አቶ ማሞ፣ የዘመናይና የእስከዳር አባት፣ የወ/ሮ ከልካይ ባለቤት፣ አንድ ወፍጮ ቤት አላቸው። እህልም ይነግዳሉ። ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ እዚያው ገዝተው እዚያው የሚያስፈጩ ደምበኞች ሞልተዋል። አቶ ማሞ በሰፈሩ ተወዳጅ ናቸው። ተወዳጅ ያደረጋቸው ደግሞ ምርቃታቸው ነው። ምርቃቶቹ በቄንጥ የተደረደሩ ቃላት ሳይሆኑ 50 ኪሎ ጤፍ ላይ ሁለት ወይም ሶስት ኪሎ መጨመራቸው ነው። “እጅ አጠረኝ ...” ላለ ጎረቤት ደግሞ መልሳቸው፤ “ምን ችግር አለ! ሲያገኙ ይከፍላሉ ...” ነው። የተበጠሰ ቺንጋ እየቀየሩ፤ መፋቂያ የተሰኩባቸውን ጉራማይሌ ጥርሶቻቸውን በፈገግታ ብልጭ እያደረጉ። አቶ ማሞ ሃብታም አይደሉም። ድሃም አይደሉም። የሚያገኙት ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ይበቃቸዋል። ያቶ ማሞ መኖሪያ ቤትና ወፍጮ ቤት የተያያዘ ነው። አጥር ነው የሚለየው። ሌሊት ወፍጮ ቤቱ ሲዘጋ እንዳይላሉ የሚባለው፤ ቀኑን … [Read more...] about “ባቡር ይሄድበታል”
Opinions
ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!
በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር - ህወሃት ሰሞኑን ዕቅድ ብሎ ባወጣው ዘገባ ላይ ለዓመታት ሲወራለት የነበረው የድርብ አኃዝ ዕድገት እንደተደሰኮረለት እንዳልሆነ እንዲያውም ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን የሥራ አጥነት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ በከተማዎች ብቻ ሳይሆን በገጠርም ችግር እየሆነ መምጣቱን ለራሱ ባመነበት የኢኮኖሚ ፕላን ላይ አትቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- መንግስት ኢኮኖሚው ውድቀት ላይ መሆኑን አመነ • የኢኮኖሚ መዋቅሩ ከሳህራ በታች ከሚገኙ ሀገራትም ያነሰ ነው • የወጪ ንግድ ገቢ እና የገቢ ንግድ ክፍተት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል • ለውጭ ገበያ የቀረበው አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ ሰሊጥና … [Read more...] about ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!
“እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል”
ለ900ሺ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ የእርዳታ እህል የጫኑ መኪኖች ሰሙኑን መቀሌ ከተማ ደርሰዋል። አንድ ሚሊዮን ለሚጠጋ ተረጂ እስከ 350 መኪኖች እህል ጭነው በቀጥታ ከጅቡቲ ትግራይ ገብተዋል። መንግስት እንዳለው የጫኑት ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ሳይሆን ከውጭ በእርዳታ የገባ መሆኑ ጭነው የመጡት ሹፌሮች አውግተውኛል። "ድርቁ በቁጥጥር ስር ኣውለነዋል" የሚል የትግራይ መንግስት መግለጫ ተደጋግሞ እየተሰማ ባለበት ቅፅበት "ለእርዳታ የመጣው እህል እየተሸጠ ነው" የሚል ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው። እህሉ መቀሌ ከተማ ወደሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጠ መሆኑና ጥያቄ ላነሱ ሹፌሮች ደግሞ "ድርቁን በቀላሉ ስለተቆጣጠርነው ትርፉ ተሽጦ ለአባይ እንዲሆን ተወስኗል" ተብሎዋል። ከእኔ ጋር ሁኖ ጨዋታው ሲያዳምጥ የነበረው ወጣት "… የትኛው አባይ ነው? አባይ ግድብ፣ አባይ … [Read more...] about “እርዳታው እህል ተሽጦ ለ “አባይ” እንዲውል ተወስኗል”
ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ ኤሊ ውሃ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም ስለተፈጸመው ግድያ መረጃ ልከውልናል፡፡ ከመረጃ አቀባያችን ጋር በተደጋጋሚ በተላላክነውና ባቀረብነው በርካታ ጥያቄዎች መሠረት ያገኘነው መረጃ ይህንን ይመስላል፡- እጅግ ዘግናኝ የሚባለው ግድያ የተፈጸመው ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ በሚገኘው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የእማኝ ዘጋቢው በራሳቸው አገላለጽ እንዲህ ዘግበውታል፡- (የላኩልን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም ሲሆን ወዳማርኛው እንዲህ መልሰነዋል) “ወንጀሉ የተፈጸመው ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ በኤሊውሃ ከተማ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ ነው፡፡ የተቃጠለው ልጅ ወልዱ ይባላል፡፡ በ(ፕሮጀክቱ) … [Read more...] about ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
ነጻ አውጪ ግምባር አገዛዝ እንጂ መንግሥት አይመሠርትም
ላለፉት 25 ዓመታት በነጻ አውጪ ግምባር ስም ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር "ኢህአዴግ" ብሎ በፈጠረው ስያሜ አገር በግፍ እየገዛ መሆኑ ሳያንስ በየአምስት አመቱ በሚያካሂደው "ምርጫ" የሚመሠርተው "መንግሥት" መፍትሔ ሊሰጥ እንደማይችል መድረክ አስታወቀ። ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሃብ የአገዛዙ ፓርቲ ተጠያቂ ነው ይላል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ "ኢህአዴግ ያቋቋመው መንግስት መፍትሄ አይሰጥም ተባለ" በሚል ርዕስ ያወጣው ዜና ከዚህ እንደሚከተው ይነበባል:- ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለው ረሃብ የገዥው ፓርቲን ፖሊሲ ውድቀት ያሳያል ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ፡፡ ኢህአዴግ ያቋቋመዉ አምባገነን መንግስት ለኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ ሊሰጥ አይችልም ሲል ታቃዋሚዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ … [Read more...] about ነጻ አውጪ ግምባር አገዛዝ እንጂ መንግሥት አይመሠርትም
ኑሮ በመፈክር
አቶ ዠ 57 አመታቸው ነው። መተዳደሪያ አላቸው። እንዴት ያለ ሙያ!! ባሥራ ሰባት አመታቸው የጀመሩት። አርባ አመት ሙሉ ያለማቋረጥ እየሰሩ ያሉት። ሰዉ ከሥራው በመንግሥት ለውጥ፣ በሰበብ ባስባቡ ሲባረር እሳቸው ሥራ አላጡም። ሥራቸው? መፈክር አድምቆ መጻፍ። መጀመሪያ በሁለት ቃላት ጀመሩ። በነጻ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብለው አድምቀው ጻፉ። ከዚያ እየተከፈላቸው ደግሞ “ከቆራጡ መሪ ጋር ወደፊት!!” ብለው ቀጠሉ። ሰውየው ብቻቸውን ሲቀሩ። ወደ መጨረሻው ግድም ደግሞ “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት” ብለው ደጋግመው አድምቀው ጻፉ። “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ዝምባብዌ!” ብለው አላፌዙም። አቶ ዠ ፕሮፌሽናል ናቸው። የከፈለ ያጽፋቸዋል። ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ መፈክሮቹም መርዘም ጀመሩ። አንድ ገጽ የሚሆን መፈክር ጻፍ ሲባሉ እንኳን “እሺ፣ ሂሳቡ ይሄ ነው” ብለው … [Read more...] about ኑሮ በመፈክር
The True Ethiopiawinet We Never Knew
Let’s get to the bottom of this. Make a distinction first: ETHIOPIAWINET is a concept we already know. TRUE ETHIOPIAWINET is what we never knew. The DNA of TRUE ETHIPIAWINET is the inherent incessant drive to actualize equality among all ethnic groups in real life that goes beyond mere talk. The reason for such drive is not so that we may become Ethiopians, but because we already are Ethiopians. When the various masks that were put on us by the leaderships of the ages from ancient time till the … [Read more...] about The True Ethiopiawinet We Never Knew
Human Rights for Human Beings
Mr. Obang Metho speaks to Ethiopian Muslims in Washington DC about the widespread human rights violations in Ethiopia and the need for justice, freedom, tolerance, mutual respect and human dignity. I would like to thanks First Hijraha Foundation for inviting me to speak to you today on the very important topic of human rights. It is good to be here with all of you. I also thanks the First Hijraha Foundation, UEM-PMSG, Risala Intentional and Oromo Muslims Foundation for this very nice and … [Read more...] about Human Rights for Human Beings
ደመራ
ሰላሙ የደፈረሰበት ህዝብ የመንፈስ ጤንነት አይሰማውም። ሰላምና ጤና የሚነጣጠሉ አይደሉምና፤ የመንፈስ ጤንነት የደፈረሰበት ህዝብ ጤናማ ነው ማለት አይቻልም። “ሰላም ሳይኖር ሰላም የሚሉ ወዮላቸው!” ከሚለው ከነብያት ቃል ጋራ ተጋጨ። ይህም ብቻ አይደለም። ሰላም የሌለን ቄሶች ሰላም እንደሌለን እያወቅን፤ የተቀጠርንለት እለታዊ ገቢያችን እንዳይቀርብን “ ሰላም ለኩልክሙ” እንላለን። በጥቅሉ ልማድ አድራሾች ሆን። የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነን የምንል ኢትዮጵያውያን ሰላም ምንጭ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊወሀደን ቀርቶ አልተቀበልነውም። ከዚህ ዓመት የደረስነው አሁን ያለንበት “በደብረ ሰላም ኢይኩን ሀከክ” ማለትም፦ በደብራችን ህውከት ብጥብጥ አይኑር” እያልን ጉሮሯችን እስኪሰነጠቅ የምንጮኸው ላምድ ለማድረስ ብቻ ነው። ስለዚህ “እንኳን አደረሳችሁ” እንጅ “እንኳን በሰላምና በጤና … [Read more...] about ደመራ
ነገረ – ኢሕአዴግ
በብዙ መልኩ ዴሞክራሲያዊ ገፅታን ያልተላበሰው ኢሕአዴግ ራሱን በገዥ መደብነት "አመቻችቶ" አስቀምጧል፡፡ ግንባሩ በቀደመው ዓመት አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በዝግ በማካሄድ እንደተለመደው ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቋል፡፡ በዚሁ ጉባኤ፣ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ጉባኤዎች በተለይም በ1994 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከተካሄደው አራተኛው የድርጅቱ ጉባኤ ጀምሮ ይነሱ የነበሩ አጀንዳዎች ቅርፃቸውን ብቻ በመቀየር ይዘታቸውን እንደጠበቁ እስከ አስረኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ድረስ ዘልቀዋል፡፡ በተለይም የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና ጉዳይ ከድርጅቱ ጋር አብረው የተፈጠሩ እስኪመስሉ ድረስ ችግሮቹ ገንግነዋል፡፡ በ1994ዓ.ም የአዲስ አበባው ጉባኤ አብይ አጀንዳ በመሆን ጉባይተኛው የተወያየበት አጀንዳ "ጥገኛ ዝቅጠት አስተሳሰብ" የስርዓቱ አደጋ መሆኑን ነበር፡፡ የቃላት ሃብታሙ … [Read more...] about ነገረ – ኢሕአዴግ


![ኢኮኖሚው [እንዳወራነው] አላደገም!](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2014/06/poor1-300x157.jpg)







