• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Opinions

ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

November 6, 2019 09:21 am by Editor Leave a Comment

ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር “አለማወቅ” ነው። ይህን ስል ለአንዳንዶች ንቀት አሊያም እብሪት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ስለ እኔ የሚኖራችሁ ስሜት ያነሳሁትን ሃሳብ ቅንጣት ያህል አይቀይረውም። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ያለው መሰረታዊ ችግር አላዋቂነት ነው። አዋቂ ማለት ጠያቂ ነው። ምንም ነገር ሲሆን “ምን? የት? እንዴት? ለምን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ያነሳል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ሲያገኝ እርምጃ ይወስዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጥያቄ የሚጀምረው ከድርጊት በኋላ ነው። በተለይ የዛሬ ትውልድ የፊት ገፅታሀን የሚያጣራው አንገትህን በሜንጫ ቆርጦ ከጣለ በኋላ ነው። ለምሳሌ አቶ ጃዋር መሃመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ “ተከብቤያለሁ” ብሎ ሲፅፍ በዚያ ውድቅት ሌሊት ወጣቱ ድንጋይና ፌሮ ይዞ መሮጥ ከመጀመሩ በፊት “ጃዋር ማንና የት ነው? ጃዋር ለምንና እንዴት … [Read more...] about ጃዋር እና ህወሓት፤ ከክህደት የመነጨ የባላንጣዎቹ ፍቅር!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre, Left Column, tplf

የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

November 5, 2019 07:01 pm by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት 30 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች! ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ መሸሸቱንና ገንዘቡንም ለማስመለስ መንግሥት ከባድ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀገር የሸሸውን ገንዘብ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ቢጠይቅም መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለው አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዳልታዬ ምሁራኑ ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ እንደገለጹት በኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት በሙስና እና ማጭበርበር የሸሸው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጧል፤ ገንዘቡም በወቅቱ የኢትዮጵያን የስድስት ዓመት ተኩል በጀት መሸፈን የሚችል … [Read more...] about የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: 30 billion, Right Column - Primary Sidebar, tplf

ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!

October 28, 2019 01:31 am by Editor Leave a Comment

ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!

“በብዙ እብዶች መካከል ጤነኛ ያብዳል” ይባላል ይህን እውነታ ኡመር ሱሌማን ነው ከ18 አመት በፊት የተናገረው። ብዙ ሰዎች የወደዱት እምቢ ካለ ወይም እነሱ የጠሉትን ከወደደ “እብድ” ወይም “ከሃዲ መባሉ አይቀርም። በዚህ ውስጥ አልፈን ነው የመጣነው እኔ ጤንነቴን በደንብ አውቀዋለሁ የሰውም ማረጋገጫ አልፈልግም ለሰውም እንደዛው ትልቅና አስቀያሚ በሽታ ነው ያለው። ይህን ለማከምና ለማስተካከል መታገል ትክክል ነው ግን ደግሞ ትግሉ አገር በሚያፈርስ መልኩ መሆን የለበትም። የፈለገ ችግር ቢኖር ከየመን ከሊቢያና ከሶሪያ ኢትዮጵያ ትሻላለች! የመንን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንጂ ኢትዮጵያን ወደ የመን መውሰድ ጤንነት አይደለም። ሩዋንዳን የዘነጋ ሰው በራሱ በሽታ ነው። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ይቸግር ይሆናል። ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ያለንንም ማስታወስ ተገቢ ነው … [Read more...] about ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre, Right Column - Primary Sidebar

እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!

October 27, 2019 07:00 pm by Editor Leave a Comment

እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!

በመጀመሪያ "የለውጡን (ሥሌት) የሰራሁት እኔ ነኝ" አለ - በዝምታ "አዎ ነህ" ተባለ ቀጠለና "እዚህ ሀገር ሁለት መንግሥት ነው ያለው የአብይ እና የቄሮ [የኔ]" አለ አሁንም በዝምታ "አዎ ልክ ነህ" ተባለ መንግሥት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጃዋር መንግሥት በንግግር ብቻ ሳይገታ ውሳኔዎችን መሻር ማሳለፍ ጀመረ - በዝምታ መንግሥትነቱ ተረጋገጠለት እነሆ አሁን ደግሞ ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የመንግሥት ሰዎች፣ አኩራፊዎች እና ጥገኛ ባለሀብቶች በተቀነባበረ ሴራ "ኢመደበኛው መንግሥታችሁ ሊገረሰስ ነው" ተብሎ (“የመግደል ሙከራ” በሚል ፈጠራ) 67 ንፁሃን ምስኪኖች ያልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይፀና፤ ምሽጉም ይጠነክር ዘንድ መስዋዕት ሆነው ቀረቡለት። ይሄን ጊዜ በዝምታ አያልፉም ስንል - ተናገሩ! ምን አሉ "አንተ ዐይን ነህ - እንደ ብሌናችን … [Read more...] about እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, jawar massacre, Right Column - Primary Sidebar, tplf

“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ

October 27, 2019 04:32 pm by Editor 1 Comment

“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች! የኢትዮጵያን ሕዝብ በአፈና፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ ጥሰት ሲገዛ በነበረው ህወሓት እና በሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቡድኖች በገዥነት ዘመናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል አገርን ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ተረድተናል። በተለይም አሁን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ ሌሎች አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ የሚያደርገው ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን የውህደት እንቅስቃሴ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ከማጣጣል ጀምሮ፣ የተለያዩ የትርምስ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን … [Read more...] about “የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ

Filed Under: News, Opinions Tagged With: hacked, jawar, jawar massacre, Left Column, tplf

ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!

October 25, 2019 07:37 am by Editor Leave a Comment

ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!

በተለያየ አጋጣሚ ከሚያጋጥሙኝ አስተያየቶች አንዱ ጃዋር መሃመድን መነጋገሪያችን ማድረጉን እንተው፤ግለሰቡ የሚሰጠንን አጀንዳ አንስተን በመተንተን ሰውየው የሚፈልገውን ክብር በመስጠት ተፅኖ ፈጣሪነት እንዲሰማው አናድርግ የሚል ነው። በግሌ ስራየ ብሎ ሰውን ማጉላትንም ሆነ ሆን ብሎ ሰውን ማሳነስን ብቻ አላማ አድርጎ መጓዙ የብልህ መንገድ አይመስለኝም። ጠቃሚው ነገር የሰው ስራ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩ ይመስለኛል። በዚህ ሁኔታ ግባችን ግለሰቦች ሳይሆኑ የግለሰቦች ሃሳብ እና አካሄድ የሚያመጣው በጎ ወይ መጥፎ ተፅዕኖ ነው። በጎ ወይም መጥፎ ተፀዕኖ ያመጣውን የሰዎችን ስራ በተመለከተ ስንነጋገር የሰዎችን ስም ማንሳታችን ደግሞ አይቀርም። በጎውን ስራ ስናወድስ፤ መጥፎው ስራ ወደ ባሰ መጥፎ እንዳያድግ ልንነጋገርበት ስናነሳሳው ከግለሰቦች ጋር የተለየ ፀብ ወይም … [Read more...] about ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!

Filed Under: Opinions Tagged With: jawar, Right Column - Primary Sidebar, tplf

ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!

October 24, 2019 09:39 am by Editor Leave a Comment

ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!

ማነው የዋሸው? ጃዋር? የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወይስ የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር? መንግሥት በሕዝብ ገንዘብ ጥበቃ የሚያደርግለትን ጃዋርን በሌሊት የሚከብበት ምን ምክንያት አለ? ማለቴ ተከቦ የተቀመጠው በመንግሥት ጠባቂዎች አይደለም ወይ? ለምን ጃዋርስ ተፈጠረ የተባለውን ነገር ሆን ተብሎ በመንግሥት የተቀነባበረና “እኔን ለማጥቃት የተፈጸመ ድርጊት ነው” አለ? ማለቴ ይህ ዓይነት ጥርጣሬ ካለው እንዴት በመንግሥት ታጣቂዎች እየተጠበቀ ዕንቅልፍ ወስዶት ያድራል? እንዴት እንዲህስ ሊያስብ ይችላል? ወይስ ጠባቂዎቹን የራሱ አድርጓቸዋል? ከመቼ ወዲህ ነው የመንግሥት ታጣቂዎች በመንግሥት ተመድበው ሳለ ራሱ መንግሥት፤ ለዚያውም እንደ ጃዋር አገላለጽ ዋናው ኮማንደር ለቃችው ውጡ ሲላቸው እንቢ ሊሉ የቻሉት? ከመንግሥት ይልቅ ታዛዥነታቸው ለጃዋር ያደላ ነው ማለት ነው? በዚህ ዓይነት … [Read more...] about ጃዋር መሃመድ “አጋችና ታጋች” የሆነበት ድራማ!

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

“የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ አለበት” የሐዋሳ ነዋሪ

July 19, 2019 06:52 am by Editor Leave a Comment

“የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ አለበት” የሐዋሳ ነዋሪ

ኤጄቶ ሁከት የሚያስነሳው ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ነው አንድ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ አሁን በስልክ የነገረኝን ላካፍላችሁ። እሱ በሚኖርበት አከባቢ የተወሰኑ የሲዳማ ወጣቶች አንድ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች መስሪያ ድርጅትን በእሳት ለማቃጠል ጥረት ያደርጋሉ። ነገር ግን የአከባቢው ማኅብረሰብ ተሯሩጦ ድርጊቱን ለመከላከል ይሞክራሉ። በዚህ መሃል የደቡብ ክልል ፖሊሶች በፓትሮል መኪና ከቦታው ይደርሳሉ። በድርጊቱ የተሳተፉ ወጣቶችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፈፅሞ አልሞከሩም። ከዚያ ይልቅ በዚህ የወንጀል ተግባር የተሰማሩትን ወጣቶች ከአከባቢው በቶሎ እንዲሸሹ በምልክት ይነግሯቸዋል። ወጣቶቹም መንገድ ለመዝጋት የደረደሩትን ድንጋይ እያነሱ ወደ ሌላ ቦታ ሄዱ። በኋላ ላይ የሌላ ምስኪን ነዋሪን ሃብትና ንብረት በእሳት ያወድማሉ። በአጠቃላይ ሐዋሳ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚቀሰቀሰው ከክልሉ ፖሊሲ … [Read more...] about “የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ አለበት” የሐዋሳ ነዋሪ

Filed Under: News, Opinions Tagged With: Left Column

ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም

February 6, 2019 10:04 am by Editor Leave a Comment

ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም

ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሕዝቡ መሪውን ራሱ እንዲመርጥ የሚያስችለውን አሠራር  (ፕሬዚዳንታዊ መንግስት) ወይም ደግሞ እንደ አሁኑ ፓርቲው መሪውን እንዲመርጥለት የሚያደርገውን አሠራር (ጠቅላይ ሚኒስቴራዊ መንግስት)፤ ከሁለቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ፈቃዱን እንዲያስታውቅ ለሕዝቡ በሪፈረንደም ዕድል ይሰጠው ዘንድ ለመሞገት አራት ማስረጃዎች አቀርባለሁ። 1ኛ/ ሕዝቡ አዋቂ ነውና እናውቅልሃለን ከእንግዲህ አይሰራም እናውቅልሃለን የሚሉ ሊሂቃን አንዴ ንጉስ፥ አንዴ ፕሬዚዳንት፥ አሁን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እያሉ መንግስት መሰረቱ።  የለውጥ አየር እየነፈሰለት እፎይታን በማጣጣም ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእሳት ተፈትኖ አዋቂ የሆነ ነውና፥ ዛሬ ላይ ቆመን ቀንበር እንደ በፊቱ ባናሸክመው መልካም ነው።  ጊዜውን የሚመጥን አካሄድ በመከተል ሕዝቡ መሪዉን ብቻ ሳይሆን የመንግስቱን … [Read more...] about ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

መሬት ላራሹ! Land tenure!

February 6, 2019 09:54 am by Editor 1 Comment

መሬት ላራሹ! Land tenure!

የኢትዮጵያን የክልሎች ወሰን ጥያቄ የሚፈታው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሲመለስ ነው። የኢትዮጵያ ህገ-መግስት አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 6 ላይ ሲናገር “የኢትዮጵያ መሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች…” ይላል። ይህ ማለት የሃገሪቱ መሬት በብሄሮች የተያዘ የቡድን ሃብት ነው ማለት ነው። የደርጉ መንግስት መሬትን ከከበርቴው ነጥቆ ለመንግስት ያደረገ ሲሆን ይሄኛው መንግስት ደግሞ  ለቡድኖች ኣድሏል። እነዚህ ሁለት የመሬት ሃብት ዝውውሮች ችግሮች ኣሉባቸው። መሬት ላራሹ ማለት መሬት ለሚሰራበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወይም ለዜጋው ከነ ሙሉ መብቱ ይሰጥ የሚል እንድምታ ነው ያለው። ይህንን ጥያቄ መመለስና የመሬትን የሃብት ዝውውር ከቡድን ወደ ግለሰብ በማዛወር የወሰን ጥያቄዎችን እስከ ሃቹ መፍታት ይቻላል። ይህ የተቋቋመው የማንነት ኣስተዳደርና ወሰን ኮሚሽን ይህንን ኣሳብ … [Read more...] about መሬት ላራሹ! Land tenure!

Filed Under: Opinions Tagged With: land, Left Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • Page 2
  • Page 3
  • Page 4
  • Page 5
  • Page 6
  • …
  • Page 159
  • Next Page »

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule