• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !

August 2, 2017 07:52 pm by Editor 1 Comment

ክምሩን የሀገር ሀብት ስርቆት ፣ ብክነት ሳስበው  …

ክምር በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር መዋዕለ ንዋይ ከመቶ ባልበለጡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የመዘረፉን ወንጀል እየሰ ማን ነው ። ጥሎብኝ ገንዘቡን ወደ አባይ ግድብ አስጠጋውና የሳውዲ ነዋሪ ለአመታት ካጠራቀመው ጋር አወዳድረዋለሁ። አልገናኝህ ይለኛል … ገንዘቡ ከፍ ሲል ሌላ ማወዳደሪያ እፈልጋለሁ ። .. ውጭ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ ወደ ሀገር ከሚልከው ገንዘብ የተገኘውን ገቢ አስበውና እንደገና የተሰረቀው ከባድ የመሆኑን ክብደት ያስደነግጠኛል ፣ እደነግጣለሁ ። “ጠፋ ፣ ተሰረቀ” የተባለው የዚህች ድሃ ሀገር ገንዘብ ስንት አውሮፕላን እንደሚገዛ ሳሰላ ውዬም አውቃለሁ፣ የሞኝ ነገር ትሉኝ ይሆናል። ግን አይደለም። የገንዘቡን ክብደት ለማወቅ እንጅ … እንዲህ ሲቆጨኝ ስዳክር ነው የሰነበትኩት

ክምሩ የሀገር ሀብት መሰረቅ መረጃ እንደዋዛ አጋርቸ  “ወደ ገበያ ሲረጭ ጣራ የነካውን ኑሮ ሽቅብ ስለሚያጉነው እውነት ምን ትላለህ?” ያልኩት አንድ የምጣኔ ሀብት ተንታኔ ያጫወተኝ ቀልቤን ጨምድዶታል።  ብሩን ወደ ኢንዲስትሪ ቀይሮ ለሳውዲ ተመላሽ አስተማማኝ ገቢ እንሚፈጥርም ሲያሰላው ሀገሬ የገባችበትን የዝርፊያ መቀመቅ በቁጭት አሰደመመኝ ። … ግን ክምሩን የሀገር ሀብት ስርቆትና ብክነትና ጫፍ የነካ ሙስና ሳስበው ባልበቃቃ ምክንያት የሚሰቃዩት ጎልማሳ ወጣት ትንታጎች ስቃይ አመመኝ እነሱ ትልልቅ አሳዎች ናቸው … የሚታሰሩት በክብር፣ ፍርድ ቤት የሚቀርቡት በክብር ፣ ወህኒም የሚወርዱበት ሁኔታ አይታወቅም ..

የክምሩ ዘርፊያ ተዋናኞችን ትላልቅ  አሳዎችን አስቤ … ሀሳባቸውን በነጻ በገለጹ ፣ ለሀገራቸው መጻኤ ህይዎት ህልም ባለሙ ፣ የሚሳደዱት ፣ የሚታሩት ፣ እድሜያቸውን በወህኒ የሚያሳልፉት ግፉአን ታወሱኝ ፣ ምክንያቴ የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከእስር መፈታት ሆኖ ድምጽ ጠራኝና የግፍ መንገድ  ፣ በጉድ ሀገር ብዬ ቀጠልኩ …

የግፍ መንገድ፣ በጉድ ሀገር …

በዚህ ሁሉ መካከል ያን  ሰሞን ወጣቷ ንግስት ይርጋ በማዕከላዊ የደራባትን መራራ ስቃይ ሰምተን ባይገርመንም ፣ ተበሳጨን  ሀዘናችን ሳይበርድ ሌላ ሌላ ሰማን …ከቀናት በፊት ደግሞ ጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፊሰር መራራ ጉዲና “ፍርድ ቤት የፍጥኝ ታስሮ ቀረበ” የሚል መረጃ ተሰራጨ … የብዙው ሀገር ወዳድ ቅስም ተሰብሮ ተመለከትኩ … እኔን ግን አልደንቅህ አለኝ፣  አላመመኝም አበሳጨኝ እንጅ … በዚህም መካከል የታሳሪው ጋዜጠኛ የኤልያስ ገብሩና የጎልማሳው ፖለቲከኛ የዳንኤል ሽበሽ በዋስ የመፈታት መረጃ ሰምተናል … የዋስ ብር ጠፋ ተብሎ ስንታመስ ያ የተገፋው ትንታግ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው መዠረጥ አድርጎ የዋስ ብሩን መክፈሉን ስሰማ ደስታዬ ወሰን አጣ … በዚህ መካከል ነው እንግዲህ ግፍ ያተገታው የወጣት ጎልማሳው ፣ ግፍ ያልተንበረከከው መንፈስ የታየኝ …

ግፍ ያልገታው ፣ ያልተንበረከከው መንፈስ …

ከባለ ብሩህ አእምሮው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከምናውቀው መሳደድ  ፣ መታሰር ፣  መገለል ፣ መገፋት  … መክሳት መጥቆር አልፎ ብዙ አይተን ሰምተናል…ትንታጎቹ ሀገር ወዳድ የሀገሬ ልጆች ግን አልሸሹም… በእስክንድር  እግር ሳተናውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሞጋች ብዕሩን ሲያነሳ በእርግጥም ነበልባል ብዕሩ በእውነት የተሞላ ነበርና ትንታኔው ይለበልባል፣ አሸብሯል … እናም በኢትዮጵያዊነት ጠንካራ መንፈስ ልቡ የተንቀለቀለው ጋዜጠኛ እስክንድር ስቃይ ተሜ አላሸሸውም …  ብርቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተራው ተሳዶ፣ ታስሮ፣ ተፈረደበት …በእስር ላይ እስር ይሆንበት፣ ይጨልምበት ዘንድ በጨለማ ቤትም ተወረወረ ጨለማ አልገታውም!!! … ተመስገን የህግ አሳሪ ህገ መንግስታዊ መብቱ ሲገፈፍ በእናቱ እንዳይጎበኝ ከመደረግ ጀምሮ፣ ህክምና የማግኘትና በጠበቃና በሀይማኖት አባቶች የመጎብኘት መብቱን ሳይቀር ተገፎ ከርሟል … ይህ ሁሉ ስቃይ ግን ጋዜጠኛ ተመስገንን ቀርቶ ሊጠይቀው አሳር መከራውን እያየ ያለውን ወንድሙን ታሪኩን ታሪኩ ደሳለኝ መንፈስ አላንበረከከውም… !

ግፍ ሲበዛ፣ ታሪክ ራሱን ደገመ፣ ምሬት ሌላ ትንታግ ይወለድ ዘንድ ምክንያት እንጅ የወጣቱንና የጎልማሳውን ሀገር ወዳድ ልብ አላንበረከከውም… መንፈሰ ጠናካራው ታሪኩ ደሳለኝ ፖለቲለኛ አይደለም ፣ የላቀ እውቀትን ያዳበረ የፊልም ጥበበኛ ነው … የመገፋት መረጃ ትረክቱን ደጋግሞ  አጋርቶናል …ከቀናት በፊት በጠራራው ጸሐይ በመሃል አዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ገጀራ የያዙ ወሮበሎች ሞባይሉን ነጥቀው የፈጸሙበትን ደብደባና ዝርፊያ ላነበበ ታሪኩ ደሳለኝ  በሙያው ከጋዜጠኞቹ ከእኛ በላይ መጻፍ መቻሉን ምስክር እንሰጥ ዘንድ ቀልባችን ደጋግሞ ወስዶ አሳዝኖናል… ወንድሙን ብሎ በሄደበት መንገድ ግን ሲገፉት ፣ሲጨቁኑት የነጻነት መንፈሱን ፈትነው የወንድሙን የደም ውርስ አወረሱት … እየጎነተሉ እያማረሩ፣ እያስከፉ የሆነውን ቀሽሮ የሚጽፍ ጎበዝ ጋዜጠኛ አደረጉት!

የጋዜጠኛ እስክንድር መገፋት ጋዜጠኛ ተመስገንና ወንድሙን ብቻ አላሳየንም…መግለጽ ለሚቸግረኝ ትንታግ ሀገር ወዳዶች ተመልክተናል … ፖለቲለኛው፣ አክቲቪስቱ፣ ጋዜጠኛውና ተራው ዜጋ ሲገፋ መብት ይከበር ዘንድ የሚጽፉ ትን  የቀደመው ሆነ አሁን የምንሰማው የማዕከላዊ ማሰቀያ እስር ቤት አሰቃቂ ድብደባና ምርመራን እየሰማን የፈራ የለም። ግፍ በበዛ፣ በተሰማና በታየ ቁጥር ጭራሹኑ ወጣቱ ጎልማሳው አምርሯል። የትንታግ ወጣት ታዳጊዎችንና ጎልማሳ ሀገር ወዳዶችን ወኔ የንግስት ይርጋ የመረረ መብት ገፈፋ፣ ሰሞነኛው የዶር መራራ ጉዲና ልብ ሰባሪ አያያዝም ሆነ በፍርድ ቤት ሞቱ በተነገረው ታሳሪ ጎልማሳ አየነ በየነ  ነጋሳ ህልፈት ማንንም ሊያስፈራና ሊያሸሽ አልተቻለውም። ጭራሽ ወጣት ጎልማሳው ለነጻነት መብቱ በሰላማዊ መንገድ ይታገል ዘንድ ያበረታው እንጅ የሚያምበረክክ የሚያሸሽው አይመስልም። አጠንክሮት አየን እንጅ … ሲገፉ ስለ መጠንከር፣ ሲቀጠቀጡ ስለ በመበርታት ስናወሳ የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የፖለቲከኛው የዳንኤል ሽበሽ የወራት ስቅየት እንግልት ይዘከራል …

እንኳንም ተፈታህ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ  …

መገፋት የወለደው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከወራት እንግልት በኋላ በመፈታቱ ደስ ብሎኛል ፣ ጎልማሳው ፖለቲከኛው ዳንኤል ሽበሽም ነገ ከእስር ይፈታል ተብሏል ሁሉም ግፍ ያበረያቸው፣ ግፍ የወለዳቸው ሀገር ወዳዶች ናቸው። ያሳለፉት ስቃይ አይገድባቸውም፣ መታሰር መገፋታቸው ነገም እንደ ትናንቱ ለነጻነት መብታቸው ከመናገር ፣ ከመመስከር የሚገታቸው አልሆነም ። የወጣት ጎልማሳው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊነት ወኔ አልተቻለም!

ከመታበይ ወጥቶ በሰከነ አዕመሮ እየሆነ  ያለውን  መንገዱን ለማይገመግመው ፖለቲከኛ የማያየው እውነት ይታየናል …በእርግጥ የወደፊት የሀገር ተስፋ ሀገር ወዳዶችን ጊዜ በእስር ማባከን የሀገርን ተስፋ ማጨለም ጭምር ነው …በእርግጥ የወደፊት የሀገር ተስፋ ሀገር ወዳዶችን ገላ በምርመራ ዱላ እየመተሩ ማኮላሸት የታሪክ ጠባሳን ከትውልድ ትውልድ ያወርሳል እንጅ ትውልዱን አይጠቅምም። በአደባባይ የቀሪውን ሞራል ለመስበር የአዕምሮ ጦርነት በአደባባይ መክፈት ፣ የሀገርን ተስፋ ማኮላሸት ፣ የማደግን ህልም ማጨለም ጭምር መሆኑ ሊገባቸው ይገባል!

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እንኳን በሰላም ከቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ከአድናቂ አፍቃሪዎችህና  ከሚወድህ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጋር ተገናኘህ!

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 27 ቀን 2009 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    August 5, 2017 05:01 pm at 5:01 pm

    ውድ ጎልጉል፣ እስክንድር ነጋን ለአዲስ ዘመን ወያኔ ይፈታል ብዬ እገምታለሁ። ለአሜሪካኖች ጌቶቻቸውን ሲሉ። እስክንድር ከአገር እንዲወጣ ጭምር ያደርጋሉ። ሁልጊዜ ከግፍ አይጸዱም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule