ለጎልጉል የእማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በላኩልን መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሣው ንቅናቄ ወደ ሲቪል ሠራተኞች ዘልቆ እንዳይገባ ስጋት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ ሠራተኞችን ማባበልና ማንቃት ጀምሯል፡፡ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በሲቪል ሠራተኝነት የሚታወቁ ዜጎችን ኢህአዴግ በየቦታው መሰብሰብ ጀምሯል፡፡ እማኙ በላኩት መረጃ እንደገለጹት ለሁለት ቀን በሚካሄደው ስብሰባ በየወረዳው ለሚሰበሰቡ ሠራተኞች ቢያንስ ብር 300 አበል በመስጠት የማባበያ ስብሰባው እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በየወረዳው ካለው ሲቪል ሠራተኛ አንጻር ለአበል የታሰበው ብር በሚሊዮን ሊቆጠር እንደሚችል እማኙ ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ዋናው አጀንዳ ሲቪል ሠራተኛው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ ተሳታፊ እንዳይሆን፤ እንዳይተባበር፤ ድጋፍ እንዳይሰጥ፤ … ሲሆን … [Read more...] about በሕዝባዊው ንቅናቄ ኢህአዴግ ሠግቷል
News
ተቃውሞ በዝምታ
* እስካሁን አምስት ሰዎች ሞተዋል ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ጋዜጠኝነት “አሸባሪነት” በመሆኑ መረጃ እንደልብ ባይገኝም ከተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የተማሪዎች ሰላማዊ የዝምታ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ እንደሚነገረው ዘገባ ከሆነ ስማቸውና የመኖሪያ ስፍራቸው የአንዳንዶቹም ከነፎቶዋቸው ይፋ የተደረገው መረጃ ላይ እንደሰፈረው የተማሪዎች ንቅናቄ ከተጀመረ እስካሁን የአምስት ወገኖች ህይወት በህወሃት ታጣቂዎች አልፏል፡፡ ዛሬ የተደረገው ተቃውሞ በበርካታ የተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ሲሰማ በእንቅስቃሴው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በተለይ በአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ … [Read more...] about ተቃውሞ በዝምታ
ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
በመጪው ጥቂት ወራቶች ፈረንሳይ እስከ 160 የሚጠጉ መስጊዶችን ለመዝጋት መወሰኗ ተሰማ፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ ኢማም እንዳሉት በሥራ ላይ በዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ የእምነት ቦታዎች መዘጋት አለባቸው፡፡ በኅዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ በፓሪስ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ እስካሁን ጽንፈኛ አቋም አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት መስጊዶች መዘጋታቸውን የአገር አቀፍና የአካባቢ ኢማሞች ለመምረጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢማም ሃሰን ኤል-አላዊ ለአልጃዚራ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በቀጣይ ወራቶች በርካታ መስጊዶች እንደሚዘጉ አስረድተዋል፡፡ “ከአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋር በምናደርገው ውይይት እና ይፋ በሆኑት መረጃዎች መሠረት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ታክፊሪ ንግግር የሚደረግባቸው ከ100 እስከ 160 መስጊዶች ይዘጋሉ” … [Read more...] about ፈረንሳይ እስከ 160 የሚሆኑ መስጊዶችን ልትዘጋ ነው!
የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል) … [Read more...] about የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው
ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ "የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም" የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት "በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት" በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ … [Read more...] about ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው
በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ባለሥልጣናት “ተዘርፈናል” – የሳውዲ ባለሃብቶች!
የሳውዲ ባለሃብቶች እነሱ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት” ያሏቸው አንዳንድ የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች መሬታቸውንና መሣሪያዎቻቸውን የዘረፏቸው መሆኑን በማስታወቅ ክስ አሰሙ፡፡ ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ በኢትዮጵያ ባለው አገዛዝ አንዳንድ ባለሥልጣኖች መሬታቸውን እየተቀሙ በደልና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን በአፍሪካ የሳውዲ ባለሃብቶችን ቡድን የሚመሩት ሞሀመድ አልሸህሪ የተባሉ ባለሃብት ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል። እኒሁ ባለሃብቶችን መርተው ወደ አፍሪካና ወደ ኢትዮጵያ ከአመታት በፊት ወደ የዘለቁት ባለሃብት አንዳንድ የአገዛዙ ኃላፊዎች በኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ሀገሪቱ ያስገቡትን ንብረቶች ለመውረስ በእርሳቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው ማስታወቃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል። ቅሬታ አቅራቢው ሳውዲ ባለሃብት ሞሃመድ አልሸህሪ … [Read more...] about በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ባለሥልጣናት “ተዘርፈናል” – የሳውዲ ባለሃብቶች!
ከ9ሺህ በላይ ፈላሻ ሙራዎች ወደ እስራኤል ሊጓዙ ነው
ከ25 ዓመታት በላይ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ለመጓዝ እየጠበቁ ያሉ በተለየ ፈላሻ ሙራ ተብለው የሚጠሩት ቤተ እስኤላውያን ወደ “ቅድስት አገራቸው” እንዲመጡ የእስራኤል መንግሥት ወሰነ፡፡ እስኤል እንደገቡም የአይሁድ እምነትን በተመለከተ የተሃድሶ ትምህርት እንደሚሰጣቸው ተመልክቷል፡፡ በእስራኤል ያሉ እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት የጠ/ሚ/ር ቢኒያም ኔታንያሁ መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው እሁድ ዕለት በሙሉ ድምጽ ነበር፡፡ ይህ የአሁኑ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የዛሬ ሁለት ዓመት እስራኤል ምንም ዓይነት ዜጋዋ በኢትዮጵያ እንደሌለ ይፋ ነበር፡፡ “ዛሬ ጠቃሚ ውሳኔ አስተላልፈናል” በማለት የተናገሩት ኔታንያሁ ውሳኔው በእስራኤል እየኖሩ ከቤተሰቦቻቸው ለተለያዩት ኢትዮጵያውያን ተስፋ ሰጪና ጠቃሚ እንደሆነ በላኩት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ በፊት እስራኤል “የተስፋዋ … [Read more...] about ከ9ሺህ በላይ ፈላሻ ሙራዎች ወደ እስራኤል ሊጓዙ ነው
ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም!
* ከአገዛዝ ለውጥ በፊት ችጋር ይቀድማል? * “በአሁኑ ጊዜ ችጋሩ እንደ 1977 ሆኗል!” በኢትዮጵያ ላለፉት ፴ ዓመታት ያለታየ ችጋር ተከስቷል። ድርቁና ረሃቡ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ኢህአዴግን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይፋ እያደረጉ ነው። “የምግብ ዋስትናን አረጋግጫለሁ” በማለት ሲወተውት የኖረው ህወሃት ተገዶ ያመነው ችጋር ከ፩፱፯፯ ድርቅ በላይ የከፋ እንደሚሆን ስጋት አይሏል። ከዚህ በፊት እንደተከሰቱት ለውጦች ይህኛውም የአገዛዝ ለውጥ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ። በአስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል መቋቋም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ህወሃት ከድርቅ እና ድርቅን ተከትሎ ከሚገኝ ዕርዳታ ጋር በተያያዘ ካለው አስጸያፊ ተሞክሮ በመነሳት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንደሚሉት ከድርቁ ጋር በተያያዘ ፍትሐዊነት ያሳስባቸዋል፡፡ ሲያብራሩም በከፍተኛ የሙስና እና የአድልዖ … [Read more...] about ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም!
“ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስም የኧርነስትና ያንግ የተሰኘውን የንግድ ሒሳብና ኦዲት ሥራ የሚያከናውን ኩባንያ ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ዘመድነህ ንጋቱ በኦባንግ ሜቶ ለዓምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አቤቱታ ቀረበባቸው፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለዓለምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ዋና የሥራ ኃላፊዎች ማርክ ዋይንበርገር እና ሮጀር ደንባር ጥቅምት 9፤2008 ዓም (October 20, 2015) በጻፉት ደብዳቤ የኩባንያው ሸሪክ አስተዳዳሪ አቶ ዘመድነህ ንጋቱ ኩባንያው ከቆመለት ዓላማ ውጪ በመንቀሳቀስ ከህወሃት ጋር በማበር ከሙያው ሥነምግባር ያፈነገጠ አካሄድ በመሄድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየበደሉ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ “ላለፉት 14 ዓመታት” ይላል ደብዳቤው … [Read more...] about “ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”
ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ ኤሊ ውሃ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም ስለተፈጸመው ግድያ መረጃ ልከውልናል፡፡ ከመረጃ አቀባያችን ጋር በተደጋጋሚ በተላላክነውና ባቀረብነው በርካታ ጥያቄዎች መሠረት ያገኘነው መረጃ ይህንን ይመስላል፡- እጅግ ዘግናኝ የሚባለው ግድያ የተፈጸመው ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ በሚገኘው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የእማኝ ዘጋቢው በራሳቸው አገላለጽ እንዲህ ዘግበውታል፡- (የላኩልን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም ሲሆን ወዳማርኛው እንዲህ መልሰነዋል) “ወንጀሉ የተፈጸመው ቅዳሜ መስከረም 22፤2008 ዓም በአፋር ክልል ሃዳር ወረዳ በኤሊውሃ ከተማ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የቻይና መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ ነው፡፡ የተቃጠለው ልጅ ወልዱ ይባላል፡፡ በ(ፕሮጀክቱ) … [Read more...] about ሠራተኛውን ማን አቃጠለው?










