበለጡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የመዘረፉን ወንጀል እየሰ ማን ነው ። ጥሎብኝ ገንዘቡን ወደ አባይ ግድብ አስጠጋውና የሳውዲ ነዋሪ ለአመታት ካጠራቀመው ጋር አወዳድረዋለሁ። አልገናኝህ ይለኛል ... ገንዘቡ ከፍ ሲል ሌላ ማወዳደሪያ እፈልጋለሁ ። .. ውጭ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ ወደ ሀገር ከሚልከው ገንዘብ የተገኘውን ገቢ አስበውና እንደገና የተሰረቀው ከባድ የመሆኑን ክብደት ያስደነግጠኛል ፣ እደነግጣለሁ ። "ጠፋ ፣ ተሰረቀ" የተባለው የዚህች ድሃ ሀገር ገንዘብ ስንት አውሮፕላን እንደሚገዛ ሳሰላ ውዬም አውቃለሁ፣ የሞኝ ነገር ትሉኝ ይሆናል። ግን አይደለም። የገንዘቡን ክብደት ለማወቅ እንጅ ... እንዲህ ሲቆጨኝ ስዳክር ነው የሰነበትኩት ክምሩ የሀገር ሀብት መሰረቅ … [Read more...] about ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!
የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ - የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ሰጡዋቸው። ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት አብስረዋል። እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም። ታሳሪዎቹን ሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር እንደማንኛውም ተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል? ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው - መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምን አቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል? የሙስና ጉዳይ … [Read more...] about ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!










